Grade 8 SB

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 173

አማርኛ

እንደ መጀመሪያ ቋንቋ


የተማሪ መጽሐፍ

፰ኛ ክፍል
አማርኛ
እንደ መጀመሪያ ቋንቋ

የተማሪ መጽሐፍ

፰ (8ኛ) ክፍል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

አዘጋጆች፡-

ልዑል በቃሉ ዘሪሁን

ንግሥት ኪዳኔ አሰጋኸኝ

ዳግማዊት ዋጋዬ ካሳዬ

ገምጋሚና አርታኢዎች፡-

መስፍን ደፈረሱ ወልደመድህን

ትንቢት ግርማ ኃይሉ

ፋሲል ብዙነህ በቀለ

ጥራት ተቆጣጣሪና ገምጋሚ፡-

ፍሬሕይወት አሠፋ ከበደ

አስተባባሪ፦

ጌታቸው ታለማ አጥናፉ

አቀማመጥ እና ስዕል፡- እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ (TMS)


© የመጽሐፉ ህጋዊ ቅጂ ባለቤት 2014 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ነው፡፡

ምስጋና
ይህን የትምህርት መጽሐፍ ከዝግጅት ጀምሮ በከተማችን በሚያስተምሩ መምህራን
እንዲዘጋጅ በማድረግ፣ አስፈላጊውን በጀት በማስፈቀድ እንዲሁም በጥብቅ ዲስፕሊን
እንዲመራ ላደረጉት ከፍተኛ ሙያዊና አስተዳደራዊ ድጋፍ ላደረጉት ለትምህርት ቢሮ
ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ፣
እንዲሁም የዝግጅቱ ስራ ቁልፍ ስራ መሆኑን ተረድተው ትኩረት በመስጠት
በሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት፣ የአፈጻጸም ሂደቱን በመከታተል፣
በመገምገም ሁሌም ከጎናችን ለነበሩ የትምህርት ቢሮ የማኔጅመንት አባላት የስርዓተ
ትምህርት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ፣ የትምህርት ቴክኖሎጂ ዘርፍ
ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ፣ የመምህራን ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
አቶ ሳምሶን መለሰ፣ ለትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ፣ ለትምህርት
ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ፣ ለቴክኒክ አማካሪ አቶ ደስታ መርሻ ላበረከቱት
አስተዋጽኦ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

በመጨረሻም መጽሐፉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስየትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን


ለአዘጋጅ መምህራን ከዚህ በላይ ስራ የለም በማለት ፍቃድ በመስጠትና የሞራል ድጋፍ
ስላደረጋችሁም ምስጋናችን እናቀርባለን፡፡
ማውጫ
ይዘት ገፅ

መግቢያ -----------------------------------------------------------------iv

ምዕራፍ አንድ፡- የሥራ ሥነ ምግባር--------------------------------1

ምዕራፍ ሁለት፡- ባህላዊ ቅርስ--------------------------------------14

ምዕራፍ ሦስት፡- ሰብዓዊ እሴቶች----------------------------------29

ምዕራፍ አራት፡- አጭር ልቦለድ------------------------------------47

ምዕራፍ አምስት፡- ሥነ-ሕዝብ----------------------------------------65

ምዕራፍ ስድስት፡- በረሃማነት-----------------------------------------80

ምዕራፍ ሰባት፡- የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ------------------------95

ምዕራፍ ስምንት፡- ሰላም---------------------------------------------111

ምዕራፍ ዘጠኝ፡- የአየር ንብረት----------------------------------128

ምዕራፍ አሥር፡- ተውኔት----------------------------------------144

ዋቢ ጽሁፎች----------------------------------------------------------162

አባሪ
መግቢያ

ይህ መጽሐፍ አማርኛን በመጀመሪያ ቋንቋነት የሚማሩ የ8ኛ


ክፍል ተማሪዎች በቋንቋዉ በብቃት ማዳመጥ፣ መናገር፣ ማንበብና
መጻፍ እንዲችሉ፤ የቃላትና የሰዋስው ዕውቀት እንዲያገኙ
ለማድረግ የተዘጋጀ የሥርዓተ ትምህርት አካል ነው። ከዚህ
በተጨማሪም መጽሐፉ ለዚህ የክፍል ደረጃ ሥርዓተ ትምህርትና
ለሚሰጠው የትምህርት ይዘት መረጃ ይሰጣል። ከዚህም በላይ
ተማሪዎችና ወላጆች በትምህርት ቤት የተከናወኑ ተግባራትን
ለማስቀጠልና ይበልጥ ለማዳበር በጋራ እንዲሠሩ ያስችላቸዋል።

መሠረታዊ መርሆዎች
ተማሪዎች በማህበረሰብ ሕይወት ውስጥ አስፈላጊ ስለሆኑ

የማዳመጥ ይዘቶችና ርዕሰ ጉዳዮች ይማራሉ፡፡
ለነዚህ የማዳመጥ ይዘቶችና ርዕሰ ጉዳዮች የተጻፉ ምንባቦችን

ካዳመጡ በኋላ፣ በእነሱ ላይ በመመስረት ይናገራሉ፡፡
በቀጣይም በማሕበረሰቡ ውስጥ አስፈላጊ ስለሆኑ የምንባብ

ይዘቶችና ርዕሰ ጉዳዮች የሚማሩ ሲሆን የተጻፉ ምንባቦችን
ካነበቡ በኋላ፣ በዕነሱ ላይ በመመስረት ጽሑፍ ይጽፋሉ፡፡
አራቱን ክሂሎች ከላይ በተቀመጠው መሰረት ከተማሩ በኋላ

በክፍል አምስትና ስድስት የቀረቡትን የቃላትና የሰዋስው
ትምህርቶች በየምዕራፉ በተገለጸው ዓላማ መሰረት
ይማራሉ፡፡
ተማሪዎች በግላቸው ብቻ ሳይሆን አብረዋቸው ከሚማሩ

ጓደኞቻቸው እውቀትን ይቀስማሉ፡፡

IV
በቤት ውስጥ ከቤተሰብ ጋር መማር
ተማሪዎች በትምህርት ቤት የሚቀስሟቸውና በቤታቸው ከወላጆቻቸው
ጋር የሚሠሯቸው በርካታ ትምህርታዊ ተግባራት አሉ። ከእነዚህ
በርካታ ተግባራት ቢያንስ የተወሰኑትን ከወላጆቻቸው ጋር በጋራ
እንዲሠሩ ይጠበቃል።

፩. የየእለቱን ትምህርት ይዘት በተመለከተ ከቴሌቪዥን፣ ከሬዲዮ

ወይም ከድረ ገጽ ስለርዕሰ ጉዳዩ ማዳመጥ ወይም መመልከት

ይኖርባቸውል።

፪. ልጆች የተሰጣቸውን የቤት ሥራ ሲሠሩ፣ የሚከብዳቸው


ጥያቄ ካለ እና ወላጆቻቸው የሚያቁት ከሆነ መጠየቅ
ይኖርባቸማል፤ወላጆችም ለልጆች የሚቅጠይቁትን መረዳትና
ማገዝ ይኖርባቸዋል።

፫. ወላጆች የሳምንቱን ወይም የዕለቱን የምንባብ ይዘት ወይም

ርዕሰ ጉዳይ ልጆቻችሁን በመጠየቅ ተረዱ። በትምህርት ቤት

ያነበቧቸውን ምንባቦች በጋራ አንብቡ። ይህንንም ልጆች ወይም

ወላጆች ለብቻ ወይም በየተራ በማንበብ ልትተገብሩት ትችላላችሁ።

፬. ልጆቻችሁን የተለያዩ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ስለምንባቡ ተወያዩ፤

፭. ስለርዕሰ ጉዳዩ የሚያወሱ ሌሎች ጽሑፎችን ከመጻሕፍት፣

ከጋዜጦች ወይም ከመጽሔቶች ፈልጋችሁ አንብቡ።

V
፮. ልጆች ራሳቸውን ችለው በግላቸው እንዲያነቡ
አበረታቱ፤ ከዚያም ስላነበቡት ጉዳይ ተወያዩ።

፯. ልጆች በክፍል ውስጥ ምን ምን እንደተማሩ ደብተራቸውን


በጋራ ተመልከቱ፤ ስለምን እንደተማሩና ምን እንደተሰማቸው
የተለያዮ ዓይነት ጥያቄዎች በማንሳት ተወያዩ።

፰. የመጻፍ ችሎታቸውን ለማዳበር የተማሯቸውን ዝርዝር ክሂሎች


በመረዳት ምን እንደተማሩ ለማወቅ የሚከተሉትን ዓይነት
ጥያቄዎች ልጆቹን ጠይቋቸው፡፡ ለምሳሌ፡- የቃላቱ ፊደላት በተገቢ
ሁኔታ ተጽፈዋል/ ተሰድረዋል/ ወይ? በዓረፍተ ነገሮች ውስጥ/
መካከል/ ያሉት ሥርዓተነጥቦች (አራት ነጥብ፣ ነጠላ ሰረዝ፣ ድርብ

ሰረዝና የመሳሰሉት) በተገቢ ቦታቸው ገብተዋል ወይ? ወዘተ.

፱. ልጆች አጫጭር ደብዳቤዎች (ለምሳሌ፡- ለቤተሰብ አባላት


ወይም ለጓደኞች) እንዲጽፉ ወይም በዕለቱ ወይም በሳምንቱ
ስለተከሰቱ ጉዳዮች ወይም ስለአንድ ጉዳይ ያላቸውን
አስተያየት ወዘተ. እንዲጽፉ የማድረግ ልምድ ሊኖራችሁ
ይገባል።

VI
አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ምዕራፍ አንድ

የሥራ ሥነምግባር

ከምዕራፉ የሚጠበቁ ውጤቶች፣ ይህንን ምዕራፍ ተምራችሁ


ከጨረሳችሁ በኋላ፡-

በጥሞና አዳምጣችሁ በተነገረበት ዐውድ መሰረት



ትመልሳላችሁ፤
የስራ ሥነ ምግባርን ጽንሰ ሃሳብ ትገልፃላችሁ፤

አዳዲስ ሀሳቦችን አካታችሁ ጽሁፍ ትፅፋላችሁ፤

ቃላትን በተለያየ አውድ ውስጥ ትጠቀማላችሁ፤

የቋንቋውን ትክክለኛ የሰዋሰው አወቃቀር ትጠቀማላችሁ፡፡

1 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፩


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል አንድ፡- ማዳመጥ

ሰው ለሥራ
ቅድመ ማዳመጥ
ሀ. ስራ ለሰው በሚል ርዕስ ስር ምን ምን ጉዳዮች የሚነሱ
ይመስላችኋል?
ለ. የስራ ሥነ ምግባራትን ዘርዝሩ፡፡
ሐ. ከዚህ በታች ያለውን ሥዕል በማየት የተረዳችሁትን ሀሳብ

ግለፁ፡፡

አዳምጦ መረዳት

ተግባር:-

የሚከተሉትን ጥያቄዎች ባዳመጣችሁት ምንባብ መሰረት በቃላችሁ


መልሱ፡፡

፩. ንፁህ አዕምሮ ያለው ሰው ዛሬ ላይ የሰራውን ስህተት ነገ ላይ


አይደግመውም ማለት ምን ማለት ነው?
2 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፪
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፪. «ሰው የተፈጠረው በስራና ለስራ ነው» የሚለውን አባባል

አብራርታችሁ ተናገሩ፡፡

፫. አንድ ሰው ስራው ስኬታማ እንዲሆን ምን አይነት የግል

ምርጫዎችና ውሳኔዎች ሊኖሩት ይገባል?

፬. ስራን በዕውቀት ላይ ተመስርቶ መስራትና ስራን መውደድ ምን

ምን ጠቀሜታዎች እንዳሏቸው ዘርዝሩ፡፡

፭. ስራ መስራት እንዴት ራስን፣ ቤተሰብን፣ ሀገርንና ዓለምን

እንደሚቀይር አብራሩ፡፡

ክፍል ሁለት፡- መናገር


ተግባር፡-

ከዚህ በታች በቀረቡላችሁ ጥያቄዎች ላይ ተወያይታችሁ በተወካያችሁ


አማካኝነት ለክፍል ጓደኞቻችሁ በቃል አቅርቡ፡፡

፩. ተማሪዎች ስታድጉ በምን ዓይነት የሙያ መስክ ላይ


መሰማራት ትፈልጋላችሁ? ለምን?
፪. የመረጣችሁት ሙያ ምን ዓይነት የስራ ስነምግባር የሚጠይቅ
ይመስላችኋል? እንዴትና በምን ዓይነት ሁኔታስ ልትወጡት
አሰባችሁ?

፫. ጠንካራ የስራ ባህል ምን ምን ጉዳዮችን የሚያካትት ይመስላችኋል?

3 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል ሶስት፡- ንባብ
የአውራምባ ማህበረሰብና መገለጫው

4 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፬


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ቅድመ ንባብ ጥያቄዎች

፩. ጠንካራ የስራ ሥነምግባር መገለጫዎች ምን ይመስላችኋል?

፪. ስዕሉን በመመልከት የአውራምባ ማህበረሰብ ምን ዓይነት የስራ


ባህል ያለው ይመስላችኋል?

የአውራምባ ማሕበረሰብና መገለጫው


በኢትዮጵያ የእኩልነት፣ የመከባበር፣ የመደማመጥና የመቻቻል
ተምሳሌት የሆነው የአውራምባ ማህበረሰብ በዙምራ ኑሩ አማካኝነት
በ1964 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን በሥራና ሰርቶ በማደግ ብቻ
የሚያምንና ለዘላቂ ሕይወቱ መለወጥም ጠንክሮ የሚሰራ ነው፡፡
አቶ ዙምራ ከፆታ ክፍፍል የፀዳና ጠንካራ የስራ ሥነምግባር ያለው
ማህበረሰብ ለመፍጠር የነበራቸውን ምኞት እውን ለማድረግና
አዲሱን አስተሳሰባቸውን የሚጋራ ሰው ለማግኘትም ቆላ መውረድ፣
ደጋ መውጣት፣ ከማህበረሰቡ ጋር መጋጨትና መገለል ግድ
በመሆኑ በቤተሰቦቻቸውና በአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ ሳይቀር
እንደ አፈንጋጭ ወይም እንደ ዕብድ ይቆጠሩ ነበር፡፡ ድካምና ልፋቱ
ሳይበግራቸው ገና በጨቅላነት ዕድሜያቸው ወሎን፣ጐንደርንና
ጐጃምን በማካለል ሀሳባቸውን የሚቀበል ሰው ፍለጋ ሌት ተቀን
ባትለዋል፡፡

• እስካሁን ካነበባችሁት ሀሳብ በመነሳት አቶ ዙምራ የገጠማቸውን


ውጣ ውረድ ስትመለከቱ ምን ተሰማችሁ?

• በቀሪው የፅሁፍ ክፍልስ የአቶ ዙምራ አስተሳሰብ እውን የሚሆን


ይመስላችኋል?

ለአሥራ ሰባት ዓመታት መውጣት መውረዱ ቀጥሎ የኋላ ኋላ


ልፋትና ድካማቸው መና ባለመቅረቱ ፎገራ ወረዳ ውስጥ ጥቂት

5 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
1ተከታዮችን ከጐናቸው ማሰለፍ ቻሉ፡፡ እናም ዙምራ የተመኙትና
የናፈቁትን ብሎም በልጅነት እድሜያቸው ብዙ የደከሙለትና
እጅግ ከፍተኛ የሆነ መስዋዕትነትም የከፈሉለት አስተሳሰብና
የሚከተሉት ፍልስፍና ተቀባይነት በማግኘቱ መተሳሰሪያውን
ፍቅር ሕይወቱን ሥራ ያደረገ ማህበረሰብ በይፋ ተመሠረተ፡፡

የአውራምባ ማህበረሰብ አባላት የስራ ባህል ከሌላው ሕብረተሰብ


በብዙ መልኩ እንዲለዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ማሕበረሰቡ በአስተሳሰብና
በእምነት ፍጹም ለየት ያለ በመሆኑ እምነቱን ፍቅር፣ ሐይማኖቱን
ደግሞ ሥራ ያደረገ እስኪመስል ድረስ የሚንቀሳቀስ መሆኑ ብቻ
ሣይሆን ይህ ሥራ የሴት ይህ ደግሞ የወንድ የሚባል የሥራ
ክፍፍልንም ሆነ ልዩነትን አይቀበልም፡፡ ሴቶች ጠምደው ያርሣሉ፤
ሸማ ይሠራሉ፤ በአጠቃላይም በተለምዶ የወንድ ሥራ ተብሎ
በሚታወቀው ማንኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ ውስጥ ሁሉ በእኩልነት
ይሣተፋሉ፡፡ ወንዶች ደግሞ እንጀራ ይጋግራሉ፤ ወጥ ይሠራሉ፤
ጥጥ ይፈትላሉ ወዘተ. ብቻ ስራን ሳይንቁና ወደ ሌላ ሳይገፉ
በኩራት ይሰሩታል እንጅ ይኸ የሴት ስራ ነው በማለት ሀፍረት
ብሎ ነገር አይስተዋልባቸውም፡፡

ስለሆነም አውራምባዎች ሥራ ያሉትንና ለህይወታቸው ጠቃሚ


ነው ብለው የሚያምኑበትን ሁሉ ተግባብተው ይሠሩታል፤ ሁሉም
የማህበረሰቡ አባላት ከድህነትና ኋላ ቀርነት መላቀቅ የሚቻለው
በሥራና በስራ ብቻ እንጅ ቁጭ ብሎ ከሰማይ መና እንዲወርድለት
በመጸለይ እንዳልሆነ በጽናት ያምናሉ፡፡ እናም ኑሮአቸውን
ለማሻሻል ሌት ተቀን ተግተው ይሠራሉ፤ ለለውጥና ለሥራ ማነቆ
የሆኑ ኋላቀር አስተሣሰቦችን በጽናት እንጅ ጊዜ ሰጥተው በጭራሽ
ለማስታመም አይሞክሩም ብቻ ሳይሆን ለማደናቀፍ ለሚሞክሩ ስራ
ፈቶች ጊዜና ቦታ መድበው ሀሳባቸውን እንዲያደናቅፉባቸው ዕድል
አይሰጧቸውም፡፡

6 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፮


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
በእርግጥም የአውራምባ ማህበረሰብ መተሳሰሪያ ገመዱን ፍቅር
የለውጥ መሳሪያውን ደግሞ ሥራ እንዲሁም እምነቱንም በፈጣሪ
አድርጐ ከአራት አሥርት ዓመታት በላይ በጽናት ዘልቋል፡፡ መላ
የማህበረሰቡ አባላትም እርስ በርስ ከመዋደድና ከመከባበር አልፈው
ድህነትን በሥራና በሥራ ብቻ በማሸነፍ ኑሯቸውን ለመለወጥ ሌት
ተቀን ተግተው መንቀሳቀስን የሕይወታቸው አካል አድርገውታል፡
ሥራን ይወዳሉ ወይም ያፈቅራሉ ማለት ብቻ የአውራምባዎችን
ጠንካራ የስራ ባህል ለመግለጽ በቂ ቃል ሊሆን አይችልም፤
ምክንያቱም ያመልኩታልና፡፡ ይህም ሆኖ ሲሠሩ ያያቸው የአገሬው
ሰው በመደመምና በመደነቅ ጭምር ለምን ይህን ያህል ሥራን
እንደሚያፈቅሩና እስከማምለክም ድረስ መዝለቃቸውን ሲጠይቃቸው
ምኑን ሠራነው! ገና ምኑ ተያዘና ድህነት ከላያችን ላይ ሙሉ
ለሙሉ እስከሚወገድ ድረስ ጠንክረን እንሰራለን የሚል እፁብ ድንቅ
የሚያሰኝ መልስ ይሰጡታል፡፡
(በሲሳይ መንግስቴ፣ 2006 ዓ.ም ለባህልና ቱሪዝም ኢንስቲቲዩት የፓናል
ውይይት የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ፣ መጠነኛ ለውጥ ተደርጎ የተወሰደ)

አንብቦ መረዳት
ተግባር አንድ፡-

ምንባቡን በሚገባ በማንበብ የሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ

«እውነት» ስህተት ከሆኑ ደግሞ «ሐሰት» በማለት መልሱ፡፡

፩. ዙምራ ኑሩ የተመኙትን ማህበረሰብ መፍጠር ችለዋል፡፡

፪. የአውራምባ ማህበረሰብ የስራ ባህል፣ የአኗኗር ዘይቤና


የሚከተሉት ፍልስፍና ከሌላው የተለየ አይደለም፡፡
፫. የአውራምባ ማህበረሰብ አስተሳሰብ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም
አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡
7 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፯
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፬. ዙምራ በቤተሰቦቻቸውም ሆነ በአካባቢው ነዋሪ ሕብረተሰብ ዘንድ
እንደ አፈንጋጭ ወይም እንደ እብድ ይቆጠሩ ነበር፡፡
፭. ምንባቡ በሶስት አንቀፆች የተደራጀ ነው፡፡

ተግባር ሁለት፡-

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች መካከል በምንባቡ


መሰረት ተስማሚውን መልስ ምረጡ፡፡

፩. በ1964 ዓ.ም በተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ተቀባይነትን


በማግኘቱ መተሳሰሪያውን ፍቅር ህይወቱንም ስራ በማድረግ
የተመሰረተው ማህበረሰብ የቱ ነው?
ሀ. የአዊ ማህበረሰብ ለ. የአውራምባ ማህበረሰብ
ሐ. አንፌሎ ማህበረሰብ መ. የሳሆ ማህበረሰብ

፪. የምንባቡ አጠቃላይ ሀሳብ ምንድን ነው?

ሀ. የአቶ ዙምራን የህይወት ታሪክ መተረክ

ለ. የአውራምባ ማህበረሰብን ፆታዊ አድልዎ ማመልከት

ሐ. የአውራምባ ማህበረሰብን የስራ ባህል ማስቀኘት

መ. ሁሉም መልስ ይሆናል።

፫. ከሚከተሉት አንዱ የአውራምባ ማህበረሰብ ወንዶች የሚሰሩት


ስራ አይደለም፡፡
ሀ. የእንጀራ መጋገር ለ. ወጥ መስራት
ሐ. ጥጥ መፍተል መ. መልስ የለም
፬. በምንባቡ ውስጥ የተገለፀው ማህበረሰብ መተሳሰሪያ ገመዱ ፍቅር
መሆኑን የሚያስገነዝበው ስንተኛው አንቀፅ ነው
ሀ. አምስተኛው ለ. ሁለተኛው
ሐ. ሶስተኛው መ. አራተኛው
8 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፰
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፭. የአውራምባ ማህበረሰብ አባላት ከድህነትና ከኋላቀርነት መላቀቅ
የሚቻለው በምንድን ነው? ብለው ያምናሉ።
ሀ. በስራ ለ. በመለመን
ሐ. በእምነት መ.በመፀለይ
፮. አውራምባዎች ሁልጊዜ ጠንክረው በመስራት ከላያቸው ላይ
ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ የሚመኙት የስልጣኔያቸው ተግዳሮት
ምንድን ነው?
ሀ. ሀሜት ለ. ደካማ የስራ ባህል
ሐ. ድህነት መ. ኋላቀርነት

ክፍል አራት፡- ጽሕፈት


ተግባር አንድ፡-

የሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች ቅደም ተከተል በማስተካከል አንቀፅ


ፃፉ፡፡

ሀ. ሰዎች አቅደውም ይሁን ሳያቅዱ ከስራ ተለይተው አያውቁም፡፡

ለ. «ይህን አቀብይኝ፣ ያንን ዝጋው፣ ውሃ ስጠኝ ወዘተ» ሲባል ስራ


ተጀምሯል ማለት ነው፡፡
ሐ. ስራ ከዕለት ተዕለት ህይወት ጋር የተቆራኘ ነው፡፡

መ. ሰዎች ስራ የሚጀምሩት ምንነቱን ሳይረዱት ገና በህፃንነት


ዕድሜያቸው ነው፡፡
ሠ. በዕለት ከዕለት የሚያከናውኗቸው እንደ መመገብ፣ መራመድ
የግልና የአካባቢ ንፅህና መጠበቅ የመሳሰሉት ተግባራት ህይወት
በሥራ የተጠመደች መሆኗን ያመለክታሉ፡፡

9 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ



አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር ሁለት፡-

ከዚህ በታች የቀረበውን ጅምር አንቀፅ ሀሳብ ተረድታችሁ በራሳችሁ


አገላለፅ አሟልታችሁ ፃፉ፡፡

ዕለቱ ሰኞ ጠዋት ነው፡፡ ከምንኖርበት ገጠራማ ክፍል ከተማ ለገበያ


ተልኬ በሄድኩበት ነው ወሬውን የሰማሁት፡፡ የታዘዝኩትን ገዝቼ
ከጨረስኩ በኋላ ወደቤቴ ገሰገስኩ፡፡ አስናቀችን ከሩቅ አየኋት፡፡
ምንም እንኳ ወላጆቿ በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ሆነው የፈለገችውን
ባያሟሉላትም አስራ ሁለት አመት አብረን ስንማር አንድም ቀን
አንደኛ ደረጃዋን ለቃ አታውቅም፡፡ ጠርቼ በእጄ ምልክት ሰጠኋት፡፡
እየሮጠች መጣችና ሰላምታ ሰጠችኝ፡፡ በናፍቆት ስንጠብቅ የነበረው
ውጤት መውጣቱን አበሰርኳት፡፡የመደንገጥ ስሜት ፊቷ ላይ ይታይ
ነበር፡፡ ተያይዘን ሩጫችንን ወደ ትምህርት ቤት ቀጠልን….

ክፍል አምስት፡-ቃላት

የቃላት ዓውዳዊ ፍቺ

አንድ ቃል በተለያዩ አውዶች ውስጥ ሲገኝ የሚኖረው ፍች


እንደየአገባቡ ይለያያል፡፡ የአንድ ቃል ትክክለኛ ፍች የሚታወቀው
በዓረፍተ ነገር ውስጥ ገብቶ ከሌሎች ቃላት ጋር በመሆን መልዕክት
ሲያስተላልፍ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- «አገልግል» የሚለውን ቃል ወስደን
በተለያዩ ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ ያለውን አውዳዊ ፍቺ እንመልከት፡

1. እናቴ ከባህርዳር አገልግል ላከችልኝ፡፡


ፍቺ፡- ምግብ መያዣ
2. ወታደሩ ሀገርህን አገልግል ተባለ፡፡

ፍቺ፡- እርዳ፣ አግዝ ከላይ ማየት እንደሚቻለው


«አገልግል» የሚለው ቃል በሁለቱ አረፍተ ነገሮች ውስጥ
የተለያዩ ፍቺዎችን ይዟል፡፡
10 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፲
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር አንድ፡-

ከዚህ በታች ለቀረቡት ቃላት በምንባቡ መሰረት አውዳዊ ፍቺ ስጡ

ሀ. ባተሌ መ. መና
ለ. ማነቆ ሠ. ማሰላሰል
ሐ. መጎናፀፍ ረ እውን

ተግባር ሁለት፡-

ክፍል ሶስት በቀረበው ምንባብ መሰረት በ «ሀ» አምድ ለተሰጡት


ቃላትና ሐረጋት ተመሳሳያቸውን በ«ለ»ረድፍ ካሉት በመምረጥ
አዛምዱ፡፡

«ሀ» «ለ»
፩. መባከን ሀ. መሰናክል
፪. እፁብ ድንቅ ለ. ልጅነት
፫. መደመም ሐ. መልፋት
፬. ማጋበስ መ. መሰብሰብ
፭. ጉብዝና ሠ. ወጣ ያለ
፮. አረጋዊ ረ. መደነቅ
፯. አፈንጋጭ ሰ. አስገራሚ
፰. እንቅፋት ሸ. ወጣትነት
ቀ. የእድሜ ባለፀጋ

11 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፲፩


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል ስድስት፡- ሰዋስው

የቋንቋ መዋቅር

• የቋንቋ መዋቅር፡- ድምፅ ከድምፅ ጋር ተቀናጅቶ ቃልን፣


ቃል ከቃል ጋር ተገጣጥሞ ሐረግን፣ ሐረግ ከሀረግ ጋር
ተዋቅሮ ዓረፍተ ነገርን፣ ዓረፍተ ነገር ከዓረፍተ ነገር ጋር
ተቀናጅቶ አንቀፅን፣ አንቀፆች ደግሞ በቢጋር ስርዓት ባለው
መንገድ ተቀናጅተው ድርሰት የሚፈጥሩበትን ስርዓት
የሚያመለክት ጥበብ ነው፡፡ የማንኛውም ቋንቋ መዋቅር
መሰረቱ ደግሞ ድምፅ ነው፡፡

• አንድ የቋንቋ መዋቅር እርስ በርሱም ሆነ ከሌላ የቋንቋ መዋቅር


ጋር ተቀናጅቶ አዲስ መዋቅር ሲፈጥር ስርዓት ባለው መልኩ
መሆን ይኖርበታል እንጂ የተደረደሩ ድምፆች ሁሉ ቃላትን፣
ቃላትም ሀረጋትን ወዘተ. ይፈጥራሉ ማለት አይደለም፡፡

ለምሳሌ፡- /ብ-ኤ-ት/ የሚሉት ድምፆች በስርዓት ስለተቀናጁ


«ቤት» የሚል ትርጉም አዘል ቃል ሰጥተውናል፡፡ ነገር ግን
/ት-ብ-ኤ/ አይነት የድምፆች ቅደም ተከተል ቢኖር ምንም እንኳ
ፊደሎቹ ተመሳሳይ ቢሆኑም «ትቤ» የሚል ትርጉም አልባ
ነው የምናገኘው፡፡ ሌሎች መዋቅሮችም እንዲሁ ስርዓታዊ
ቅንጅታቸውን ካልጠበቁ የትርጉም ልዩነት ያመጣሉ ወይም
ደግሞ ትርጉም አልባ ይሆናሉ፡፡
ተግባር፡-

የቋንቋውን ተገቢ መዋቅር ጠብቃችሁ “የመምህርነትን የስራ


ስነምግባር” በተመለከተ አጭር ድርሰት ፃፉ፡፡

12 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፲፪


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ማጠቃለያ

በዚህ ምዕራፍ አውዳዊ ፍቺ ማለት ቃላት በተለያዩ ዓ.ነገሮች ውስጥ


ሲገቡ የሚያስገኙት ፍቺ እንደሆነና የቃላት ትክክለኛ ትርጓሜ
የሚታወቀው በዓ.ነገር ውስጥ ገብተው አውድን መሰረት አድርገን
ስንፈታቸው እንደሆነ ተመልክተናል፡፡

በመጨረሻም የቋንቋ መዋቅር መሰረቱ ድምፅ እንደሆነና ድምፆች


ተቀናጅተው ቃላትን፣ ቃላት ተቀናጅተው ሐረግን፣ሐረጋትም
ተቀናጅተው ዓ.ነገርን ወዘተ. እንደሚያስገኙ እና ሲቀናጁ ግን
የቋንቋን ስርዓት መሰረት ባደረገ መልኩ መሆን እንደሚኖርበት
ለመረዳት ችለናል፡፡

የክለሳ ጥያቄዎች
ተግባር፡-
የሚከተሉትን ቃላትና ሐረጋት በተስማሚው ዓረፍተነገር ውስጥ
በማስገባት
ዓረፍተ ነገሩን የተሟላ አድርጉ፡፡

የስራ እድል ፍቅር የስራ ባህል


ለማስተጓጎል ስራ ድህነት
1. ከ----------------------- መውጫ መሳሪያው ስራና ስራ ብቻ ነው፡፡
2. ሰዎች የራሳቸውን ኑሮ እንዲያሻሽ ከተፈለገ--------------------------
መፈጠር ይኖርበታል፡፡
3. ዓላማችንን --------------------------ጥረት ለሚያደርጉ ሰዎች ጆሮ
መስጠት ተገቢ አይደለም፡፡
4. ለሁሉም ነገር ማሰሪያ ገመዱ----------------------ነው፡፡
5. ጠንካራ ---------------------------ያለው ማህበረሰብ ምንጊዜም ቢሆን
ለድህነት እጅ አይሰጥም፡፡

13 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፲፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ምዕራፍ ሁለት

ባሕላዊ ቅርስ

ከምዕራፉ የሚጠበቁ ውጤቶች፣ ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ


ተምራችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ፡-

የሌሎችን ሀሳብ በጥሞና ታዳምጣላችሁ፤



የባህላዊ ቅርስን ምንነት ታብራራላችሁ፤

የተለያዩ የቅኔ አፈታት ዘዴዎችን ተጠቅማችሁ ቅኔዎችን

ትፈታላችሁ፤
አዳዲስ ቃላትን በተለያየ አገባብ ውስጥ ትጠቀማላችሁ፤

14 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፲፬


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል አንድ፡- ማዳመጥ

ቅርሶች በኢትዮጵያ

ቅድመ ማዳመጥ

ሀ. በሀገራችን ከሚገኙ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ


የምታውቋቸውን ተናገሩ፡፡
ለ. ከዘረዘራችኋቸው ቅርሶች ውስጥ በዩኔስኮ የባህል፣ የትምህርትና
የሳይንስ ማዕከል የተመዘገቡት የትኞቹ ይመስሏችኋል?

15 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፲፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

አዳምጦ መረዳት

ተግባር አንድ፡-

የሚከተሉትን ጥያቄዎች ባዳመጣችሁት ምንባብ መሰረት ትክክል


ከሆኑ “እውነት” ስህተት ከሆኑ ደግሞ “ሐሰት” በማለት መልሱ፡፡

፩. የጦርነት ጊዜ ሽለላዎች በቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስችላቸውን


መስፈርት ሊያሟሉ አይችሉም፡፡
፪. ቅርሶች ከምንጭ አንፃር ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ተብለው
በሁለት ይከፈላሉ፡፡
፫. የጢያ ትክል ድንጋይ በዩኔስኮ ከተመዘገቡ ቅርሶች መካከል
አንዱ ነው፡፡
፬. የቀድሞ አባቶቻችንና እናቶቻችን ሰርተው እና ተጠቅመውበት
ያለፉት ሀብት ቅርስ ሊሆን አይችልም፡፡
፭. በዩኔስኮ ከተመዘገቡ የስነ-ፅሁፍ ቅርሶች መካከል ስምንቱ የብራና
ላይ ፅሁፎች ናቸው፡፡

ተግባር ሁለት፡-
ለሚከተሉት ጥያቄዎች የተነበበላችሁን የማዳመጥ ምንባብ መሰረት
በማድረግ ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡

፩.------------------------------የህዝቦች ማንነት የሚገለፅበትና የረጅም


ዘመን ባህላቸውንና ታሪካቸውን እንዲገነዘቡ የሚረዳ ቁሳዊና
መንፈሳዊ ሀብት ነው፡፡
ሀ. ውርስ ለ. ስጦታ ሐ. ቅርስ መ. ኑዛዜ
፪. የተባበሩት መንግስታት የሳይንስና የባህል ማዕከል በዓለም
ቅርስነት ከመዘገባቸው ቅርሶች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር
የያዘችው አፍሪካዊት ሀገር ማን ናት?

16 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፲፮


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ሀ. ሱዳን ለ. ኢትዮጵያ ሐ. ኡጋንዳ መ. ታንዛንያ

፫. ከሚከተሉት ውስጥ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ተብሎ በዩኔስኮ


የተመዘገበው የትኛው ነው?
ሀ. የመስቀል በአል ለ. የገዳ ስርዓት ሐ. ፍቼጨምበላላ
መ. ሁሉም
፬. ከኢትዮጵያ በዩኔስኮ የተመዘገቡ እና በብራና ላይ የተፃፉ የስነ
ፅሁፍ ቅርሶች ስንት ናቸው?
ሀ. ስምንት ለ. ዘጠኝ
ሐ. ሰባት መ. አስራሁለት
፭. በዩኔስኮ የቅርስ መዝገብ የሚዳሰሱ ቅርሶች ተብለው ከተመዘገቡ
የኢትዮጵያ ቅርሶች ውስጥ የማይካተተው የትኛው ነው?
ሀ. አክሱም ለ. ላሊበላ ሐ. የጀጎል ግንብ
መ. መልስ አልተሰጠም
፮. ከሚከተሉት አንዱ በዩኔስኮ ከተመዘገቡ የስነ-ፅሁፍ ቅርሶች
ውስጥ አይመደብም፡፡
ሀ. አፄቴዎድሮስ ለእንግሊዟ ንግሥት የፃፉት ደብዳቤ
ለ. ቀዳማዊ ኃይስላሴ ለአሜሪካው ፕሬዘዳንት የፃፉት
ደብዳቤ
ሐ. ዳግማዊ አፄ ምንሊክ ለሞስኮው ንጉሥ የፃፉት ደብዳቡ
መ. ንጉሥ ሳህለሥላሴ ለእንግሊዟ ንግሥት የፃፉት ደብዳቤ

ክፍል ሁለት፡- መናገር


ተግባር፡-
ከዚህ በታች በቀረቡላችሁ ጥያቄዎች ላይ ተወያይታችሁ
በተወካያችሁ አማካኝነት ለክፍል ጓደኞቻችሁ በቃል አቅርቡ፡፡

፩. ባህላዊ ቅርስ ማለት ምን ማለት ነው?

፪. በባህላዊ ቅርስ ውስጥ የሚካተቱት ሀገር በቀል ቅርሶች ምን


ምን ይመስሏችኋል?
17 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፲፯
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፫. ቅርስን የመጠበቅ ሀላፊነት ያለበት ማን ይመስላችኋል? ለምን?

፬. በኢትዮጵያ ቅርስን ባህላዊና ዘመናዊ ብሎ የመመደብ ስልጣን


ያለው አካል ማን ነው?
 ባህላዊና ዘመናዊ ብሎ ለመፈረጅስ መስፈርቱ ምን
ይመስላችኋል?
(በአካባቢያችሁ ካለ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት በመጠየቅ መልሱን
ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡ፡፡

ክፍል ሶስት፡- ንባብ

ቡሄና ቃላዊ ግጥሞቹ

ቅድመ ንባብ ጥያቄዎች


፩. በቡሄ ጊዜ ግንባር ቀደም ተዋናዮች እነማን ይመስሏችኋል?
፪. በቡሔ ጌዜ የሚደረደሩ ቃላዊ ግጥሞችን እያነሳችሁ ተወያዩ፡፡

፫. በድሮ ጊዜ እና አሁን በሚደረደሩ የቡሄ ቃላዊ ግጥሞች ላይ

ልዩነት የሚኖር ይመስላችኋል? ለምን? በማስረጃ ለማሳየት


ሞክሩ፡፡
፲፰
18 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ቡሄና ቃላዊ ግጥሞቹ

ቡሄ ከባዱ የክረምት ወራት ዝናቡ፣ ብርዱና ደመናው ተወግዶ


የብርሃን ወገግታ ሲታይ የሚከበር በዓል ነው። ሰማይ ከጭጋጋማነት
ተላቆ ወደ ብሩህነት ይሸጋገራልና ሳይጠያየቅ የቆየው ዘመድ አዝማድ
ወደነበረው ማህበራዊ ህይወቱ የሚመለስበት ጊዜም ነው። በዚህም
ሆያ ሆዬ…ሆ… በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን
የሚያስተላልፉ ልጆች ከቤተሰቦቻቸው ፈቃድ አግኝተው በየቤቱ
እየተዘዋወሩ ይጨፍራሉ። በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን ጅራፍ
በማጮህ፤ ችቦ በማብራት፤ ሙል ሙል ዳቦ በማዘጋጅትና
በልጆች ጭፈራ ይከበራል፡፡ የቡሄ በዓል ከሌሎች በዓላት በፊት
የሚከበርና የሌሎች በዓላት መነሻ በመሆንም ያገለግላል፡፡ ቀዳሚና
የበዓላት መነሻ መሆኑም በሥነ-ቃል አማካኝነት እንዲህ ይገለፃል፡፡

የበዓል መነሻ ቡሄ ነውና በጋራ እናክብረው ሰብሰብ በሉና። በዓሉ


በተለያዩ ክልሎች በተለያየ ስያሜ ይከበራል፡፡ ለምሳሌ፡- በኦሮሚያ
ክልል «ኡኬ»፣ በአማራ ክልልና በአዲስ አበባ ደግሞ ደብረታቦር
ወይም ቡሄ በመባል ይታወቃል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስትያን ደግሞ የክርስቶስ መገለጥ ቀን ተብሎ ይጠራል፡፡ በቡሄ
በዓል ጊዜ ቀድሞ ይደረደሩ የነበሩት ቃላዊ ግጥሞች በአሁኑ ሰዓት
በተለይም በከተማዎች አካባቢ ቅርፃቸውን ከመቀየራቸውም ባሻገር
የትርጉም ለውጥም ይስተዋልባቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም፡፡

19 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፲፱


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ልጆች ድሮ፡-
ክፈት በለው በሩን
የጌታየን፤

ክፈት በለው ተነሳ

ያንን አንበሳ--- እያሉ በመጨፈር በአቀንቃኙ መሪነት ወደ


ሚጨፍሩበት ቤት ያመራሉ። ከዚያም

ዝና ጠይቆ የመጣ እንግዳ

እራቱ ሙክት ምሳው ፍሪዳ------ እያለ አቀንቃኙ ሲያዜም


ተቀባዮችም ይህንን ይደግማሉ። አያይዘውም

ሆያ ሆዬ፣

ወይ የኔ ጌታ ዋርካ ነህ ዋርካ

ቢጠለሉብህ የማታስነካ--- ሲል አቀንቃኙ፣ ተቀባዮቹም “ሆ” እያሉ


አባወራውን ያሞግሳሉ። በዚያም ሳይበቃቸው ለእማወራዋም እንዲህ
ሲሉ ይገጥሙላታል።

የኔማ እመቤት መጣንልሽ

የቤት ባልትና ልናይልሽ።

የኔማ እመቤት ብትሰራ ዶሮ

ሽታው ይጣራል ገመገም ዞሮ---እያሉ ወይዘሮዋን በሙያዋና


በባልትናዋ ያወድሷታል። ይህንን ሁሉ ብለው የዳቦ ስጦታው የዘገየ
ከሆነ የሚሉት ነገር አይጠፋቸውም።

20 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፳


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ለምሳሌ፡-
አንዱን አምጭው አታማርጭው
ወደ ጓዳ አታሩጭው፤ ይላሉ። ከዚያ የልጆቹ መምጣት የምስራች
ማብሰር ሆኖ ስለሚቆጠር ባለቤቱ በደስታ ይቀበላቸዋል። መርቆ
ሙልሙል ዳቦ ሰጥቶም ይሸኛቸዋል። ወጣቶችም በተራቸው እንዲህ
እያሉ ይመርቋቸዋል።
ክበር በስንዴ ክበር በጤፍ ምቀኛህ ይርገፍ---እያሉ ይመርቋቸዋል፡፡
ይህ ሁሉ በከተማውም በገጠሩም ቀደም ሲል የነበረ የቡሄ አከባበር
ነው። አሁንስ ከተባለ ገጠሩ ላይ ብዙም ለውጥ አይታይም፤ የቃል
ግጥሙ ልዩነት የመጣው ወደ ከተማው ሲገባ ነው። ለአብነት በአዲስ
አበባ ከተማ የሚደረደሩ ቃላዊ ግጥሞችን ስንመለከት፡-

አስዮ ቤሌማ ሆሆ

አስዮ ቤሌማ የቤሌማ እናት

ሆሆ አስር …ፎቅ አላት…በማለት ጉዞ ወደ ሚጨፍሩበት ቤት


ያደርጋሉ። ከዚያ እንደደረሱም፡-

መጠለሉንስ ተጠልያለሁ ያችን ስሙኒ የት አገኛለሁ። እያሉ


ያዜማሉ። ቀጥለው ደግሞ ወደሙገሳው ይገባሉ።

እዚያ ማዶ አንድ ሻሽ
እዚህ ማዶ አንድ ሻሽ
የኔማ እገሌ ወርቅ ለባሽ---
እዚያ ማዶ አንድ ጀሪካ

21 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፳፩


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
የኔማ ጋሽዬ ሊሄድ ነው አሜሪካ--- በማለት ስደትንና ውጭ
ናፋቂነትን የሚያበረታታ ይዘት ያለው ግጥም ይደረድራሉ፡፡ ይህ
ደግሞ ጥሩ መልዕክት ስለሌለው መስተካከል ይኖርበታል፡፡

ተማሪዎች እስካሁን ካነበባችሁት ሀሳብ በመነሳት ስለ ቡሄ



በዓል አከባበር ምን ተረዳችሁ?

በቀሪው የምንባቡ ክፍልስ ስለ ቡሄ ምን የሚነሳ



ይመስላችኋል?

የሁለቱን ዘመናት ግጥሞች በዋናነት አንድ የሚያደርጋቸው


የሚባሉበት አውድ ሲሆን የሚከወኑበት ጊዜና ቦታም ተመሳሳይ
ነው፡፡ ጭፈራውን የሚያከናውኑት ልጆች የዕድሜ ሁኔታም ቢሆን
ተመሳሳይነት አለው። ምንም እንኳ የሰንጎ መገን እና የወል ቤት
ቅርፅ ያላቸው አንዳንድ ስንኞች ቢኖሩም በሐረግ ያላቸው የቀለም
ምጣኔ ተመሳሳይነትም አንድ ያደርጋቸዋል። በየዘመናቱ የተጠቀሱ
ግጥሞች በቃላት አጠቃቀምና በግጥም አፈጣጠር ደግሞ ልዩነት
አላቸው፡፡ በአንደኛው ዘመን የሌሉ የቃላት አጠቃቀሞች በሌላኛው
ዘመን ላይ ይስተዋላሉ፡፡ በተለይም በቀደምት የቡሄ በሉ ግጥሞች
ውስጥ ያሉ ቃላት በአሁኑ ዘመን ላይ አይታዩም፡፡ ከእነዚህም
ውስጥ አጋፋሪ፣ ጥጃ፣ ገመገም፣ የንብ እንጀራ፣ የሸረሪት ድር
የሚሉት ቃላት በአሁን ዘመን ላይ ካሉት ግጥሞች ውስጥ
እምብዛም አይታዩም። የዘመናት ልዩነት የቡሄ ቃላዊ ግጥሞችን
ለውጥ ማምጣቱ ተፈጥሯዊ ቢሆንም ባህል፣ ወግና ማንነትን
ባለቀቀ መልኩ ቢሆን የተሻለ ነው፡፡
(በጽጌረዳ ጫንያለው፣ ነሃሴ 12/2011፣ አዲስ ዘመን ለዚህ የክፍል
ደረጃ ተሻሽሎ የቀረበ)

22 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፳፪


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
አንብቦ መረዳት

ተግባር አንድ፡-
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት ትክክል ከሆኑ «እውነት»
ስህተት ከሆኑ ደግሞ «ሐሰት» በማለት መልሱ፡፡

፩. ከይዘት በስተቀር ወግና ማንነትን ባለቀቀ መልኩ በዘመናት


ልዩነት በቡሄ ቃላዊ ግጥሞች የቃላት አጠቃቀም ላይ ለውጥ
ቢታይ ችግር የለውም፡፡
፪. የቡሄ በዓል ልጆች እየዞሩ በመጨፈር የሚያከብሩት ነው፡፡

፫. በቀድሞም ሆነ በአሁኑ ጊዜ በቡሄ ወቅት የሚደረደሩ ቃላዊ


ግጥሞች ይዘታቸው (የሚያስተላልፉት መልዕክት) ተመሳሳይ ነው፡፡
፬. በየዘመናቱ የተጠቀሱ የቡሄ ቃላዊ ግጥሞች የቃላት አጠቃቀምና
የግጥም አፈጣጠር ልዩነት አላቸው፡፡
፭. በቡሄ ጊዜ የሚደረደሩ ቃላዊ ግጥሞች በሐረግ ያላቸው የቀለም
ምጣኔ ሁል ጊዜም ተመሳሳይ ነው፡፡

ተግባር ሁለት፡-
ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች መካከል በምንባቡ
መሰረት ተስማሚውን መልስ ምረጡ፡፡

፩. ቡሄ የሚለውን በዓል ከበዓላት አኳያ በየትኛው እንመድበዋለን


ሀ.ከህዝባዊ ለ.ከባህላዊ ሐ.ከድል መ.መልስ አልተሰጠም

፪. የቡሄ በዓል ሲከበር ከሚከናወኑ ተግባራት ውስጥ የማይካተተው


የቱ ነው?
ሀ. ጅራፍ ማጮህ ለ. ችቦ ማብራት

ሐ. ሙልሙል ዳቦ ማዘጋጀት መ. የአዛውንቶች ጭፈራ

23 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፳፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፫. በቡሄ ጊዜ በሚደረደሩ ቃላዊ ግጥሞች ላይ በአብዛኛው ልዩነት
እየታየ ያለው የት ነው?
ሀ. በገጠር ለ. በከተማ

ሐ. በትምህርት ቤት መ. በቀበሌ
ተግባር ሦስት
ቀጥሎ የቀረቡትን ጥያቄዎች እንዳጠያየቃቸው መልስ ስጡ፡፡

1. በምንባቡ አንቀፅ ሁለት ላይ ቡሄ «ቀዳሚ የበዓላት መነሻ» ተብሎ


የተገለፀው ለምንድን ነው?
2. የኔማ እመቤት ብትሰራ ዶሮ
ሽታው ይጣራል ገመገም ዞሮ ሲል ምን ለማለት ተፈልጎ ነው?
3. በሁለቱ ትውልድ መካከል ያለው የባህል ውርርስ ላይ ልዩነት
እንዲፈጠር ያደረገው ነገር ምንድ ነው?
ተግባር አራት
ማስታወሻ፡- ቅኔና የቅኔ አፈታት ዘዴዎች
ቅኔ አዕምሮ እንዲቀለጥፍ፣ ጥልቅ የሆነ የማሰብ ችሎታ እንዲኖርና ነገሮችን
በቀላሉ የመረዳት ችሎታን ለማዳበር የሚረዳ ጥበብ ነው፡፡ በተጨማሪም
የሰው ልጅ ደስታውን ፣ሐዘኑን፣ ቁጭቱን ድጋፍ ተቃውሞውን ለመግለጽ
ቅኔ ይቀኛል፡፡ በርካታ የቅኔ አይነቶች አሉ፡፡ የትኛውንም አይነት የቅኔ
ዓይነት አዳምጠን ወርቁን (ሚስጥራዊ ፍቺውን) ለመረዳት ከሚያግዙ
የአፈታት ዘዴዎች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ ታሪክን ጠንቅቆ
ማወቅ፣ ቃላትን ሁለት ቦታ በመክፈል፣ ቃልን በማጥበቅና በማላላት፣
ቃልን ከቃል በማጣመር፣ ከቃል ውሰጥ ምዕላዶችን በማውጣት ፣ አንድ
ቃል ከአንድ በላይ ፍቺ እንዳለው በመመርመር ወዘተ. የአንድን ቅኔ
ሚስጥር ለመረዳት የሚያግዙ ዘዴዎች ናቸው፡፡

24 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፳፬


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
መምህራችሁ በሚሰጣችሁ መመሪያ መሰረት ከላይ በተገለጹት የቅኔ
አፈታት ዓይነቶች ሊፈቱ የሚችሉ ስድስት ቅኔዎቸን ቤተሰቦቻችሁን
በመጠየቅ ይዛችሁ በመምጣት ለመምህራችሁ አሳዩ፡፡

ክፍል አራት፡- ጽሕፈት


ድርሰት

 በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ አንቀፆችን የያዘ የስነፅሁፍ


ክፍል ነው፡፡
 የተለመዱ የድርሰት አይነቶች አራት ናቸው፡፡ እነሱም፡- ተራኪ
ድርሰት፣ ስዕላዊ ድርሰት፣ አመዛዛኝ ወይም አከራካሪ ድርሰትና
ገላጭ ወይም አስረጂ ድርሰት ናቸው፡፡ ከነዚህ የድርሰት አይነቶች
በዋናነት የምናየው አመዛዛኝ ወይም አከራካሪ ድርሰትን
ይሆናል፡፡
አከራካሪ ድርሰት፡- ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ተቃራኒ ሀሳቦችን
በማመዛዘን የትኛው እንደሚሻል የሚያሳይ የድርሰት አይነት ነው፡፡

ለምሳሌ፡-አንድ ደራሲ በአንድ መድሃኒት ቀማሚ ይመሰላል፡


ምክንያቱም መድሃኒት ቀማሚ ሳይማርና ልምድ
ሳይኖረው መድኃኒት ቀማሚ እሆናለሁ ቢል ተቀባይነት
እንደማይኖረው ሁሉ ደራሲም አንድ ጽሁፍ ከማዘጋጀቱ
በፊት የፅሁፉን ስርዓት ጠንቅቆ ማጥናት ይጠበቅበታልና፡፡

ተግባር፡-

«ቅርሶችን የመጠበቅ ሀላፊነት የመንግስት ብቻ ወይስ የእያንዳንዱ


ግለሰብ? በሚል ርዕስ ባለ ሶስት አንቀፅ ድርሰት ፅፋችሁ ለክፍል
ጓደኞቻችሁ አቅርቡላቸው፡፡

25 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፳፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል አምስት፡- ቃላት

አውዳዊ ፍች
ተግባር አንድ፡-
ከዚህ በታች ያሉትን ቃላት በምንባቡ መሰረት አውዳዊ ፍቻ ጻፍ።

ሀ. ጓዳ ሠ. ዝና
ለ. እማወራ ረ. መጠለል
ሐ. አባወራ ሰ ባልትና
መ. ማበርከት ሸ. ሙልሙል
ተግባር ሁለት፡-
በ «ሀ» አምድ ለተሰጡት ቃላት ተመሳሳያቸውን በ«ለ» አምድ
ካሉት በመምረጥ አዛምዱ፡፡
«ሀ» «ለ»
፩. ወገግታ ሀ. ቦታ፣ ሁኔታ
፪. ቀዳሚ ለ. ሀያአምስት ሳንቲም
፫. መገለጥ ሐ. ለምሳሌ
፬. አውራጅ መ. መታየት
፭. ማብሰር ሠ. አቀንቃኝ
፮. ስሙኒ ረ. መጀመሪያ
፯. አውድ ሰ. ፀዳል
፰. ለአብነት ሸ. መንገር
ቀ. ንዑሳን
ክፍል ስድስት፡- ሰዋስው
ጊዜ

አንድ ድርጊት መቼ እንደተፈጸመ ወይም መቼ እንደሚፈጸም


የሚገልጽ የግስ ባህሪይ ሲሆን በሶስት ይከፈላል፡፡
26 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፳፮
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
እነሱም፡-
፩. የአሁን ጊዜ
፪. የኃላፊ ጊዜ
፫. የትንቢት ጊዜ ናቸው፡፡ ከነዚህ ሶስት የግስ አይነቶች

ውስጥ የአሁን ጊዜ ግስን በዚህ ርዕስ እናያለን፡፡

የአሁን ጊዜ፡- በአሁን ጊዜ የሚፈጸም ወይም በመፈጸም ላይ ያለ


ድርጊትን ወይም ሁነትን የሚገልጽ የጊዜ አይነት ነው፡፡ አሁን
የሚባለው አንድ ሰው ስለ አንድ ድርጊት ወይም ሁነት ንግግር
በሚያደርግበት ጊዜ ስለሆነ ነው፡፡ የአሁን ጊዜ ግሶች ‹‹እየ-›› የሚል
ምእላድ ሊያስቀድሙና ‹‹ነው›› የሚል ረዳት ግስ ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
ምሳሌ፡- ፋጡማ ምሳዋን እየበላች ነው፡፡
ሀጎስ ቡና እየጠጣ ነው፡፡
ተግባር አንድ፡-
የሚከተሉትን ጥያቄዎች አንብባችሁ የአሁን ጊዜ የሚያመላክት ግስ
የያዙ ዓረፍተነገሮችን ፊደል ክበቡ፡፡

ሀ. አልማዝ የተሰጣትን የቤት ስራ እየሰራች ነው፡፡


ለ. ግርማ ከአዳማ እየመጣ ነበር፡፡
ሐ. ት/ቤታችን አስረኛ ዓመቱን ዘንድሮ እያከበረ ነው፡፡

መ. የወንድሜ ልጅ ቡሌ ሆራ ዩንቨርሲቲ እየተማረች ነው፡፡

ሠ. መሃመድ በሚቀጥለው ዓመት ይመረቃል፡፡

ተግባር ሁለት፡-

የአሁን ጊዜ ግሶችን በመጠቀም አምስት ዓረፍተ ነገሮችን ስሩ፡፡

27 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፳፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ማጠቃለያ
በዚህ ምዕራፍ የተለመዱ የድርሰት አይነቶች ተራኪ ድርሰት፣ስዕላዊ
ድርሰት፣ አከራካሪ ድርሰት እና ገላጭ ድርሰት እንደሆኑናአከራካሪ
ድርሰት የሚባለው ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቃራኒሀሳቦችን
በማመዛዘን የትኛው እንደሚሻል የምናሳይበት የድርሰትአይነት
እንደሆነ ተገንዝበናል፡፡
በመጨረሻም የአሁን ጊዜ፣ የሀላፊ ጊዜ እና የትንቢት ጊዜግሶች
እንዳሉና የአሁን ጊዜ ግሶች በአሁን ጊዜ የሚፈፀምወይም በመፈፀም
ላይ ያለን ድርጊት የሚገልፁ መሆናቸውንአይተናል፡፡

የክለሳ ጥያቄ

ተግባር፡-

ከሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ የአሁን ጊዜ ግስ የያዙ ዓረፍተ


ነገሮችን ፊደል በመክበብ አመልክቱ፡፡

ሀ. መቅደላዊት ወደትምህርት ቤት እየመጣች ነው፡፡

ለ. ማህደርን ትናንትና መርካቶ አየኋት፡፡

ሐ. አባይ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ እየተገደበ ነው፡፡

መ. በረከት ፒያሳ እሄዳለሁ ብሎኝ ነበር፡፡

ሠ. ቃለአብ የቤት ስራውን እየሰራ ነው፡፡

ረ. ዳዊት በሚቀጥለው ሳምንት ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ ይመለሳል፡

ሰ. ወደፊት በሥነምግባር የታነፀ፣ በእውቀት የጎለበተ ጥሩ መምህር


መሆን እፈልጋለሁ፡፡

28 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፳፰


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ምዕራፍ ሶስት

ሰብዓዊ እሴቶች

ከዚህ ትምህርት የሚጠበቁ ውጤቶች፣ ይህንን ምዕራፍ ተምራችሁ


ከጨረሳችሁ በኋላ፡-
 አዳምጣችሁ የጽሁፉን መልእክት ትመዝናላችሁ፤
 ሰለ ሰብዓዊ እሴት ምንነት ታብራራላችሁ፤
 ከሌሎች ጋር ምልልስ ታደርጋላችሁ፤
 በሰብዓዊ እሴት ውስጥ የሚካተቱ ነገሮችን ትዘረዝራላችሁ፤
 የቀረበላችሁን ጽሁፍ በመመዘን የተገነዘባችሁትን በአራት
አንቀጽ ትጽፋላችሁ

29 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፳፱


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል አንድ፡- ማዳመጥ
ዶክተር ካትሪን ሀምሊን
ቅድመ ማዳመጥ

ተማሪዎች ‘‘በጎነት ለራስ ነው’’ የሚባለው ለምን



ይመስላችኋል?
በሀገራችን በበጎ አድራጎት ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችን

ወይም ድርጅቶችን ስም ጥቀሱ፡፡
ዶክተር ካትሪን ሀምሊንን ከፊስቱላ በሽታጋር የሚያገናኛቸው

ምን ይመስላችኋል?
ከዚህ በታች የቀረበውን ስዕል አይታችሁ የተረዳችሁትን

ግለፁ፡፡

አዳምጦ መረዳት

ተግባር፡-
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ባዳመጣችሁት ምንባብ መሰረት በጽሁፍ
መልሱ፡፡

፩. የምንባቡ አጠቃላይ ሀሳብ ምንድን ነው?


30 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፴
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፪. ዶክተር ካትሪን ሀምሊን የየትሀገር ተወላጅ ናቸው?
፫. በምንባቡ ውስጥ በጎ ስራቸው የተዳሰሰላቸው ዶክተር የምን ሙያ
ባለቤት ናቸው?
፬. ባለታሪኳ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲቆዩ ያስገደዳቸው ምክንያት
ምንድን ነው?
፭. ምዶክተር ካትሪን ሀምሊን የመጀመሪያውን የፌስቱላ
ሆስፒታልያ ያሠሩት የት ነው?
፮. ዶክተር ካትሪን ሀምሊን ሴቶችን በህክምና ከመርዳት ባለፈ ምን
ምን ጉዳዮች ያከናውኑ ነበር?
፯. የዶክተሯ አስተዋፅኦ በዋጋ የሚተመን ይመስላችኋል? እንዴት?
፰. የበጎ ስራ ባለቤት ለሆኑት ዶክተር ሀምሊን ከተበረከቱላቸው
ሽልማቶች መካከል ቢያንስ ሶስቱን ዘርዝሩ፡፡

ክፍል ሁለት፡- መናገር

ጭውውት
ጭውውት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች እርስ በዕርስ
የሚያካሂዱት ምልልስ ነው፡፡ በጭውውት ወቅት አንዱ ከሌላው
የችግርን መፍቻ ሀሳብ ያገኝበታል፤ ልምድም ይጋራበታል፡፡
በጭውውት ጊዜ የእርስ በዕርስ መደማመጥና መከባበር እንደተጠበቀ
ሆኖ ቀልዶችን ጣል ጣል እያደረጉ ዘና ማለት የተለመደ ነው፡፡
ተግባር አንድ፡-

አራት አራት ሆናችሁ በመቧደን ከዚህ በታች የቀረበላችሁን


ጭውውት በተግባር ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡ፡፡

(እናት ወ/ሮ ትዕግስት እርጅና የተጫጫናቸው ከመሆናቸውም


በላይ፣ አብዛኛዎቹ ጥርሶቻቸው ወልቀው ከቀሩት ጥቂት
ጥርሶች መካከል የመንጋጋ ጥርሳቸውን አሟቸዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ
የሆስፒታል ቀጠሮ አላቸው፡፡ ልጃቸው ይበልጣል ባለቤቱን
አመለወርቅን ወደ እናቱ ቤት ልኮ ሀኪም ቤት የሚወስዳቸውን
መኪና ለማፈላለግ ወደኋላ ቀርቷል፡፡ አመለወርቅ አማቷ
ቤት በደረሰች ጊዜ ወ/ሮ ትዕግስት ፊት ለፊት ተቀምጠው
31 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፴፩
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ከጎረቤታቸው ከአቶ ጥበቡ ጋር እየተጫወቱ ነበር፡፡)

አመለወርቅ፡- “ሰላም ለዚህ ቤት! እንደምን አደራችሁ!”

አቶ ጥበቡ፡- “ፈጣሪ ይመስገን እንዴት ሰነበትሽ?”

አመለወርቅ፡- “እማማ! እንዴት ነዎት ዛሬ?” አለች ከአቶ ዳንኤል

ጋር እጅ ከተለዋወጠች በኋላ ወደ አማቷ ጠጋ ብላ፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት፡- “በጎ ነኝ ልጄ! መቼም ከትናንትናው ዛሬ መለስ

ብሎልኛል” ካሉ በኋላ ወዲያውኑ “ይበልጣልን የት


ጥለሽው መጣሽ?” ብለው ጠየቋት፡፡
አመለወርቅ፡- ከቤት አብረን ወጣንና “አንቺ ቀድመሽ እማማን

አዘጋጃት እኔ መኪና አፈላልጌ ልምጣ” ብሎኝ ነው

የተለያየነው፤ ‘‘አሁን ይመጣል’’፡፡ ካለች በኋላ፣

ፊታቸውን የተሸፋፈኑበትን ነጠላ ገልጣ ለማየት

እየሞከረች፣ “ኧረ ተመስገን ነው፤ ዛሬማ እብጠቱንም

ቀንሷል እኮ!“ አለች፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት፡- “እኔማ መቼም ሲይዘኝ ‘ኑሮ ኑሮ ከመሬት፣

ዞሮ ዞሮ ከቤት’ ነውና መሞቴ ካልቀረ ለምን እድሜ

ሰጥተህ ታሰቃየኛለህ? እያልኩ፣ ፈጣሪየን

አማረርኩት፡፡ የሱ ቸርነት አያልቅም፤ አሁን ደግሞ

ተንፈስ አደረገኝ፡፡”

አቶ ጥበቡ፡- “አይ እሜቴ! ለምን ሆደ ባሻ ይሆናሉ? በትንሽ

በትልቁ ፈጣሪን ማማረር የለብዎትም ‘እግዜር በትር


32 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
፴፪
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ሲቆርጥ ቆላ አይወርድም’ ሲባል አልሰሙም?”

ወ/ሮ ትዕግስት፡- “አይ ዳንዬ! በጊዜ በሰበሰበኝ ምንኛ ደግ ነበር?

አየህ! የሰጠኝን በሽታ ሁሉ ሆዴን አስፍቼ ችየው

ነበር፡፡ አሁን ግን የማልችለውን እየሰጠኝ ነው፡፡ ‘ልጅ

ከጦረው ጥርስ የጦረው’ ይባላል እኮ!” እንዳሉ


ይበልጣል ወደ ቤት ይገባል፡፡

አቶ ይበልጣል፡- “እንዴት አደራችሁ? ምነው ፍርዬ፣ እማማን

አላዘጋጀሻትም እንዴ!?” ካለ በኋላ፣ መለስ ብሎ

“እማማ! ተሸሎሽ አደረ?” አላቸው፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት፡- “በጎ ነኝ ልጄ! ምንም አልል፡፡ ና እንግዲህ

መኪናውን ካመጣህ ደገፍ አድርገኝና እንሂድ፡፡”

አቶ ይበልጣል፡- “እሺ! አይዞሽ እማማ ትድኛለሽ” እያለ ደግፎ

ያነሳቸዋል፡፡ “አይዝዎት! አይዝዎት! ይድናሉ” እያሉ

አቶ ዳንኤልና ፍሬህይወትም እየደገፏቸው

ይወጣሉ፡፡

ተግባር ሁለት፡-
ጥንድ ጥንድ በመሆን ከዚህ በታች በቀረበላችሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ
ውይይት አድርጉ፡፡
• ሰዎችን ማክበር ማለት ምን ማለት ነው?
• በሰብአዊ እሴት ውስጥ የሚካተቱትን ነገሮች ዘርዝሩ፡፡
• በአካባቢያችሁ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችንና
ግለሰቦችን በመዘርዘር የሚያከናውኑትን ተግባር አስረዱ፡፡

33 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፴፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
• ከሁለት አንዳችሁ ከላይ በተወያያችሁባቸው ርዕሰ ጉዳዮች
ላይ መረጃ ሰጪ ንግግር አድርጉ፡፡

ክፍል ሶስት፡- ንባብ


ጉርብትና

ቅድመ ምንባብ ጥያቄዎች

፩. ሰዎች ከጎረቤቶቻቸው ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት ሊኖራቸው


ይገባል ብላችሁ ታስባላችሁ?
፪. ‹‹ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት›› የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር
ምንን የሚያበረታታ ይመስላችኋል?
፫. «ጉርብትና» የሚለውን ምንባብ ርዕሱንና ስዕሉን በመመልከት
ይዘቱን ገምቱ?
ጉርብትና
በአጓጉል ጨዋታዎች ላይ መሆናችንን የሚያስጠነቅቀን ዞርበሉ፣
ልብ አድርጉ፣ አንተ ስድ፣ አንተ ወሽካታ የሚል የለመድነው የዘይነባ
ሰኢድ ድምጽ ነው፡፡ ጉፍታዋን ተከናንባ፤ እህል ከእንክርዳድ እየለየች፤
34 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፴፬
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
አይኖቿን ወደምንጫወትበት እየሰደደች፤ ዋልጌነታችንን በተግሳጽ
ትከረክማለች፡፡ የዘይነባን ‹‹አን›› ትርጉም ግን ጥቂት ከታገለችኝ
በኋላ ደረስኩባት ለካ ዘይነባ ‹‹ወሎዬ›› ናት፡፡ በተወለደችበት ቀዬ
አንተ ባለጌ ለማለት ‹‹ተ›› ፊደል የስሜታቸውን ድምጽ ትሰብር
ስለነበር ‹‹ተ›› ን እየገደፉ ‹‹አን ሌባ›› ማለትን ቀጠሉበት የሚል
የራሴ ድምዳሜ ላይ ደረስኩ፡፡

ምነው እሜቴ! ትለኛለች ከት/ቤት ስመጣ ከቤታችን ምሳ ባለመድረሱ


ከሷቤት ሂጄ ወጥ ለማስጨመር አንከርፍፌ የያዝኩትን ደረቅ እንጀራ
ወደ ሰሃኑ እያስጠጋችና እንደ ባለ መብት ከፊቷ የተገተርኩትን
እኔን እያየች፡፡ ድንች በስጋን ሳድግ ወይ ሳገባ የዘወትር ቀለቤ
አደርገዋለሁ የሚል ምኞት ያደረብኝ ብርሃኔ ያለስስት እንጀራዬ
ላይ ደፍታበት የጣቶቼ ግማሽ እና የከንፈሬን ክፈፍ በወዝ
ያራሰችበት ቀን የእርካታዬ መጠን ወደፊት ድንች በስጋ ከእቅዴ
ውስጥ እንዲገባ አስገደደው፡፡ ይህ ለአንድ አጋጣሚ የተሰራ ደግነት
ሳይሆን ባስፈለገኝ ጊዜ ሁሉ የብርሃኔ ቤት ቤቴ ነው፡፡

ፋጡማ መንሱር ከውቅሮ ከመጣች ከ40 ዓመት በላይ ሆኗታል፤ እጇ


መድሃኒት ነው፡፡ ወላጆቻችን እኛን ሀኪም ቤት ከመውሰድ ይልቅ
በእርሷ ባህላዊ የህክምና ዘዴ ተጠቅመው ከህመማችን ይገላግሉናል፡
ከሁሉ የሚገርመኝ አፍ መፍታት ላልቻለ ህጻን፣ ለጆሮ ደግፍ፣
ለቦሃ፣ ጸጉር አላበቅል ላለ ጭንቅላት የምታዛቸው መንፈሳዊ ምክርና
ከእጽዋትና ከስራስር የምታዘጋጃቸው መድሀኒቶች ውጤታማነት
ነው፡፡ ፋጡማ ለኔ በልዩ ስፍራ የማስቀምጣት በየምክንያቱ የምገልጻት
መጽሃፈ ምሳሌዬ ናት፡፡ ምክንያቱም እሷ ሰጥታ የማትጠግብ፣
ካዘነው ጋር የምታዝን፣ ፈጣሪን መፍራት በየእለት እንቅስቃሴዋ
የምትተገብር ሰው ናትና፡፡

በጥፋቶቻችን የምንገረፍባት “ዘነበች” የምትባል አለንጋ ነበራቸው


ጋሽ ዘሪሁን ጉዴ፡፡ የመንደሩ ህጻናት ከወላጆቻቸው ይልቅ የሚፈሩት

35 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፴፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
እርሳቸውን ነው፡፡ ህጻናቱ የመንደሩን መተዳደሪያ ደንብ ሳያጓድሉ
የመኖር ግዴታ አለባቸው፡፡ ትንሽ ቅብጠት ካሳየን ጋሽ ዘሪሁን
‹‹ፊልድ›› ሄደዋል ማለት ነው፡፡ ያም ቢሆን ጥፋታችንን ገልጠው
የሚያስለጠልጡን ወላጆቻችን ነበሩ፡፡ እኛም በርሳቸው በመገረፋችን
የምንቋጥረው የቂም ዶሴ አልነበረንም፡፡ የፍቅር ልምጭ እንደሆነ
የልጅነት ንጹህ ልባችን መስክሮልናል ባይ ነኝ፡፡ አንዳንዴ ባንዳችን
ጥፋት ሁላችንም ታጉረን የምንለጠለጥበት ምክንያት ግር ይለን
ነበር፡፡ ቆይተን አጥፊው እንዳያጠፋ የኛ ተግሳጽ ያስፈልግ እንደነበር
ገባን፡፡ ቸልተኝነት፣ ምናገባኝነት፣ እኔ የለሁበትም ማለት ለካ
ጥፋትን መተባበር ነው አልን፡፡ በጋራ እንዳንገረፍ ጥፋትን በጋራ
መከላከልን ለመድንበት፡፡ አሁን አሁን በቸልታ፣ በእኔ የለሁበትም
የሚጠፉ ጥፋቶችን ሳይ በጋሽ ዘሪሁን አለንጋ ማስለጥለጥ ነበር
የሚል ቁጭት ይይዘኛል፡፡

በበርበሬና ዘይት የታሸ የጤፍ እና የስንዴ ቅይጥ ዳቦ ቆሎ ጆሮ


ግንዳችንን እስኪያመን ከበላን ‹‹እታተይ›› ከወልድያ አምጥታልን
ነው፡፡ ክረምቱን ከእርሷ ቤት በራፍ ተቀምጠን ዳንቴል በመስራት
እንሽቀዳደማለን፡፡ ሰብሰብ ብለን ስንቀመጥ እየመጠኑ መሳቅን፣
ከንፈር ገጥሞ ማላመጥን፣ ጓደኛ አለማብዛትንና ንጽህና
መጠበቅን ደጋግማ በመናገሯ ይሰለቸን ነበር፡፡ በኋላ ላይ ተማረን
(«ረ»ትጠብቃለች) አስቴር ብለን የኮድ ስም ሰጠናት፡፡ ልክ ለምክር
ስትጠራን በሹክሹክታ በሉ አስቴር ሙዚቃዋን ልትከፍትብን ነው
ብለን እንሳሳቅ ነበር፡፡ እታቴ (የወርቅ ውሃ) ለኔ የክርስትና እናቴ
ለልጅ ፊት የማሳየት ልምድ ባይኖራትም እንኳ በልጅነት ምኞታችን
ድፍረት በካርቦን (ጉሎ) የተዘፈዘፈ ነጠላዋን ደብቀን በመልበሳችን
የማገር ስባሪ መዛብን እስክትረሳው አያቴ ሰፈር ከርሜያለሁ፡፡ ኦ--
--ጵ-----ላ----ስ! ተባብለን የሰቀለችውን ቋንጣ ቆርጥመን አለቀልን
ስንል ራርታልናለች፡፡ ሳል ሲያመኝ ኑግ፣ አጃ የምታፈላልኝ እርሷ
ናት፡፡
36 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፴፮
አማርኛ ፰ኛ ክፍል

• ተማሪዎች እስካሁን ካነበባችሁት ሀሳብ በመነሳት ጉርብትናን


በተመለከተ ምን ተረዳችሁ?

• በቀሪው የምንባቡ ክፍልስ ጉርብትናን በተመለከተ ምን የሚነሳ


ይመስላችኋል?

እኔ እንግዲህ የነኚህ ሰዎች ሰፈር ሰው ነኝ፡፡ ሰፈሬ ማንነቴ ነው፡፡ ይህ


ማንነቴ በመንፈስም ሆነ በአካል እንዲጠረቃ ጎረቤቶቼን የሰበሰበልኝ፤
በተዋጣ ፍቅር፣ በተዋጣ ምግብ፣ በተዋጣ ምርቃትና በተዋጣ ተግሳጽ
እንዳድግ የተመረጥኩ እድለኛ ሰው ነኝ፡፡ በነኚህ ሰዎች ምክንያት
ህብረት፣ እኩልነትንና እኛነትን ተምሬያለሁ፡፡ ሰብዓዊነትን፣
ኢትዮጵያዊነትንና የአስተሳሰብ ልህቀትን ቀስሜበታለሁ፡፡ ለኔ የሀገር
ትርጉም ከዚህ በላይም አይደለም፡፡ እኔነቴ በእያንዳንዳቸው ቋንቋ፣
በእያንዳንዳቸው ባህል፣ በእያንዳንዳቸው ሀይማኖት ተገጥግጧል፡፡

በተረፈ ከዛጉ ጣሪያዎች ስር አዕላፋትን የሚገነቡ ንጹህ ልቦች እንዳሉ


ምስክር ነኝ፡፡ አሳሳች ሀሳቦችን የምንመክትበት ጥሩር ላሥታጠቁን
ጎረቤቶቻችን ወሰንየለሽ ክብር አለኝ፡፡ እኔና እኩዮቼ በተለያዬ
የከተማና አለማት ተበትነናል፤ ነገር ግን ውላችንን እንዳንስት ወደኛ
የሚወነጨፉትን አፍራሽ አመለካከቶች ለማክሰም ቃል አለን፡፡
(ምስራቅ ተረፈ፣ 2009፣ ጨው በረንዳ ለማስተማሪያነት

እንዲያገለግል ተሻሽሎ የቀረበ)

አንብቦ መረዳት

ተግባር አንድ፡-

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች መካከል በምንባቡ


መሰረት ተስማሚውን መልስ ምረጡ፡፡

37 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፴፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፩. በትረካው የተገለጸችው ዘይነባ ሰኢድ ‹‹አንተ›› ለማለት ‹‹አን››
የምትለው ለምንድን ነው?
ሀ. በተፈጥሮዋ ኮልታፋ ስለነበረች

ለ. ‹‹ተ›› ፊደል የስሜቷን ድምጽ ትሰብር ስለነበር

ሐ. በአማርኛ ቋንቋ መነጋር ስለሚከብዳት

መ. መልስ አልተሰጠም

፪. በምንባቡ ውስጥ የተጠቀሰችው ፋጡማ መንሱር ምን አይነት


ልዩ ችሎታ ነበራት?
ሀ. ሰውን ማስተናገድ ሐ. ድንች በስጋ ወጥ መስራት

ለ. ባህላዊ መድሃኒት መቀመም መ. ሀ እና ለ መልስ ናቸው

፫. የጋሽ ዘሪሁን ጉዴ አለንጋ ምን ተብላ ትጠራለች?

ሀ. ዘነበች ለ. አስናቀች ሐ. አበበች መ. ዘረፈች

፬. ‹‹ባንዳችን ጥፋት ሁላችንም ታጉረን የምንለጠለጥበት ምክንያት


ግር ይለን ነበር›› ስትል ምን ማለቷ ነው?
ሀ. በወቅቱ ልጆችን ለማስተካከል ይሰጥ የነበረውን ፍትሀዊ
ያልሆነ ቅጣት ማመልከት ነው፡፡

ለ. ‹‹ምናገባኝነት›› እና ‹‹እኔ የለሁበትም›› ማለት ጥፋት


መሆኑን ማሳየቷ ነው፡፡

ሐ. ጎረቤቶቿ ልጆች እንዳይበላሹ ለማድረግ የሚጠቀሙበትን


ዘዴ ማመልከቷ ነው፡፡

መ. ለ ና ሐ መልስ ናቸው

38 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ


፴፰
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር ሁለት፡-

ከዚህ በታች ከምንባቡ ውሰጥ የወጡ አዳዲስ ቃላት ቀርበዋል፡፡


ቃላቱ በምንባቡ ውስጥ ባላቸው አገባብ መሰረት ፍቻቸውን ስጡ፡፡
ምሳሌ፡-
ዋልጌ፡- ባለጌ
ወሽካታ፡- ለፍላፊ
ሀ. ወግዱ ሠ. አንከርፍፌ

ለ. ትከረክማለች ረ. ክፈፍ

ሐ. ቦኣ ሰ. ኦጵላስ
መ. እየገደፉ

ተግባር ሶስት፡-

ከዚህ በታች ከምንባቡ የወጡ ቃላት በሰንጠረዥ ቀርበዋል፡፡ ከቀረቡት


ቃላት በመምረጥና ባዶ ቦታው ውስጥ በማስገባት ዓረፍተ ነገሩን
አሟልታችሁ ፃፉ፡፡

ጉፍታ ማገር ቀዬ የቂም ዶሴ ዋልጌ

ፊት ማሳየት ወሽካታ ልህቀት ጥሩር የምንለጠለጥበት

፩. አዛውንቶችን የማያከብር ልጅ በማህበረሰቡ_________ ተብሎ


ሊነቀፍ ይችላል፡፡
፪. ልጆች ሲያጠፉ በጎረቤቶቻቸው ቢገሰጹ________ አይቋጥሩም፡፡

፫. የዘምዘም__________ ሰማያዊ እና ለስላሳ ነው፡፡

፬. ብዙ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ከኖሩበት________ ሊሰደዱ


ይችላሉ፡፡
39 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፴፱
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፭. ያለ የሌለውን ነገር የሚለፈልፍ ሰው__________ ተብሎ
በሰዎች ሊገሰፅ ይችላል፡፡
፮. የአእምሮ___________ መኖር አካባቢንና ሀገርን ያሳድጋል፡፡

፯. ለልጅ____________ ልጅን ማቅበጥ ነው ብለው ያስባሉ፡፡

፰. ወታደሮቹ ወደ ጦር ሜዳ ሲሄዱ -------------ለበሱ፡፡


ክፍል አራት፡- ጽሕፈት

ቢጋር /አስተዋጽኦ/ መንደፍ


አንድ ድርሰት ከመፃፋችን በፊት በውስጡ ሊካተተ የሚችሉ ዋና
ዋና ነጥቦችን አካቶ የሚይዝ ቅርፅ ነው፡፡ በተጨማሪም የሃሳብ
ቅደም ተከተልን በቅድሚያ ለመወሰንና በወጉ ለማቀናበር ያግዛል፡፡
የቢጋር ጥቅሞች
• አላማን ግልጽ ለማድረግና ሀሳብን ከአላማ ጋር ለማዛመድ
ያግዛል፤
• ድርሰቱ ከመጻፉ በፊት የሀሳቡን ቅንጅት ለማየትና
ለማስተካከል ይጠቅማል፤
• መልዕክትን ለማስተላለፍ ራሱን የቻለ መሳሪያ በመሆን
ያገለግላል፤
• ጽሁፍ በሚጻፍበት ጊዜ ከዋናው ሀሳብ እንዳያፈነግጥ
ይረዳል፡፡

ምሳሌ ፡- ርዕስ፡- የጎዳና ሕይወት

ርዕሱ ሰፊ ስለሆነ መጥበብ ይኖርበታል፡፡


1. ለጎዳና ተዳዳሪነት የሚዳርጉ ምክንያቶች
1.1 ከመጥፎ ጓደኛ ጋር መወዳጀት
1.2 በአጉል ሱሶች ‘‘መጠመድ’’

40 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፵


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
1.2.1. ከሲጋራ
1.2.2. ከጫት
1.2.3. ከአልኮል መጠጥ

ተግባር አንድ፡-
«የሰብአዊ እሴቶች ጥቅም» በሚል ርዕስ ሶስት አንቀጽ ያለው

ድርሰት ለመጻፍ የሚያስችል ቢጋር አዘጋጁ፡፡

ተግባር ሁለት፡-
በተግባር አንድ ያዘጋጃችሁትን ቢጋር መሰረት አድርጋችሁ

ሶስት አንቀጽ ያለው ድርሰት ጻፉ

ተግባር ሶስት፡-
ጉርብትና የሚለውን ምንባብ ካነበባችሁት በኋላ ከአካባቢያችሁ
ማህበራዊ ትስስር ጋር በማነፃፀር አራት አንቀፅ ያለው ድርሰት

ፃፉ፡፡

ክፍል አምስት፡- ቃላት

ድርብ ቃላት
ድርብ ቃል ሁለት የተለያየ ትርጉም ያላቸው ቃላት በአንድ ላይ ሆነው
አንድ ለየት ያለ ትርጉም የሚያስገኙበት የቃላት ቅንጅት ነው፡፡ ድርብ
ቃል በሰረዝ ወይም ያለሰረዝ ቃላትን በማዋሀድ ሊፃፍ ይችላል፡፡
ምሳሌ፡- ዕኩለ ሌሊት

ቤተ-መዘክር

ተግባር አንድ፡-
በሚከተለው ሰንጠረዥ ውስጥ ያሉ ድርብ ቃላትን ተጠቅማችሁ
ከታች ያሉትን ዓረፍተ ነገሮች አሟልታችሁ ፃፉ፡፡
41 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፵፩
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
መቅረፀ-ድምፅ ሰላማዊ ሰልፍ አውራ-ጎዳና
ብርድ-ልብስ ቤተ-መንግስት ትምህርት ቤት
ብረት ምጣድ ሸክላ-ድስት አየር-መንገድ
፩. ኢትዮጵያውያን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ስላረካቸው -----------------
አካሄዱ፡፡
፪. አሜሪካ ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ------------------------------ይዞ
መግባት አይቻልም፡፡
፫. እናቴ ዶሮ ወጥ የምትሰራበት----------------------ገዛች፡፡

፬. ሀሴት የገብስ ቆሎ ለመቁላት ከጎረቤቷ--------------------ተዋሰች፡፡

፭. ፅዱ እና ውብ የሆነው የአንድነት ፓርክ መገኛ ቦታው------------


-------------ነው፡፡
፮. ከአዲስ አበባ ወደ አዋሳ የሚወስደው----------------------------------
በመፍረሱ እየተጠገነ ነው፡፡
፯. የኢትዮጵያ----------------------------------------ሰራተኞች ስራቸውን
በአግባቡ እየተወጡ ነው፡፡

ተግባር ሁለት፡-

በሚከተለው ሰንጠረዥ ውስጥ ያሉ ዉስብስብ ቃላትን ተጠቅማችሁ


ከታች ያሉትን ዓረፍተ ነገሮች አሟልታችሁ ፃፉ፡፡

ይፈጥርላቸዋል ተማሪዎቻቸው አገልግሎታቸውን


ይገነዘቡበታል ኑሯቸውን ከተከታተልናቸው
መልዕክቶችን እየጨፈጨፉ ምጣኔሀብታዊ

፩. የአንድ ሀገር----------------እድገት በዜጎች ኑሮ ላይ ለውጥ


ማምጣት ይኖርበታል፡፡
፪. ሰዎች ደኖችን--------------------የአካባቢ መራቆትን እንዲፈጠር

42 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፵፪


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ያደርጋሉ፡፡
፫. ደብዳቤ ----------------------------ለማስተላለፍ ያገለግላል፡፡

፬. ሰዎች ለሰዎች መልካም ነገሮችን ሲያደርጉ የህሊና እርካታ-----፡፡


፭. በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን------------------ ለማሻሻል
ሌት ተቀን በርካታ ስራዎችን ይሰራሉ፡፡
፮. አንዳንድ መስሪያ ቤቶች ------------------ለህዝብ ይፋ ያደርጋሉ፡፡

፯. መምህራን ለ--------------ሁልጊዜ አርአያ መሆን አለባቸው፡፡

፰. አረጋውያንን ትኩረት ሰጥተን ካዳመጥናቸው እና-------------------


ጠቃሚ ቁምነገሮችን ያስጨብጡናል፡፡

ክፍል ስድስት፡- ሰዋስው


ቁጥር

ስሞች ተቆጣሪና ኢ-ተቆጣሪ (የማይቆጠር) ተብለው በሁለት


ይከፈላሉ፡ ተቆጣሪ ስሞች ነጠላና ብዙ ተብለው እንደገና በሁለት
ይከፈላሉ፡፡ ነጠላ ቁጥር የሚባሉት በቁጥር አንድ ብቻ ወይም
አንድ ፍሬ ብቻ መሆኑን የሚያመለክቱ ስሞች ናቸው፡፡ ብዙ ቁጥር
የሚባሉት ደግሞ ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ነገሮችን ለመግለጽ
የምንጠቀምባቸው ስሞች ናቸው፡፡ ማንኛውም ስም የሆነ ቃል
ተቆጣሪ ነገሮችን የሚጠቁም ከሆነ የቁጥር ምዕላድ ይባላል፡፡
ምሳሌ፡- ነጠላ ቅጥያ ምዕላድ ቃል (ብዙ)
ልጅ -ኦች ልጆች

ተማሪ -ዎች ተማሪዎች

«-ኦች» እና «-ዎች» ብዛትን የሚገልፁ ጥገኛ ምዕላዶች ሲሆኑ


ነጠላነትን ለማመልከት ግን ምንም አይነት ምዕላድ አንጠቀምም፡
እነዚህ ምዕላዶች ምንም እንኳን ብዙ ቁጥር አመልካች ቢሆኑም
በአገባብ ግን ልዩነት አላቸው፡፡ «ኦች» ን የምንጠቀመው ምዕላዱን
43 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፵፫
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
የሚያስጠጋው ነጻ ምዕላድ የመጨረሻ ፊደል ሳድስ ሲሆን ነው፡፡
ከሳድስ ውጭ የሆኑ ፊደላት ካሉት ግን «-ዎች» የሚለውን ጥገኛ
ምዕላድ እንጠቀማለን፡፡

ከግዕዝ ወደ አማርኛ የገቡ ስሞች የግዕዙን የብዙ ቁጥር ምዕላድ


ያስከትላሉ፡፡ ግዕዝ ብዙ የቁጥር ምዕላዶች አሉት ከነዚህ አንዱ
-ኣት የሚለው ምዕላድ ነው፡፡ የሚከተለውን ለአብነት ተመልከቱ፡፡
ምሳሌ፡- ነጠላ ቅጥያ ምዕላድ ቃል(ብዙ)

ቀን -ኣት ቀናት

ተግበር አንድ፡
የሚከተሉትን ስሞች «-ኣት» የሚለውን ምዕላድ በመጨመር ወደ
ብዙ ቁጥር ለውጡ፡፡

ተራ ቁጥር ነጠላ ብዙ
፩ ዓመት
፪ ዲያቆን
፫ ወር
፬ ካህን
፭ ቃል
ተግባር ሁለት፡- የሚከተሉትን ምሳሌዎች መነሻ በማድረግ ከታች
የተደረደሩትን ነጠላ እና ብዙ ቁጥር አመልካች ስሞች ተጠቅማችሁ
ዓረፍተነገር ስሩ፡፡
ምሳሌ፡- ልጅ-ነጠላ
-የሁሴን ልጅ በስነ ምግባር የታነፀ ነው፡፡
ልጆች-ልጅ-ኦች
-የኛ ሰፈር ልጆች በትምህርታቸው ጎበዞች ናቸው፡፡
ሀ. ሴት ለ. ላም ሐ. ተማሪ መ. መምህር

ሴቶች ላሞች ተማሪዎች መምህራን


44 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፵፬
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ማጠቃለያ

በዚህ ምዕራፍ ጭውውት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ


ሰዎች እርስ በዕርስ የሚያካሂዱት ምልልስ መሆኑን አይተናል፡
በተጨማሪም ቢጋር አንድ ድርሰት ከመፃፋችን በፊት በውስጡ
ሊካተተ የሚችሉ ዋና ዋና ነጥቦችን አካቶ የሚይዝ ቅርፅ እንደሆነ
ተመልክተናል፡፡

የተለያየ ትርጉም ያላቸው ቃላት በአንድ ላይ ሆነው አንድ ለየት


ያለ ትርጉም የሚያስገኝበት የቃላት ቅንጅት ድርብ ቃል እንደሚባል
አይተናል፡፡ በመጨረሻም በቁጥር አንድ ብቻ ወይም አንድ ፍሬ
ብቻ መሆኑን የሚያመለክቱ ስሞች ነጠላ ቁጥር ሲባሉ፤ ሁለትና
ከዚያ በላይ የሆኑ ነገሮችን ለመግለፅ የምንጠቀምባቸው ስሞች ብዙ
ቁጥር እንደሚባሉ ተመልክተናል፡፡

የክለሳ ጥያቄዎች

ተግባር፡-

የሚከተሉትን ጥያቄዎች በትኩረት በማንበብ ትክክለኛውን መልስ


በክፍት ቦታዎች ላይ አስቀምጡ፡፡

፩. ሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ስሞች መካከል የሚካሄድ ኢ-መደበኛ


ውይይት----------------------------ይባላል፡፡
፪. የተለያየ ትርጉም ያላቸው ቃላት በአንድ ላይ በመጣመር ለየት
ያለ ትርጉም የሚያስገኙበት የቃላት ቅንጅት----------------ይባላል፡፡
፫. ተቆጣሪ ስሞች------------------እና--------------------ተብለው በሁለት
ይከፈላሉ፡፡
፬. -------------------------- ስሞች በቁጥር አንድ ብቻ ወይም አንድ
ፍሬ ብቻ መሆኑን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡

45 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፵፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፭. አንድ ድርሰት ለመፃፍ እንደ አቅጣጫ ጠቋሚ (ኮምፓስ)
የምንጠቀምበት መሳሪያ---------------------------------ይባላል፡፡
፮. የሚያስጠጋው ነፃ ምዕላድ የመጨረሻ ፊደል ሳድስ ሲሆን
የምንጠቀመው አብዥ ቅጥያ ምዕላድ-------------------- ነው፡፡

46 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፵፮


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ምዕራፍ አራት

አጭር ልቦለድ

ከምዕራፉ የሚጠበቁ ውጤቶች፣ ይህንን ምዕራፍ ተምራችሁ


ከጨረሳችሁ በኋላ፡-
 አዳምጣችሁ ተመሳሳይ ታሪክ ትናገራላችሁ፤
 የአጭር ልቦለድን ምንነት ታብራራላችሁ
 በጽሁፍ ውስጥ መሸጋገሪያ ቃላትን ትጠቀማላችሁ፤
 የአጭር ልቦለድ አላባውያንን ትዘረዝራላችሁ፡፡

47 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፵፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ክፍል አንድ፡- ማዳመጥ

የህይወት ቅዳጆች

ቅድመ ማዳመጥ

፩. በህይወታችሁ የማትረሱት አሳዛኝ ገጠመኝ ካለ እስኪ ለጓደኞችችሁ


ንገሯቸው?
፪. ‹‹የህይወት ቅዳጆች›› በሚል ርዕስ ስር ምን ምን ጉዳዮች የሚዳሰሱ
ይመስላችኋል?

አዳምጦ መረዳት

ያዳመጣችሁትን ጹሁፍ መሰረት በማድረግ የሚከተሉትን ጥያቄዎች


በመምረጥ መልሱ፡፡

1 በምንባብ ውስጥ እንባው አንዴ እየጠቆረና እየወፈረ፣ሌላጊዜ


እየቀጠነና ውሃ እየመሰለ ክረምት ከበጋ ግቢውን አቋርጦ
ይፈሳል የተባለው ምንድን ነው?
ሀ. የቧንቧ ውሃ ለ. የአካባው ወንዝ
ሐ. የመጸዳጃ ቤቱ ፍስሽ መ. የሚወርደው ጎርፍ

48 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፵፰


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
2 ሰለሞን የምን መርሃ ግብር ተማሪ ነው?
ሀ. የመጀመሪያ ዲግሪ ሐ. የሁለተኛ ዲግሪ
ለ. የሶስተኛ ዲግሪ መ. የዲፕሎማ ተማሪ

3 ወይኗ ‹‹መልሱንስ ጋሽ ሰለሞን›› ብላ የጠየቀችው ለምንድን ነው?
ሀ. ውሰጂው እንደሚላት ስላወቀች
ለ. በመልሱ የምትገዛው ነገር አሳስቧት
ሐ. መልሱ ብዙ ስለነበር እንዳይጠፋባት በመስጋት
መ. መልሱ አልተሠጠም

4 ሰለሞን የሚኖረው የት አካባቢ ነው?


ሀ. ፒያሳ መሃሙድ ሙዚቃ ቤት አጠገብ
ለ. ስድስት ኪሎ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ጀርባ
ሐ. አራት ኪሎ ከዳግማዊ ምኒሊክ ት/ቤት ፊት ለፊት
መ. ስድስት ኪሎ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ፊት ለፊት

ክፍል ሁለት፡- መናገር

የንግግር መመሪያ

በመድረክ ላይ የሚቀርብ ንግግር የመድረክ ንግግር ሲባል ፡


በሚከተሉት መመሪያዎች መሰረት ተዘጋጅቶ፤ ለመድረክም
ይቀርባል::

ሀ. የንግግር አዘገጃጀት

የንግግር ርዕስ መምረጥ



የንግግር ርዕስ መወሰን ወይም ማጥበብ

የንግግሩን ዓላማ በግልፅ መረዳት

49 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፵፱


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
የአድማጭን ማንነት መለየት

ንግግር በሚደረግበት ርዕስ ላይ ሰፋ ያለ መረጃ ማሰባሰብ

መረጃን የሚያመለክት ሀሳብ በአስተዋፅኦ መልክ

ማዘጋጀት
በመድረክ ላይ የሚቀርበውን ንግግር እንዴት እንደሚቀርብ

መለማመድ

ለ. የንግግር አቀራረብ

አድማጮችን በሚያረካ መንገድ ንግግር ማድረግ



ንግግር በማቅረብ ሂደት ውስጥ የአድማጮችን ሁኔታ

በመከታተልና የንግግሩ ሀሳብም ሆነ አቀራረብ ማራኪ
እንዲሆን ማድረግ
በንግግሩ ማቅረብ ሂደት መግቢያ እና ዝርዝር ሐሳብ

እንዴት ያለ አቀራረብ ሊኖረው እንደሚገባ አስታውሶ
መተግበር፡፡

ተግባር አንድ፡-

የአጭር ልቦለድ አላባውያን በተመለከተ አምስት አባላት ያለው ቡድን


በመመስረት መመሪያ እየተሰጣጣችሁ የቃል ንግግር አድርጉ፡፡

ተግባር ሁለት፡-

“እውቀት ለመለወጥ” በሚል ርዕስ በየተራ እየወጣችሁ ክፍል


ውስጥ የቃል ንግግር አድርጉ፡፡

ተግባር ሶስት፡-

ከዚህ ቀደም ካነበባችሁት ልቦለድ ታሪክ ወይም በሬዲዮና በቴሌቢዥን


ከሰማችሁት ትረካ ውስጥ የምታስታውሱትን በየተራ እየወጣችሁ
ለክፍል ጓደኞቻችሁ ተርኩላቸው፡፡

50 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ



አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል ሶስት፡- ንባብ
መምሰልና መሆን

ቅድመ ምንባብ

፩. የአጭር ልቦለድን ምንነት አብራሩ፡፡


፪. የልቦለድ አለባውያን የሚባሉት ምን ምን ይመስሏችኋል?
፫. ‹‹መምሰልና መሆን›› ከሚለው የምንባብ ርዕስ
በመነሳት ምንባቡ ስለምን የሚያወራ ይመስላችኋል?

መምሰልና መሆን
ዛሬ የሴቶች ቀን የሚከበርበት ማርች 8 ነው፡፡ በዕለቱና በሰሞኑ
ከራስ ጸጉር የበዙ ሴቶችን ስለማብቃትና ከጥቃት ስለመከላከል ብዙ
ብዙ ነገሮች ይባላሉ፡፡ ጓደኛዬ መቅደስ ከነዚህ መድረኮች በብዙዎቹ
እየተገኘች‹ ‹ሴትን ልጅ ለማብቃት ቁልፉ ነገር ትምህርት ነው፡

51 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፶፩


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ካልተማረች ምርጫ ታጣለች፤በኢኮኖሚ ጥገኛ ትሆናለች፡፡ ካልተማረች
ሁሌም እስረኛ ነች፡፡ ዕድል አግኝታ ራሷን እንድትለውጥ ማገዝ
ነው፡ ለዚህ ደግሞ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል፡፡››
በማለት ያማረና የተዋጣለት ንግግር ታደርጋለች፡፡ እንደተለመደው
ኮርቼባት ሳላበቃ ፕሮግራሙ አበቃና አዳራሹ በር ላይ ተገኛኘን፡፡

‹‹ተናገርሽው መቼም….! ደስ ይል ነበር›› አልኳት፡፡ አጥብቄ


ካቀፍኳትና ሞቅ አድርጌ ከሳምኳት በኋላ፡፡

‹‹አመሰግናለሁ፤ አመሰግናለሁ…. አወራሽ ነበር ግን መሮጥ


አለብኝ……›› አለችኝ ጥድፍ ጥድፍ እያለች፡፡

‹‹ምነው ከመሸ ወዴት ነው የሚያሮጥሽ?›› አልኳት ጥድፊያዋ


ተጋብቶብኝ እኔም እየፈጠንኩ፡፡

‹‹ገና ገብቼ እለፋለሁ …..እራት መስራት አለብኝ ……›› ፊቷ ቅጭም


አለ፡፡

‹‹ምነው ሰራተኛ የለሽም እንዴ….?››

‹‹የለኝም ባክሽ ኤዱ ….እነሱ መች ይቀመጣሉ…..? በናትሽ እስኪ


ከሰማሽ አፈላልጊልኝ….ስራ ውዬ ወደ ስራ …..መሞቴ ነው እኮ…..››
ሳቅ አልኩና ‹‹ውይ ጓደኛዬ ‹ድርብ ጭቆና› ገደለሽ አይደል?
…..ከሰማሁ እነግርሻለሁ›› ብያት ተለያየን፡፡

• እስካሁን ከቀረበው የአጭር ልቦለዱ ታሪክ ምን ተረዳችሁ?


• የዚህ አጭር ልቦለድ ታሪክ መጨረሻው ምን የሚሆን
ይመስላችኋል?

ከሶስት ቀን በኋላ ስራ ስለምትፈልግ ልጅ ስሰማ ፈጠን ብየ ደወልኩላት


ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ፣

‹‹ስሚ መቅዲ…. ሰው አላገኘሽም አይደል?›› አልኳት፡፡

52 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፶፪


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
‹‹ኧረ በጭራሽ ….በ´ናትሽ ኤደንዬ አገኘሽልኝ እንዴ…..? ጉጉቷ
ግልጽ ሆኖ ይሰማል፡፡

‹‹ አዎ……››

‹‹ምን አይነት?››

‹‹አነስ ያለች ልጅ ናት፡፡ ……ገና መምጣቷ ነው አሉ ከክፍለ ሀገር፤


…..ምስኪን …..ታማኝ ልጅ ናት፡፡

‹‹ወይኔ ታድዬ! ታማኝ ሰው እኮ ነው የቸገረን ዘንድሮ! መቼ ትመጣለች


ታዲያ?››

‹‹ነገ ወይ ከነገ ወዲያ፡፡ የዘመዷን ስልክ አህኑኑ ቴክስት


አደርግልሻለሁ….. እዛ ነው ያለችው ተብያለሁ፡፡››

‹‹ውይ ተመስገን ….! ምሳ አለብኝ የኔ ቅመም….. ሀይለኛ ምሳ ነው


የምጋብዝሽ፡፡››

‹‹ችግር የለውም…. በነገርሽ ላይ

‹‹ እ…..››

አቋርጣ ነው እንጂ ‹‹ሰባተኛ ክፍል ናት፡፡ ዘንድሮ ያው …..እዚህ


ስትመጣ ትማራለች፡፡ የቤተሰብ ችግር ምና ምን ነው እንጂ ጎበዝ
ተማሪ ናት አሉ፤ መሸኛ አምጥታ ለሚቀጥለው ትመዘገባለች፡፡ እድለኛ
ናት አንቺ ቤት ከገባች ብዙ ቦታ ልትደርስ ትችላለች፤ እሱን አስቤ
ነው እኔም ቶሎ የደወልኩልሽ›› አልኩኝ በተስፈኛ ድምጽ፡፡

‹‹እ……. ትማራለች?›› ከድምጽዋ የደነገጠች መሰለኝ፡፡

‹‹አዎ… ትማራለች……ትንሽ ልጅ እኮ ናት…. እንዳልኩሽ አቋርጣ


ነው….. ምነው?››

‹‹ኤጭ! በናትሽ እኔ መማር የምትፈልግ ሰራተኛ አልፈልግም፡፡


53 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፶፫
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
…..ሌላ …… ሌላ ….መማር የማትፈልግ ከሰማሽ ደውይልኝ በቃ
…..አሁን ስራ ቢዚ ነኝ ….. ቻው …..››

ከአስራ ሶስት አመታት ላለፈ ጊዜ በሴት ልጅ ትምህርት ዙሪያ ደከመኝ፣


ታከተኝ ሳትል ስትታትር የኖረችው የሴት ልጆች መብት ተሟጋች
ወዳጄ ……፣ ለስንብት እንኳን እድል ሳትሰጠኝ ስልኳን ጆሮዬ ላይ
ስትደረግመው ትዝ ያለኝ አንድ ነገር ብቻ ነው፣ ‹‹ማንኛዋንም ሴት
የትምህርት እድል አግኝታ ራሷን እንድትለውጥ ማገዝ ያስፈልጋል፡፡
ለዚህ ደግሞ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል፡፡›› ብላ በአደባባይ
የተናገረቸው፡፡ ወይ መምሰልና መሆን! ለካ መምሰል እንደ መሆን
ቀላል አይደለም፡፡

(ከህይወት እምሻው፣ ፍቅፋቂ፣ 2010 ለማስተማሪያነት ተሻሽሎ


የቀረበ)
አንብቦ መረዳት

ተግባር አንድ፡-

የሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ ‹‹እውነት›› ስህተት ከሆኑ


ደግሞ ‹‹ሐሰት›› በማለት ከመለሳችሁ በኋላ ምክንያታችሁን በአጭሩ
ግለፁ፡፡

፩. ‘‘ሴት ልጅን ማስተማር ህብረተሰብን ማስተማር’’ ነው፡፡


፪. ሴት ልጆችን ለማብቃት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡
፫. በምንባቡ ውስጥ መቅደስ የተባለችው ገጸባህሪ
የምታወራው እና የምትሰራው ነገር የተጣጣመ ነው፡፡
፬. በምንባቡ መሰረት ድርብ ጭቆና የሚለው ሀሳብ ባለታሪኳ
ያለባትን ጫና የሚገልጽ ነው፡፡
፭. ሰዎች የቤት ሰራተኞቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ
የለባቸውም፡፡

54 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፶፬


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፮. የቤተሰብ ችግር ለልጆች ትምህርት እንቅፋት ሊሆን
ይችላል፡፡
፯. በምንባቡ ውስጥ የተጠቀሱት ገጸባህሪያት ሶስት ናቸው፡፡

አጭር ልቦለድ

አጭር ልቦለድ ከልቦለድ ዘውጎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ከረጅም ልቦለድ


የሚለይበት የራሱ የሆኑ ባህሪያት አሉት፡፡ እነዚህ መሰረታዊ ባህሪያት
ቁጥብነት፣ ጥድፊያና ነጠላ ውጤት ናቸው፡፡

የልቦለድ ዓላባውያን፡- ሰባት አይነት የልቦለድ ዓላባውያን አሉ፡፡


እነሱም፡-

፩. ታሪክ፡- በጊዜ /በቦታ/ ቅደም ተከተል የተደረደሩ ሁነቶች ትረካ

ነው፡፡

፪. ገፀ ባህርይ፡- በልቦለድ ፅሁፍ ደራሲ ከልቡ አመንጭቶ የሚፈጥራቸው


የገሀዱ ዓለም ሰዎች ወኪሎች ናቸው፡፡

፫. መቼት፡- “መቼ” እና “የት” ከተሰኙ ሁለት ቃላት የተመሰረተ


ሲሆን የልቦለዱ ታሪክ የተፈፀመበትን ጊዜና ቦታ ይመለከታል፡፡
፬. ግጭት፡- አንዱ ገፀባህርይ ከሌላው ገፀባህርይ ጋር የሚፈጥረው
እሰጣ ገባ ነው፡፡

ዋና ዋና የግጭት አይነቶች የሚባሉት ሰው ከራሱ ጋር፣ ሰው


ከተፈጥሮ ጋር፣ ሰው ከሰው ጋር፣ ሰው ከማህበረሰብ ጋር እና ሰው
ከዓምላኩ ጋር የሚያደርጋቸው ግጭቶች ናቸው፡፡

55 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፶፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፭. ጭብጥ፡- በልቦለዱ ውስጥ ሊተላለፍ የተፈለገው መልዕክት
ወይም ፍሬ ነገር ነው፡፡
፮. ትልም (ሴራ)፡- በምክንያትና ውጤት የተሳሰሩ ሁነቶች ወይም
ድርጊቶች ቅደም ተከተል ነው፡፡

ምሳሌ፡- ውሻው ይጮሃል፤ህፃኑም ያለቅሳል፡፡----ታሪክ ሲሆን

-በውሻው መጮህ ምክንያት ህፃኑ ያለቅሳል፡፡ ይህ ትልም/

ሴራ/ ነው፡፡

፯. አንፃር፡- ደራሲው ታሪኩን የሚያቀርብበትን የትረካ አቅጣጫ

የሚመለከት ነው፡፡

-ታሪኩ የቀረበው በስንተኛ መደብ ነው? 1ኛ መደብ 3ኛ መደብ

ተግባር ሁለት፡-

ቀጥሎ የቀረቡትን ዓረፍተ ነገሮች ትክክል ከሆኑ “እውነት” ስህተት


ከሆኑ ደግሞ “ሐሰት” በማለት መልሱ፡፡

፩. በአንድ አጭር ልቦለድ የአንድን ሰው ገጠመኝ ፈጠራዊ በሆነ


መንገድ ማቅረብ ይቻላል፡፡
፪. የልቦለድ ገፀባህርያት የገሀዱ ዓለም ሰዎች ምስለኔዎች ናቸው፡፡
፫. አጭር ልቦለድ በባህሪው መጠነሰፊ በመሆኑ ደራሲው ከአንድ
በላይ ጭብጥ የማሳየት እድል ይኖረዋል፡፡
፬. የልቦለድ ታሪክ በመረጃ ሊረጋገጥ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
፭. ልቦለድ ተደራሲው እራሱን በታሪኩ ውስጥ እንዲፈትሽና ንቃተ
ህሌናውን እንዲያዳብር የሚያስችል ነው፡፡

56 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፶፮


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር ሶስት፡-

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን


በመምረጥ መልሱ፡፡

፩. ከሚከተሉት ውስጥ የአጭር ልቦለድ ባህርይ ያልሆነው የትኛው


ነው?

ሀ. ቁጥብነት ለ. እምቅነት

ሐ. ጥድፊያ መ. ነጠላ ውጤት

፪. ከአጭር ልቦለድ አላባውያን መካከል የልቦለዱ ታሪክ የተፈፀመበትን


ጊዜና ቦታ የሚያመለክተው አላባ የቱ ነው?

ሀ. ግጭት ለ. ሴራ

ሐ. መቼት መ. ጭብጥ

፫. ከሚከተሉት ዓረፍተነገሮች መካከል ስለአጭር ልቦለድ ትክክል


የሆነው የቱ ነው?

ሀ. የአጭር ልቦለድ ገፀባህርያት በታሪኩ ውስጥ በርካታ ግጭቶች


ይገጥሟቸዋል፡፡

ለ. የአጭር ልቦለድ ደራሲ የራሱን ፍልስፍና ዘርዘር አድርጎ


እንዲያቀርብ ያስችላል፡፡
ሐ. አጭር ልቦለድ የረጅም ልቦለድ አንድ ቅንጫቢ ሊሆን
ይችላል፡፡

መ. የአጭር ልቦለድ ጭብጥ ነጠላ ወይም አንድ ነው፡፡

57 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፶፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፬. ከሚከተሉት ውስጥ የምክንያትና ውጤትን ትስስር የሚያመለክተው

የልቦለድ አላባ የትኛው ነው?

ሀ. ታሪክ ለ. ግጭት ሐ. ትልም (ሴራ) መ. መቼት

፭. ከሚከተሉት ውስጥ ስለልቦለድ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. ድርሰት የመፃፍ ፍላጎት ያለው ሁሉ የሚፅፈው ነው፡፡

ለ. በመረጃ የተደገፈ እንዲሆን አይጠበቅም

ሐ. የዕለት ተዕለት ገጠመኝን መነሻ በማድረግ የሚቀርብ የፈጠራ

ፅሁፍ ነው፡፡

መ. ማስዋብ ወይም ማጋነንን ይፈልጋል፡፡

ተግባር አራት፡-

ለሚከተሉት ፈሊጣዊ አነጋገሮች ፍች ከተሰጡት አማራጮች መካከል


ትክክለኛውን መልስ ስጡ

58 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፶፰


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፩. ሀብቷ ቀና

ሀ. እድለኛ ሆነች ለ. ለጋብቻ ታጨች


ሐ. ሀብታም ሆነች መ. ገንዘብ አገኘች

፪. ጥራዝ ነጠቅ

ሀ. ግልብ እውቀት ያለው ለ. ብዙ ያልተማረ

ሐ. ጥልቅ ትምህርት የሌለው መ. ሁሉም

፫. የአዞ እንባ
ሀ. የለበጣ ሀዘን ለ. እውነተኛ ሀዘን

ሐ. መከፋት መ. ማልቀስ

፬. አይነ ልም

ሀ. ቆንጆ ለ. ምቀኛ

ሐ. ተንኮለኛ መ. የዋህ

፭. አገም ጠቀም
ሀ. ሁሉን መጥቀም ለ. ያዝ ለቀቅ

ሐ. ዓይን አፋር መ. ሄድ መጣ

ክፍል አራት፡- ጽሕፈት

መሸጋገሪያ፣ቃላት ሐረጋት

የሀሳብ ተመሳሳይነት ያላቸውን ዓረፍተ ነገሮችና አንቀፆች በማያያዝ


እንደድልድይ ሆኖ የሚያገለግል ቃል ወይም ሀረግ ነው፡፡ ከነዚህ
ቃላትና ሀረጋት መካከልም የተወሰኑት፡-

59 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፶፱


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ከዚህም በላይ፣ ብሎም፣ ከዚህም በተጨማሪ፣ እንደዚሁም፣ በተመሳሳይም፣
ስለሆነም፤ይሁን እንጅ፣ በተቃራኒው ግን፣ በአንፃሩም ወዘተ. ናቸው፡፡

ተግባር አንድ፡-

በሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ ያሉትን ክፍት ቦታዎች ከዚህ


በታች ከቀረቡት መሸጋገሪያ ቃላት ወይም ሀረጋት መካከል በመምረጥ
አሟልታችሁ ፃፉ፡፡

• ከዚህ በማያያዝ በመቀጠል ከዚህ ቀጥሎ

• እስከዚህ ድረስ በሌላ ጊዜ ወደፊት

፩. ተጋባዡ እንግዳ መፃህፍት የማንበብ ልምድን በሚመለከት ገለፃ

አደረጉ፤------------ስለሚያነቧቸው መፃህፍት በራስ አባባል

ማስታዎሻ መያዝ ጠቃሚ እንደሆነ ተናገሩ፡፡

፪. እስካሁን ያለው የንባብ ልምዳችን ብዙ የሚያኮራን ላይሆን

ይችላል፤-----------------------ግን አስፈላጊነቱን ስለተረዳን ጠንክረን

ልናሻሽለው እንችላለን፡፡

፫. የጤና ባለሙያው የኤች አይ ቪ ኤዲስን የመተላለፊያ መንገዶች

በሚመለከት ዋነኛ የሆኑትን በዝርዝር አቀረቡ፤--------------------

---- በዚህ ጉዳይ ላይም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስልጋቸውን ነጥቦች

ለይተው ገለፃ በመስጠት ንግግራቸውን ጨረሱ፡፡

፬. ሁሉም ኢትዮጵያዊ የየድርሻውን በተሰማራበት ተግባር ለሀገሩ

እደገት ማበርከት አለበት፤--------------------------------የተሰሩት

60 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፷


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ስራዎች በቂ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡

፭. አጭር ልቦለድን በሚመለከት የአላባውያኑን ምንነት ተምረናል፤-

-----------------------------መሸጋገሪያ ቃላትን ወይም ሀረጋትን

እንማራለን፡፡

ተግባር ሁለት፡-

መሸጋገሪያ ቃላትን በመጠቀም “ታሪኬ” በሚል ርዕስ ባለ አራት


አንቀፅ ተረኪ ድርሰት ፃፉና ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡላቸው፡፡

ክፍል አምስት፡- ቃላት

ያልተለመዱ ቃላት
በዕለት ከዕለት የቋንቋ አጠቃቀማችን ውስጥ የማንገለገልባቸው አዳዲስ
ወይም ኢ-ተዘውታሪ ቃላትን የሚመለከት ነው፡፡

ምሳሌ፡-

መረን--------ባለጌ፣ ስድ

ሌጣ---------ነጠላ፣ ብቸኛ

ሎጤ-------ቀላዋጭ

ተግባር፡-

በ “ሀ” ስር የቀረቡትን ኢ-ተዘውታሪ ቃላት በ “ለ” ስር ከቀረቡት


ፍችዎቻቸው ጋር አዛምዱ፡፡

61 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፷፩


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
“ሀ” “ለ”

፩. ለሆሳስ ሀ. የአበባ ወቅት

፪. ለበጣ ለ. ድርስ እርጉዝ

፫. ሙዋጥ ሐ. ጌሾ ያልበዛበት ለጋ ጠጅ

፬. ቆንዳላ መ. ድምፅ አላባ፣ ሹክሹክታ

፭. በተሀ ሠ. አዘጋጀ፣ አሰናዳ

፮. ወረግቡ ረ. ሹሩባ

፯ . ከወነ ሰ. የጆንያ መስፊያ መርፌ

ሸ. ፌዝ፣ ሹፈት፣ ቀልድ

ክፍል ስድስት፡- ሰዋስው


ሐረግ፡-
ከቃል የሰፋ ከዓረፍተ ነገር ያነሰ፤ ቃላት እርስ በዕርስ በስርዓት

በመቀናጀት የአንድ ዓረፍተነገር አካል ሆነው የሚፈጥሩት
መዋቅር ነው፡፡
አንድ ሀረግ ምን አይነት ሐረግ እንደሆነ የሚወሰነውም

በሀረጉ ውስጥ መሪ ሆኖ /ከሀረጉ በስተቀኝ/ የቀረበው ቃል
በሚመደብበት የቃል ክፍል ነው፡፡
ከመስተዋድዳዊ ሀረግ ውጭ የሁሉም ሀረጎች መሪያቸው ቀኝ

መሪ ነው፡፡
ሀረግ በዓይነቱ ስማዊ ሐረግ፣ ግሳዊ ሐረግ፣ ቅፅላዊ ሐረግ፣

ተውሳከ ግሳዊ ሐረግና መስተዋድዳዊ ሐረግ በመባል ይታወቃል፡
የሀረጉ መሪ ቃል፡-ስም ከሆነ ----ሐረጉ ስማዊ ሐረግ

-ግስ ከሆነ-------ሐረጉ ግሳዊ ሐረግ
-ቅፅል ከሆነ---- ሀረጉ ቅፅላዊ ሐረግ
62 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፷፪
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
-ተውሳከ ግስ ከሆነ-----ሀረጉ ተውሳከ ግሳዊ ሐረግ
-መስተዋድድ ከሆነ----ሀረጉ መስተዋድዳዊ ሐረግ
ይሆናል፡፡
ምሳሌ፡-የብር ቀለበት-----ሰማያዊ ሐርግ
-እጅግ በጣም ጎበዝ ------ቅፅላዊ ሐረግ
-በድንገት መጣ፡፡----ግሳዊ ሐረግ
-ልጁ ክፉኛ---------ተውሳከግሳዊ ሐረግ
 መስተዋድዳዊ ሀረግ ቀኝ መሪም ግራ መሪም መሆን
ይችላል፡፡
ምሳሌ፡- ወደ ቤት---መ.ሐ
-ከልጁ ጋር----መ.ሐ
ተግባር አንድ፡-
በሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ የተሰመረባቸውን ሐረጎች አይነት
በምሳሌው መሰረት ጥቀሱ፡፡
ምሳሌ፡-
ዘይነባ አክስቷን ለመጠየቅ ወደ ደሴ ሄደች፡፡
ወደ ደሴ-----------መስተዋድዳዊ ሐረግ

ሁሉን ነገር በሆዱ የሚይዝ ሰው እራሱን ይጎዳል፡፡
ሁሉን ነገር በሆዱ የሚይዝ ሰው---------ስማዊ ሐረግ

፩. ልጁ ወደሆስፒታል ተወሰደ፡፡
፪. ወይኒቱ በጣም ጎበዝ ተማሪ ናት፡፡
፫. የፈራረሱ ቤቶች በአዲስ መልክ እንደገና ተሰሩ፡፡
፬. ትናንት የታመመው ተማሪ ተሻለው፡፡
፭. ሄኖክ የእግር ኳስ ለመመልከት ስቴድየም ገባ፡፡

ተግባር ሁለት፡-

የተለያዩ የሀረግ አይነቶቸን ተጠቅማችሁ አምስት አረፍተ ነገር


መስርቱ፡፡

63 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፷፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ማጠቃለያ

በዚህ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ቃላት፣ሀረጋት የሀሳብ ተመሳሳይነት


ያላቸውን ዓረፍተ ነገሮችና አንቀፆች በማያያዝ እንደድልድይ ሆኖ
የሚያገለግል ቃል ወይም ሀረግ እንደሆነ አይተናል፡፡

ያልተለመዱ ቃላት በዕለት ከዕለት የቋንቋ አጠቃቀማችን ውስጥ


የማንገለገልባቸው አዳዲስ ወይም ኢ-ተዘውታሪ ቃላት መሆናቸውን
ተረድተናል፡፡ በመጨረሻም ሐረግ ከቃል የሰፋ ከዓረፍተ ነገር ያነሰ፤
ቃላት እርስ በዕርስ በስርዓት በመቀናጀት የአንድ ዓረፍተነገር አካል
ሆነው የሚፈጥሩት መዋቅር መሆኑን ተመልክተናል፡፡

የክለሳ ጥያቄዎች
ተግባር አንድ፡-
የሚከተሉትን ሀረጋት የሀረግ አይነት ለዩ፡፡
፩. የወርቅ ቀለበት
፪. ወንድሙ ክፉኛ
፫. ከእህቷ ጋር
፬. በጣም ቆንጆ
፭. ትምህርት ቤት መጣ፡፡
ተግባር ሁለት፡-
ለሚከተሉት ኢ-ተዘውታሪ ቃላት መዝገበቃላዊ ፍች ስጡ፡፡
፩. ህዳግ
፪. ሀኬት
፫. ሙዳ
፬. ህፀፅ
፭. መግነጢስ

64 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፷፬


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ምዕራፍ አምስት

ሥነ ሕዝብ
ከዚህ ትምህርት የሚጠበቅ ውጤት፣ ይህንን ምዕራፍ ተምራችሁ
ከጨረሳችሁ በኋላ፡-

በአትኩሮት አዳምጣችሁ ጽሁፉን ትገልጻላችሁ፤



ስለ ህዝብ ብዛት ምንነት ታብራራላችሁ፤

የህዝብ ብዛት በኢኮኖሚ ላይ የሚሳድረውን ተጽዕኖ

ትተነትናላችሁ፤
ተራኪ ጽሁፍ ትጽፋላችሁ፡፡

65 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፷፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል አንድ፡- ማዳመጥ

የህዝብ ቁጥር መጨመር እንደ መልካም አጋጣሚ

ቅድመ ማዳመጥ

፩. የህዝብ ብዛት መኖር ለአንድ ሀገር ምን ምን ጠቀሜታ ያለው


ይመስላችኋል?
፪. የህዝብ ብዛትና የሀገር ሀብት ተመጣጣኝ ካልሆነ በሀገር ላይ ምን
ጉዳት የሚያስከትል ይመስላችኋል?
፫. ርዕሱንና ስዕሉን ተመልክታችሁ ምን ምን ጉዳዮች ይነሳሉ
ብላችሁ ትገምታላችሁ?

አዳምጦ መረዳት

ተግባር አንድ፡-

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ባዳመጣችሁት ምንባብ መሰረት ትክክለኛ


መልስ ስጡ፡፡

66 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፷፮


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፩. የውጭ አገር ኩባንያዎችና የተለያዩ ሀገራት ባለሀብቶች መዋዕለ
ንዋያቸውን በኢትዮጵያ ለማፍሰስ ፍላጎት እያሳዩ ያለው ለምንድን
ነው?
፪. ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ ምን ምን ነገሮች ሊከሰቱ
ይችላሉ?
፫. የህዝብ ቁጥር መጨመር እንደመርገም ሳይሆን እንደበረከት
ሊቆጠር የሚችለው መቼ ነው?
፬. ለድህነት መባባስ በምክንያትነት የተጠቀሰው ምንድን ነው?

፭. የህዝብ ቁጥር እንዳይጨምር ከመስራት ይልቅ ምን ላይ ቢሰራ


የተሻለ ይመስላችኋል?
ተግባር ሁለት፡-

ለሚከተሉት ከምንባቡ የወጡ ቃላት መዝገበቃላዊ ፍች ስጡ፡፡

ሀ. መነመነ

ለ. ደለደለ

ሐ. በረከት

መ. ኮተኮተ

ሠ. ትኩረት

ክፍል ሁለት፡- መናገር

ምክንያትና ውጤት
የአንድ ነገር ውጤት ከእሱ በፊት በሚኖር ምክንያት ወይም መንስኤ
ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ አንድ ምክንያት ብዙ ውጤት ሊያስመዘግብ
ይችላል፡፡ ብዙ ምክንያቶቹም እንዲሁ አንድ ውጤት ሊያስመዘግቡ

67 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፷፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ይችላሉ፡፡

ምሳሌ፡- የሜላት አባት መጠጥ እየጠጡ ከዕናቷ ጋር ተጣልተዋል፡፡


ሜላትም በቤተሰቦቿ ፀብ ተበሳጭታ ትምህርቷን ሳታጠና ስለቀረች
ፈተናውን ወደቀች፡፡

ምክንያት ውጤት

 የሜላት አባት መጠጥ መጠጣት -የባልና የሚስት ፀብ


የባልና ሚስት ፀብ
 -የሜላት መበሳጨት
የሜላት መበሳጨት
 -ትምህርቷን አለማጥናት
የሜላት አለማጥናት
 -ፈተና መውደቅ

ተግባር፡-

በሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ በመንስኤና ውጤት የተገለፁ


ሀሳቦችን እየለያችሁ በቃል አስረዱ፡፡

፩. ቋንቋ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ተናጋሪ ሲያጣ እሱም አብሮ


ይጠፋል፡፡
፪. የሀይል እጥረት ለደኖች መመናመን ዋነኛ መንስኤ እየሆነ ነው፡፡

፫. ቅድስት እናቷ ስለታመሙ አዘነች፡፡

፬. የደኖች መጨፍጨፍ የአየር ንብረት መዛባትን አስከትሏል፡፡

፭. ሳሙኤል ጠንክሮ በማጥናቱ አንደኛ ወጣ፡፡

68 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፷፰


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል ሶስት፡- ንባብ

የኢትዮጵያ የሥነ- ሕዝብ ፖሊሲ

ቅድመ ንባብ

፩. የሥነሕዝብ ፖሊሲ ማለት ምን ማለት ነው? ለምን


የሚያስፈልግ ይመስላችኋል?

፪. የህዝብ ብዛታቸውን ለልማት የተጠቀሙ ሀገራትን ጥቀሱ?

፫. የህዝብ ብዛት በኢኮኖሚ ላይ ምን አይነት ተፅእኖ የሚያሳድር


ይመስላችኋል?
፬. የቀረበውን ስዕል ተመለክታችሁ የተረዳችሁትን ግለፁ፡፡

69 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፷፱


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
የኢትዮጵያ የሥነ- ሕዝብ ፖሊሲ

በአገራችን ለሚታዩ ውስብስብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አንዱ


ምክንያት ከኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገታችን ጋር ያልተመጣጠነ
ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገት መኖር እንደሆነ ይታመናል፡፡ ለዚህ
ደግሞ ዋነኛው መንስኤ ከፍተኛ የውልደት ምጣኔ መኖር ነው፡፡
ይህንን በመረዳት የኢትዮጵያ መንግስት በ1985 ዓ.ም የሥነሕዝብ
ፖሊሲ አውጥቶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የዚህ ፖሊሲ አጠቃላይ ዓላማ የሕዝብ ቁጥር እድገትና የኢኮኖሚ


ልማት እድገትን በማጣጣም በአገሪቱ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው
ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል ነው፡፡ ይህም ተግባራዊ የሚሆነው
በሕዝቡ ሙሉ ፈቃደኝነትና ተሳትፎ ላይ በመመስረት ከፍተኛ
የሆነውን የወሊድ መጠን ደረጃ በደረጃ በመቀነስ እና አዝጋሚ
የሆኑትን የኢኮኖሚና ማህበራዊ የልማት ዘርፎችን ደግሞ አቅም
በፈቀደ መጠን በፍጥነት በማሳደግ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ የሥነ
ህዝብ ፖሊሲ አብይ ግብ “የሕዝብ ቁጥር እድገት ምጣኔን ከሀገሪቱ
ኢኮኖሚያዊ ልማትና ከተፈጥሮ ሀበት አጠቃቀም ጋር እንዲጣጣም
በማድረግ ከረጅም ጊዜ አኳያ የህዝቡ የኑሮ ደረጃና አጠቃላይ
ደህንነት እንዲሻሻል ማድረግ ነው፡፡”

የኢትዮጵያ የስነሕዝብ ፖሊሲ አጠቃላይ አላማዎችም፡- የኢኮኖሚ


ግንባታውን በማጠናከርና የህዝብ ቁጥር እድገት ምጣኔን በዕቅድ
በመቀነስ በሕዝብ ቁጥር እድገትና በዝቅተኛ ኢኮኖሚ መካከል
ያለውን ልዩነት ማስወገድ፤ በተቀናጁ የልማት ፕሮግራሞች
አማካኝነት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ማስፋፋትና የስራ እድል
እንዲፈጠር ማድረግ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን ማፋጠን፤
ከገጠር ወደከተማ የሚደረገውን የሕዝብ ፍልሰት መጠን መቀነስ፤
የአካባቢ ጥበቃንና እንክብካቤን የሚያጠናክሩ ተገቢ እርምጃዎችን

70 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ



አማርኛ ፰ኛ ክፍል
በመውሰድ በተለይ የገጠሩ አካባቢ ሰዎችን የማኖር አቅም እንዲጠበቅ
ወይም እንዲሻሻል ማድረግ፤ ሴቶችን ከባህላዊ ተፅዕኖዎች፣ ከከባድና
አሰልች ስራዎች በማላቀቅና ማህበረሰቡ ውስጥ ምርታማ ሆነው
እንዲሳተፉ በማድረግ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ደረጃቸውን ከፍ
ማድረግ፤ በቀላሉ በአደጋ ሊጠቁ የሚችሉትን ማለትም የህፃናትን፣
የወጣቶችን፣ የሴቶችንና የአረጋውያንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ
ሁኔታዎች ማሻሻል ናቸው፡፡ እነዚህን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ
የሕዝብ ልማት ወይም ማሕበረ ኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ ነው፡፡
በዕውቀት፣ በአመለካከትና በክህሎት አቅሙ የጎለበተ ሕዝብ ለአገር
እድገት ወሳኝ ግብዓት ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ አቅሙ ያልጎለበተ
ሕዝብ የልማት ፈተና መሆኑ እሙን ነው፡፡

 የስነሕዝብ ፖሊሲ ዓላማዎች ተብለው የተገለፁት ምን ምን


ናቸው?
የሀገር ልማት ሲታሰብ ምን ምን ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ

የሚያስፈልግ ይመስላችኋል?

በመሆኑም ልማት ሲታሰብ ቅድሚያ የሕዝቡን አሰፋፈር ሁኔታ


ማለትም ብዛቱን፣ ዓመታዊ የዕድገት ምጣኔውን፣ መልክዓ ምድራዊ
ስርጭቱን እና የፆታና የዕድሜ ስብጥሩን እንዲሁም የውልደት፣
የሞትና የፍልሰት ምጣኔውን በሚገባ ማጤንና ከማህበራዊ፣
ከኢኮኖሚያዊ እና ከአካባቢያዊ ጉዳዮች ጋር ያላቸውን ትስስር
መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የስነሕዝብ ሁኔታዎችን
ከግምት ውስጥ ያላስገቡ የልማት እንቅስቃሴዎች ዘላቂና አስተማማኝ
ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በአንድ አገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት
ስልቶች ውስጥ የስነሕዝብ ጉዳዮችን ማካተት ዘላቂ ልማትን
ለማምጣትና ድህነትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ወሳኝ መሆኑን
ያሳያል፡ የኢትዮጵያ መንግስት በስነሕዝብና ልማት መካከል ያለውን
ትስስር ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የስነሕዝብ ፖሊሲ አውጥቶ
71 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፸፩
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
በስራ ላይ እንዲውል አድርጓል፡፡ የሥነ-ሕዝብ ጉዳዮች ተግባራት
ደግሞ ዘርፈ ብዙ በመሆናቸው በአንድ በተወሰነ ተቋም ጥረት ብቻ
የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት የሚቻል አይደለም፡ በመሆኑም
ሌሎች ተቋማትና ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ እና በተጠናከረ መልኩ
የስነሕዝብ ጉዳዮችን በየእቅዶቻቸው እንዲያካትቱ ተደርጎ መስራት
ይገባል፡፡

(ከአብክመ ፕላን ኮሚሽን የሥነ ሕዝብና ልማት ቅንጅት ዳይሬክቶሬት፤


ታህሳስ 2012 ዓ.ም፤ ለማስተማሪያነት ተሻሽሎ የቀረበ)

አንብቦ መረዳት

ተግባር አንድ፡-

የሚከተሉትን ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት ትክክል ከሆኑ


“እውነት” ስህተት ከሆኑ ደግሞ“ሐሰት” በማለት መልሱ፡፡

፩. የሀገራችን የህዝብ ቁጥር እድገት ከኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ


እድገታችን ጋር የተጣጣመ ነው፡፡
፪. ከኢትዮጵያ የስነ ህዝብ ፖሊሲ ዓላማዎች ውስጥ አንዱ ከገጠር
ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት መቀነስ ነው፡፡
፫. ከፍተኛ የሆነ የወሊድ መጠን መጨመር ለህዝብ ቁጥር እድገት
ምንም አስተዋፅኦ የለውም፡፡
፬. ልማት ሲታሰብ የህዝብን ዲሞግራፊያዊ ባህርያት በሚገባ ማጤን
ያስፈልጋል፡፡
፭. የስነሕዝብ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገቡ የልማት
እንቅስቃሴዎች ዘላቂ እና አስተማማኝ ሊሆኑ አይችሉም፡፡
ተግባር ሁለት፡-

ምንባቡን መሰረት በማድረግ ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጡት


አማራጮች መካከል ትክክለኛውን በመምረጥ ጻፍ፡፡
72 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፸፪
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፩. በምንባቡ አንቀፅ ሁለት ላይ በአገራችን ለሚታዩ ውስብስብ
ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት ተብሎ የተጠቀሰው
ምንድን ነው?
ሀ. የህዝብ ቁጥር እድገት ለ. የልማት ፖሊሲ

ሐ. የውልደት ምጣኔ መ. የሀብት ብክነት

፪. በምንባቡ መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣው ፖሊሲ የትኛው


ነው?
ሀ. የትምህርት ፖሊሲ ለ. የጤና ፖሊሲ

ሐ. የሥነሕዝብ ፖሊሲ መ. የግብርና ፖሊሲ

፫. የኢትዮጵያ የስነሕዝብ 70 በመቶ ወጣትና ሠርቶ ያልደከመ


መሆኑ የተገለፀው መየትኛው አንቀፅ ነው?
ሀ. በአንቀፅ አንድ ለ. በአንቀፅ ሁለት
ሐ. በአንቀፅ አራት መ. በአንቀፅ ሶስት

፬. በአንቀፅ ሶስት ላይ የአገር እድገት ወሳኝ ግብዓት ይሆናል


ተብሎ የተገለፀው በምን የጎለበተ ህዝብ ነው?
ሀ. በዕውቀት ለ. በአመለካከት ሐ. በክህሎት መ. ሁሉም

፭. ዘላቂ እና አስተማማኝ ሊሆን አይችም የተባለው ምንን ከግምት


ያላስገባ የሥነሕዝብ ሁኔታ ነው።
ሀ. ጥረት ለ. ውልደት ሐ. ልማት መ. ብዛት
ተግባር ሶስት፡-

በምሳሌው መሰረት ከምንባቡ የምክንያትና ውጤት ትስስር ያላቸውን


አምስት ዓረፍተ ነገሮች አውጥታችሁ አመልክቱ፡፡

73 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፸፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ምሳሌ፡- ያልተጣጣመ ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገት መኖር ምክንያቱ
ከፍተኛ የውልደት ምጣኔ ነው፡፡
ምክንያት፡- ያልተጣጣመ ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገት
ውጤት፡- ከፍተኛ የውልደት ምጣኔ

ክፍል ሶስት፡- ጽሕፈት

ተራኪ ድርሰት

በጣም ከተለመዱት አራት ዋና ዋና የድርሰት አይነቶች ውስጥ


አንዱ ሲሆን በጊዜ ቅደም ተከተል ስላለፈ ድርጊት የሚተረክ ወይም
የሚያትት ጹሁፍ ተራኪ ድርሰት ተብሎ ይጠራል፡፡ ተራኪ ድርሰት
የሁነቶችን የድርጊት ቅደም ተከተል ጠብቆ እንዲህ ሆነ፣ እንዲህ
ተደረገ---እያለ የሚተርክ ጹሁፍ ነው፡፡ ታሪኩን የሚነግረን እራሱ
የድርጊቱ ተካፋይ ወይም ተመልካች ሊሆን ይችላል፡፡

ምሳሌ፡- አቶ ፍቅር ከአባታቸው ከአቶ ይበልጣል አጥናፉ እና


ከእናታቸው ከወ/ሮ ማህደር በላይ አዲስ አበባ ከተማ ታህሳስ
12/1984 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለአቅመ ትምህርት ሲደርስ
በአካባቢያቸው ከሚገኘው እውቀት ፋና አንደኛ ደረጃ ትምህርት
ቤት ገብተው ትምህርታቸውን ተከታታሉ፡፡ ከዚያም የሁለተኛ
ደረጃ ትምህርታቸውን በፍኖተ ጥበብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤት ተምረዋል፡፡
ተግባር አንድ፡-
የአንድን የምታውቁት ታዋቂ ሰው የሕይወት ታሪክ በአምስት
አንቀፅ ፃፉ፡፡

ተግባር ሁለት፡-

የራሳችሁን የሕይወት ታሪክ በሶስት አንቀፅ በመፃፍ ለክፍል


ጓደኞቻችሁ አንብቡላቸው፡፡
74 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፸፬
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል አራት፡- ቃላት

የቃላት እማሬያዊና ፍካሬያዊ ፍች


አንዳንድ የአማርኛ ቃላት እማሬያዊና ፍካሬያዊ ፍች አላቸው፡፡

እማሬያዊ ፍች፡--የቃላት ቀጥተኛ ወይም መዝገበ ቃላዊ ፍች



ነው፡፡
• የቃላት የተለመደ ወይም የተዘወተረ ትርጉም
ነው፡፡

• ቃላቱ ሲነገሩ ወደ አዕምሯችን በፍጥነት


የሚመጣውፍች ነው፡፡
ፍካሬያዊ ፍች፡---ከእማሬያዊ ፍቺ በተደራቢነት የምናገኘው

ፍቺ ነው፡፡
• ከቀጥተኛ ፍችው ባሻገር የምናገኘው ትርጉም
ነው፡፡
• የቃላት ድብቅ ወይም ስውር ፍች ነው፡፡

ምሳሌ፡- ቤት

እማሬያዊ ፍች ---ጣራና ግድግዳ ያለው የሰው ልጅ መኖሪያ



ፍካሬያዊ ፍች---ትዳር፣ የሰው ልጅ ጠቅላላ ኑሮ

75 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፸፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር፡-

የሚከተሉትን ቃላት እማሬያዊና ፍካሬያዊ ፍች በሰንጠረዡ ውስጥ


በቀረበው ምሳሌ መሰረት አስቀምጡ፡፡

ቃል እማሬያዊ ፍች ፍካሬያዊ ፍች

ንብ ማር አምራች በራሪ ፍጡር ታታሪ፣ ትጉህ፣ ሰራተኛ

ዱባ

ቋንጣ

አንበሳ

ተልባ

እንጀራ

ክፍል ስድስት፡- ሰዋስው


ገቢርና ተገብሮ ግሶች

ገቢር ግሶች፡- አንድ ሰው የሚፈፅመውን ድርጊት ወይም ተግባር


የሚገልፁ ናቸው፡፡ አምዱ ምንም አይነት ቅጥያ የማይጨመርበት
ሲሆን የተፈፀመ ድርጊትን የሚጠቁም በመሆኑ ሃላፊ አምድ ነው::

76 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፸፮


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ምሳሌ፡- ነገረ፣ ሰበረ፣ በጠሰ፣ ለወጠ፣ ቀደደ ወዘተ.

 በእምነት መስኮት ሰበረ፡፡


 ሰፊው ልብስ ቀደደ፡፡
 በጉ የታሰረበትን ገመድ በጠሰ፡፡
ተገብሮ ግሶች፡- የእርስ በርስ ድርጊትን የሚያመለክት ሲሆን ገቢር
አምድ ላይ በምትቀጠል (ተ-) ምዕላድ የሚፈጠር አምድ ነው፡ አምዱ
አንድ የተፈፀመ ድርጊት የተፈፀመበትን ነገር የሚጠቁም ነው::
ምሳሌ፡- ተነገረ፣ ተሰበረ፣ ተበጠሰ፣ ተለወጠ፣ ተቀደደ ወዘተ.

መስኮቱ በኤፍሬም ተሰበረ፡፡



ገመዱ በበጉ ተበጠሰ፡፡

ልብሱ በሰፊው ተቀደደ፡፡

ተግባር፡-

የሚከተሉትን ቃላት ተጠቅማችሁ ገቢርና ተገብሮ ዓረፍተ ነገር


ስሩ፡፡

፩. ገደለ ፬. ጠበሰ

ተገደለ ተጠበሰ

፪. ወደደ ፭. ጨረሰ

ተወደደ ተጨረሰ

፫. ለበሰ ፮. ቀመሰ

ተለበሰ ተቀመሰ

77 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፸፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ማጠቃለያ
በዚህ ምዕራፍ ስላለፈ ድርጊት የሚተርክ ወይም የሚያትት ፅሁፍ
ተራኪ ድርሰት ተብሎ እንደሚጠራ አይተናል፡፡ በተጨማሪም የቃላት
እማሬያዊ ፍች ማለት የቃላት የተለመደ ወይም የተዘወተረ ትርጉም
እንደሆነና ፍካሬያዊ ፍች ማለት ደግሞ የቃላት ድብቅ ወይም ስውር
ፍች መሆኑን ተረድተናል፡፡

በመጨረሻም ገቢር ግሶች አንድ ሰው የሚፈፅመውን ድርጊት ወይም


ተግባር የሚገልፁ ሲሆኑ፤ ተገብሮ ግሶች ደግሞ ገቢር አምድ
ላይ በምትቀጠል (ተ-) ምዕላድ የሚፈጠር አምድ መሆናቸውን
ተመልክተናል፡፡

የክለሳ ጥያቄዎች
ተግባር አንድ፡-

የሚከተሉትን ዓረፍተነገሮች ገቢርና ተገብሮ ዓረፍተነገር እያላችሁ


ለዩ፡፡

፩. አቤል አበባ ተከለ፡፡

፪. አበባው በአቤል ተተከለ፡፡

፫. ሔኖክ እስክርቢቶ ደበቀ፡፡

፬. እስክርቢቶው በሔኖክ ተደበቀ፡፡

78 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፸፰


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር ሁለት፡-

የሚከተሉትን ግሶች ተጠቅማችሁ ገቢርና ተገብሮ ዓረፍተነገሮችን


ስሩ፡፡

፩. ደረበ

፪. ተደረበ

፫. ከፈለ

፬. ተከፈለ

ተግባር ሶስት፡

ለሚከተሉት ቃላት እማሬያዊና ፍካሬያዊ ፍች ስጡ፡፡

፩. ፍየል

፪. ቆቅ

፫. በግ

79 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፸፱


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ምዕራፍ ስድስት

በርሃማነት

ከምዕራፉ የሚጠበቁ ውጤቶች፣ ይህንን ምዕራፍ ተምራችሁ


ከጨረሳችሁ በኋላ፡-
• አዳምጣችሁ እየተነተናችሁ ትመዝናላችሁ፤
• የበርሃማነትን ምንነት ትገልፃላችሁ፤
• በርሃማነት የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ታብራራላችሁ፤
• የተሰጣችሁን ጽሁፍ በማንበብ ማጠቃለያ ትሰጣላችሁ፤

80 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ



አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል አንድ፡- ማዳመጥ
የምድራችን ጀግና

(ዶ/ር ተወልደብርሀን ገ/እግዜአብሔር)

ቅድመ ማዳመጥ

፩. በርሃማነት ማለት ምን ማለት ይመስላቸዋል?


፪. እፅዋትንና የሰውን ልጅ ሕይወት የሚያገናኛቸው ምን
ይመስላችኋል?
፫. ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር ማን ናቸው?

አዳምጦ መረዳት

ተግባር አንድ፡-

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ባዳመጣችሁት ምንባብ መሰረት ትክክለኛ


መልስ ስጡ፡፡
81 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፹፩
አማርኛ ፰ኛ ክፍል

፩. በአሁኑ ሰዓት በብዝኃ ሕይወት አጠባበቅ ላይ እየተሰራ ያለውን


ስራ እንዴት ታዩታላችሁ?
፪. ዶክተር ተወልደ የምድራችን ጀግና የሚል ስያሜን ያገኙት ምን
ስለሰሩ ነው?
፫. የቻይናና በኢኮኖሚ የበለፀጉ ሀገሮች የማደግ ሚስጥር ምንድን
ነው?
፬. ዶክተሩ አፍሪካን ወክለው ንግግር ያደረጉት በየትኛው ጉባኤ ነው?
፭. የዕፅዋት ስያሜ ‘‘ፕሮጀክት’’ ተግባራዊ እንዲሆን ዶክተር ተወልደ
ምን ሰሩ?
፮. የምንባቡ አጠቃላይ ሐሳብ ምንድን ነው?

ተግባር ሁለት፡-

የምድራችን ጀግና በሚል ከቀረበላችሁ ምንባብ ለወጡ ቃላት አውዳዊ


ፍች ስጡ፡፡

ሀ. ምድረ በዳ
ለ. ቀናዒነት
ሐ. ረባዳ
መ. ተበተበ
ሠ. ፈር

82 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፹፪


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ክፍል ሁለት፡- መናገር

ውይይት
ውይይትአላማ ያለው ጊዜና ቦታ ተወስኖለት አንድና ከአንድ በላይ
በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰዎች ሐሳባቸውን የሚለዋወጡበትና ከጋራ
መግባባት ላይ የሚደርሱበት ተግባር ነው፡፡ ውይይት በሚደረግበት
ፅንሰ ሀሳብ ዙሪያ በሚገባ መዘጋጀት በመጨረሻ ለሚጠበቀው ውጤት
እውን መሆን የራሱ የሆ አስተዋፅ ይኖረዋል፡፡

የውይይት ዝግጅት

• የመወያያ ርእሰ ጉዳይ መምረጥ


• ርዕሰ ጉዳዩን በሚገባ መረዳት
• ርዕሰ ጉዳዩን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ መሰብሰብ
• በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ ዋና ዋና ነጥቦችን መለየት
• በየትኛውም ጉዳይ የተሰበሰቡትን መረጃዎች ታዳሚዎችን
የሚመጥኑ መሆኑን ማረጋገጥ
• ፍሬ ሀሳቦችን በቅደም ተከተል ማስቀመጥና በቂ ዝግጅት
ማድረግ

የውይይት አቀራረብ
• አለባበስንና ንፅህናን ጠብቆ መገኘት
• የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮችን ማስተዋወቅ
• ተራን ጠብቆ መናገር፣
• የሌሎችን ሀሳብ ማክበር፣
• ያልተንዛዛና የተመጠነ ሀሳብን በቅደም ተከተል ማቅረብ
• ፍርሃትና ግደለሽነትን ማስወገድ

83 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፹፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
• ሲናገሩ ድምፅን መመጠን፣
• ፍሬ ሀሳቦችን በምሳሌና በማስረጃ ማስደገፍ
• ተገቢ የአገላለፅ ስልት መከተልና አንደበትንt ማስላት
• ከታዳሚዎች የሚመጡ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን መቀበል
• የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በአግባቡ አዳምጦ ምላሽ መስጠት

ተግባር፡-

ከዚህ በታች በቀረቡላችሁ አንቀፆች ላይ ተወያይታችሁ የተረዳችሁትን


ሀሳብ በተወካያችሁ አማካኝነት ለክፍል ጓደኞቻችሁ በቃል አቅርቡ፡፡

---ደራሲነት ከባድ ስራ ነው፤ ሰው የሚመስሉ ገፀባህርያት ለመፍጠር


ሰውን ማጥናት፣ ሰውን በውል መረዳት፣ ተፈጥሮንና ማህበረሰቡን
ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ እውነተኛ ደራሲ ማህበረሰቡ ሲጨነቅ የሚጨነቅ፣
ሲያዝን የሚያዝን፣ ሲፈነድቅ ደግሞ አብሮ የሚፈነድቅ፣ የሰው ለጅ
ፍቅር ያለው ለየት ያለ ፍጡር ነው---፡፡
(ዘሪሁን አስፋው፣ 1998 ዓ.ም፣ ገፅ ፭፰ ያልታተመ)

---ትክክለኛ የወግ ጸሐፊ ገና ብዕሩን ሲጨብጥ የቃላት ዓይነቶች


ከነምስላቸው ይዥጎደጎዱለታል፡፡ ዓላማው በምናቡ አግዝፎ የሚያየውን
ጉዳይ በጥሩ አቀራረብ አቀናጅቶ ወረቀት ላይ መቅረፅ ነው፡፡ ርዕሱ
ወደሚመራው አቅጣጫ ትንሽ፣ ትልቅ ሳይል በነፃ መንፈስ፣ በምናባዊ
እይታው ጭልጥ ብሎ ይነጉዳል----፡፡
(መስፍን ሀ/ማርያም፣ 1992፣ ገፅ ፮)

84 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፹፬


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ክፍል ሶስት ፡- ንባብ

ተፈጥሮን የመመለስ ስራ

ቅድመ ንባብ
፩. በርሃማነት የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድን ነው?
፪. ተፈጥሮን በመንከባከብ በርሃማነትን እንዴት መከላከል የሚቻል
ይመስላችኋል?
፫. የቀረበውን ስዕል አይታችሁ የተረዳችሁትን ግለፁ፡፡

ተፈጥሮን የመመለስ ስራ

በሀገራችን የሚካሄደው የተፈጥሮ ጥበቃ ስራ ብዙ ርቀት መሄድ


ያለበት በመሆኑ ለረዥም ዓመታት በተከታታይ ሳይቋረጡ የተሰሩት

85 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፹፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ስራዎች ከፍተኛ ለውጥና ውጤት አስገኝተዋል፡፡ ድርቅንና የተፈጥሮ
አየር መዛባትን በዘላቂነት ለመከላከልና ለመመከት የሚቻልበት
ብቸኛው መፍትሔም የተፈጥሮ ጥበቃ ስራን አጠናክሮ መቀጠል
ነው፡፡ በመሰረቱ ለድርቅና ለረሀብ፣ እንዲሁም ለተለያዩ ተፈጥሮአዊ
አደጋዎች መከሰት ዋናው ተጠያቂ የሰው ልጅ ነው፡፡ ጫካዎችንና
ደኖችን ከመመንጠር ጀምሮ መሬትን በማራቆት ወደ በርሀማነት
እንዲለወጡ ከማድረጉ ባለፈ ከኢንዱስትሪዎች የሚለቀቀው በካይ
የኬሚካል ጋዝ በአየር ንብረት ላይ ይህ ቀረው የማይባል መዛባትና
አደጋ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህ የተነሳም አዳጊ ሀገራት
ከበለጸጉና ካደጉ ሀገራት ጋር በዓለም ላይ እየተከሰተ ስላለው የአየር
ንብረት መዛባትና እሱን ተከትሎ ስለመጣው የሰው ልጅ የከፋ አደጋ
ምክክርና ድርድር ውስጥ ገብተዋል፡፡
በእኛ ሀገርም የነበረው የደን ሽፋን ተመናምኖ እና መሬቱ ወደ
በረሀማነት ተለውጦ እያስከተለ ያለው ችግር በቀላሉ የሚፈታ መሆን
አልቻለም፡፡ በደኖች መመንጠርና መመናመን ምክንያት የዱር አራዊት፣
እንሰሳትና አዕዋፋት ጭምር መኖሪያቸውን ለቀው ወደጎረቤት ሀገራት
ተሰደዋል፤ ከየተራራው ስር ይፈልቁ የነበሩትና ትውልድን ያጠግቡ
የነበሩት ምንጮች ደርቀዋል፤ ሰብል ዘርቶ ለማብቀል አዳጋች ሆኗል፡
፡ ይህ ደግሞ የአየር ንብረት መዛባት ከፈጠረው አደገኛ ችግር
ጋር የተያያዘና የተቆራኘ ነው፡፡ ይህንን የአየር ንብረት መዛባት ችግር
ዘለቄታዊ በሆነ መንገድ መቅረፍ የሚቻለው የተፈጥሮ ጥበቃ ስራን
አጎልብቶ በመስራት ብቻ ነው፡፡

• ለድርቅና ለረሀብ ዋነኛው ተጠያቂ የሰው ልጅ ነው የተባለው


ለምንድን ነው?
• ተፈጥሮ ወደነበረችበት እንድትመለስ የሰው ልጅ ምን ምን
ነገሮችን መስራት የሚኖርበት ይመስላችኋል?

86 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፹፮


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተፈጥሮ በራሷ መንገድ ከምትፈጥረው ጫና ውጪ በአብዛኛው
ለድርቅና ለረሀብ ምክንያቱ የሰው ልጅ በራሱ የሚፈጥረው ችግር
ነው፡፡ በተለይም ከበካይ የከባድ ኢንዱስትሪዎች ጭስ ልቀት ጋር
ተያይዞ የሚከሰቱ ችግሮች ሰፊ ናቸው፡፡ ይህንን ለመከላከል የሚቻለው
ምድርን ጥንት ወደነበረችበት አረንጓዴነት ለመመለስ በመስራትና
በመንከባከብ ብቻ ነው፡፡

በሀገራችን በሁሉም ክልሎች በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠረውን ሕዝብ


በማስተባበርና በማሰማራት ሰፊና ግዙፍ የተፈጥሮ ጥበቃ ስራ እየተሰራ
ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት የተራቆቱ ቦታዎችን እንዲያገግሙ እና
ወደ ቀድሞ ገፅታቸው እንዲመለሱ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ይሄው
የተፈጥሮ ጥበቃ ስራ በአዲስ አበባ፤ በአማራ፤ በኦሮሚያ፤ በትግራይ፤
በደቡብ፤ በአፋር፣ በቤኒሻንጉልና በሌሎችም ክልሎች ጭምር
በስፋት እየተሰራ ይገኛል፡፡ የአፈር መሸርሸርን ለመግታት የእርከን
ስራ፤ የችግኝ ተከላ፤ የመስኖ ልማት ስራዎች ሁሉ እየተሰሩ ነው፡፡

በሀገራችን አርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን የዕለታዊ የአየር ንብረት


ትንበያዎች ተጠቃሚ እንዲሆን ማስተማርና ማሳወቅ ሊፈጠር
ከሚችለው የአየር ንብረት አደጋ  ግንዛቤ እንዲያገኝና እንዲጠነቀቅ
ያስችለዋል፡፡ የተፈጥሮ ሐብት ልማት ስራዎች በመላው ሀገሪቱ
በስፋትና በጥልቀት መካሄድ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ የተራቆቱ
ተራሮችና መሬቶች ወደቀደመው መልካቸው እየተመለሱ ይገኛሉ፤
ጠፍተው የነበሩ እጽዋት ተመልሰው በመብቀል ላይ ሲገኙ፤ ተሰውረው
የነበሩ አዕዋፋትና የዱር እንሰሳትም ወደ ቦታቸው መመለስ ይዘዋል፡
ይህ ደግሞ ትልቅ ለውጥና ስኬት ነው፡፡
(ከዋልታ ቲቪ፤ ሚያዝያ 25/2009 ዓ.ም፤ ለማስተማሪያነት ተሻሽሎ የተወሰደ)

87 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፹፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

አንብቦ መረዳት
ተግባር አንድ፡-
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት ትክክል ከሆኑ “እውነት”
ስህተት ከሆኑ “ሐሰት” በማለት መልሱ፡፡
፩. የተፈጥሮ ጥበቃ ስራን በተመለከተ የተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ
ለውጥና ውጤት አስገኝተዋል፡፡
፪. ለድርቅ፣ ለረሀብና ለተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች መከሰት ዋናው
ተጠያቂ የሰው ልጅ ነው፡፡
፫. በሀገራችን ምንም እንኳ የደኖች መመንጠርና መመናመን የነበረ
ቢሆንም የዱር አራዊቱ፣ እንስሳቱና አዕዋፋቱ ቦታ እንዲቀይሩ
አላስገደዳቸውም፡፡
፬. የአየር ንብረት መዛባት ችግርን ዘለቄታዊ በሆነ መንገድ መቅረፍ
የሚቻለው የተፈጥሮ ጥበቃ ስራን አጎልብቶ በመስራት ብቻ ነው፡፡
፭. በሀገራችን በሁሉም አካባቢዎች የተፈጥሮ ጥበቃ ስራ ተጠናክሮ
እንደቀጠለ ነው፡፡

ተግባር ሁለት፡-

ለሚከተሉት ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት ትክክለኛ መልስ


ስጡ፡፡
፩. የሰው ልጅ በተፈጥሮ ላይ የሚያደርሳቸው ጥፋቶች ምን ምን
ናቸው?
፪. ድርቅንና የተፈጥሮ አየር መዛባትን በዘላቂነት ለመከላከል ምን
መደረግ አለበት?
፫. ምድርን ቀድሞ ወደነበረችበት አረንጓዴነት መመለስ ሲባል ምን
ማለት ነው?
፬. “በርሃማነት” የሚለውን ምንባብ በራሳችሁ አባባል በአንድ አንቀፅ
አጠቃላችሁ ፃፉ

88 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፹፰


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል አራት፡- ጽሕፈት
ገላጭ ድርሰት
ገላጭ ወይም አስረጅ ድርሰት የአንድን ነገር አሰራር፣ አፈፃፀም፣
ምንነት፣ ባህርያት፣ ቅርፅ፣ አይነት፣ መጠን፣ አገኛኘት፣ ጠቀሜታ
ወይም ጉዳት ወዘተ. ለማብራራት የሚፃፍ የድርሰት ዓይነት ነው፡፡
ምሳሌ አንድ፡- በእስልምና ሀይማኖት በደማቅ ሁኔታ ከሚከበሩ
በዓላት መካከል የኢድ-አል አድሃ(አረፋ) በዓል አንዱ ነው፡፡ በዓሉ
የእርድ ወይም የመስዋዕትነት በዓል በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ክብረ
በዓል የሚከበረው በኢስላማዊ ዘመን አቆጣጠር በአስራ ሁለተኛው
ወር ዙልሂጃ ላይ ነው፡፡ ለበዓሉ የሚታረደው ስጋ አንድ ሶስተኛው
በቀጥታ ለድሆች የሚከፋፈል ሲሆን ሌላኛው አንድ ሶስተኛ ደግሞ
ለዘመድና ለወዳጅ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ቀሪው አንድ ሶስተኛ ግን
ለቤተሰብ አገልግሎት የሚውል ይሆናል፡፡
ምሳሌ ሁለት፡- የደሮ ወጥ አሰራር
የደሮ ወጥ ለመስራት መጀመሪያ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችንና
ቅመሞችን እናዘጋጃለን፡፡ እነዚህ ግብዓቶችም፡- ሽንኩርት፣ የተበለተ
የዶሮ ስጋ፣ ዘይት፣ ጨው፣ የሀበሻ ቅቤ፣ ጥቁር ቅመም፣ መከለሻ፣
የተቀቀለ እንቁላልና እንደየሰው ፍላጎት ሌሎች ቅመማ ቅመም ይገባሉ፡
፡ አሰራሩን በተመለከተ በመጀመሪያ ሽንኩርቱ ተልጦ ይከተፋል፡፡
በመቀጠልም ተለቅ ባለ ሸክላ ድስት ወይም ብረድስት ተጥዶ በደንብ
ይበስላል፡፡ ሽንኩርቱ በሚገባ ከበሰለ በኋላ ዘይት ወይም ቅቤ እና
በርበሬ እንደየቅደም ተከተሉ በማስገባት በደንብ ይቁላላል፡፡ ሽንኩርቱ
ከበርበሬው ጋር እየተቁላላ የተበለተው ዶሮ ስጋ በሎሚና በጨው
ተዘፍዝፎ በደንብ ይታጠባል፡፡ ቁሌቱ ላይ ጥቁር ቅመም ይገባል፡
፡ ስጋው በንፁህ ውሃ በደንብ ከተለቀለቀ በኋላ በቢላዋ ምልክት
እየተደረገበት ቁሌቱ ውስጥ ይጨመራል፡፡ የደሮው ስጋ እስኪበስል
የተቀቀለውን እንቁላል በመላጥ እናዘጋጀዋለን፡፡ ስጋው ትንሽ በሰል
ሲል በሙቅ ውሃ ከልሰን በደንብ ከተንተከተከ በኋላ መከለሻ ቅመም፣
89 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፹፱
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ልጠን ያዘጋጀነውን እንቁላል፣ ጨው እና ቅቤ በመጨመር አውጥተን
ለምግብነት እናውለዋለን፡፡

ተግባር፡-

፩. የሰው ልጅ ከልደት እስከሞት የሚያልፍባቸውን ሂደቶች በቅደም


ተከተል ገለፃዊ በሆነ መንገድ ፃፉ፡፡
፪. የፃፋችሁትን ጹሑፍ ዕርስ በዕርስ በመቀያየር ከገላጭ ጹሑፍ
ቅርፅ አንፃር ተገማገሙ፡፡

ክፍል አምስት፡- ቃላት

የቃላት እማሬያዊና ፍካሬያዊ ፍች


ተግባር አንድ፡-

በምሳሌው መሰረት የሚከተሉት ቃላት እማሬያዊና ፍካሬያዊ ፍች


ተጠቅማችሁ ዓረፍተነገር ስሩ፡፡
ምሳሌ፡- እርግብ
• እማሬያዊ ፍች፡- እርግብ በራሪ የወፍ ዝርያ ናት፡፡
• ፍካሬያዊ ፍች፡- ቤተልሄም እርግብ ናት፡፡

ተ.ቁ ቃል ዓረፍተነገር

እማሬያዊ ፍች ፍካሬያዊ ፍች
፩ መሬት
፪ ምስጥ
፫ ጉቶ
፬ እርጥብ
፭ ምላጭ
፮ እሳት
90 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር ሁለት፡

ቀጥሎ የቀረቡትን ቃላት ቀጥተኛ ፍች ከመዝገበ ቃላት ፈልጋችሁ


በደብተራችሁ አስፍሩና ለመምህራችሁ አሳዩ፡፡
፩. ትንቢት ፭. አዛውንት
፪. መባቻ ፮. ቀጠሮ
፫. ማግስት ፯. ማነፅ
፬. በለተ

ክፍል ስድስት፡- ሰዋስው

ዓረፍተ ነገር
ከአገልግሎት ወይም ከሰዋስዋዊ ቅርፅና ከይዘት አንፃር በአራት
ይከፈላል፡፡ እነሱም፡-
፩. ጥያቄያዊ ዓረፍተ ነገር፡- መጠይቃዊ ቃላትን በተዋቃሪነት በውስጡ
ይይዛል፡፡
ምሳሌ፡- -ወዴት ትሔዳለህ?
፪. ትዕዛዛዊ ዓረፍተ ነገር፡- ትእዛዝን የሚያሳይ ዓ.ነገራዊ ቅርፅ እና ይዘት
አለው፡፡
ምሳሌ፡- -የቤት ስራችሁን በአግባቡ ሰርታችሁ ኑ!
፫.ሀተታዊ ዓረፍተ ነገር፡-በአሉታዊ ወይም በአወንታዊ መልክ
የሚቀርብ ነው፡፡
ሀ. አዎንታዊ ዓረፍተ ነገር -ተስፋዬ ለልጁ ደብተር ገዛ፡፡
ለ. አሉታዊ ዓረፍተ ነገር -ተስፋዬ ለልጁ ደብተር አልገዛም፡፡

፬. አጋናኝ ዓ.ነገር፡- ነገሮችን አግዝፎ ወይም በጣም አሳንሶ የሚያቀርብ


የዓ.ነገር አይነት ነው፡፡
ምሳሌ፡- -እፎይ! ገና አሁን ቀን ወጣልኝ።

91 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፺፩


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር አንድ፡-

የሚከተሉትን ዓረፍተነገሮች ጥያቄያዊ፣ ትዕዛዛዊ፣ ሀተታዊ እና


አጋናኝ በማለት መልሱ፡፡
ሀ. ጎበዝ ተማሪ በርትቶ ያጠናል፡፡
ለ. የቤት ስራህን ስራ!
ሐ. ለምን ሁልጊዜ ትረብሻለህ?
መ. ልጁ ትናንት ደብተር አልገዛም፡፡
ሠ. እሴያ! ልጄ በጥሩ ውጤት ተመረቀችልኝ።

ተግባር፡-
የዓረፍተነገሮችን አገልግሎት የሚያሳዩ ሶስት ሶስት ዓረፍተነገሮች
ስሩ፡፡

92 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፺፪


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ማጠቃለያ
በዚህ ምዕራፍ ገላጭ ወይም አስረጅ ድርሰት የአንድን ነገር አሰራር፣
አፈፃፀም፣ ምንነት፣ ባህርያት፣ ቅርፅ፣ አይነት፣ መጠን፣ አገኛኘት፣
ጠቀሜታ ወይም ጉዳት ወዘተ. ለማብራራት የሚፃፍ የድርሰት
አይነት መሆኑን ተገንዝበናል፡፡

በተጨማሪም የቃላት እማሬያዊ ፍች ማለት የቃላት የተለመደ ወይም


የተዘወተረ ትርጉም እንደሆነና ፍካሬያዊ ፍች ማለት ደግሞ የቃላት
ድብቅ ወይም ስውር ፍች መሆኑን ተረድተናል፡፡ በመጨረሻም
ዓረፍተ ነገር ከአገልግሎት አንፃር ጥያቄያዊ፣ ትዕዛዛዊ፣ ሀተታዊ
እና አጋናኝ ተብሎ እንደሚከፈል ተምረናል፡፡

የክለሳ ጥያቄዎች

ተግባር አንድ፡-

የሚከተሉትን ቃላት እማሬያዊና ፍካሪያዊ ፍች ተጠቅማችሁ


ዓረፍተነገር ስሩ፡፡

ሀ. ነብር ሠ. ብረት
ለ. ጎጆ ረ. ደረቅ
ሐ. ውሻ ሰ. ባህር
መ. አባት ሸ. እናት

93 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፺፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር ሁለት፡-

የሚከተሉትን ዓረፍተነገሮች ጥያቄያዊ፣ ትዕዛዛዊ፣ ሀተታዊ እና


አጋናኝ በማለት መልሱ፡፡

ሀ. የወርቅ ሀብሌን ማን ወሰደው?


ለ. ትምህርትህን አጥና!
ሐ. ሀኪሞቹ ሆስፒታል ውስጥ አልተገኙም፡፡
መ. ንፁህ ትምህርት ቤትገብታለች፡፡
ሠ. ጎሽ! አንበሳ እኮ ነህ።

94 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፺፬


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ምዕራፍ ሰባት

የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ

ከምዕራፉ የሚጠበቁ ውጤቶች፣ ይህንን ምዕራፍ ተምራችሁ ከጨረሳችሁ


በኋላ፡-
• መረጃ ሰጪ ጽሁፍን በጥልቀት ታዳምጣላችሁ፤
• የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ምንነትና የሚያስከትለውን ውጤት
ትገልጻላችሁ፤
• በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ትወያያላችሁ፤
• የአረፍተ ነገሮችን ተግባር ታነጻጽራላችሁ

95 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፺፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል አንድ፡- ማዳመጥ

የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛና ሕገ ወጥ ዝውውር በከተማችን

96 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፺፮


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ቅድመ ማዳመጥ
፩. ስለ ሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ ምንነት የምታውቁትን ተናገሩ?
፪. ህገ ወጥ የሕጻናት ዝውውር ሲባል ምን ማለት ይመስላችኋል?
፫. አንዳንድ ወላጆች ለሕጻናት የህገ ወጥ ዝውውር አስተዋጽ
የሚያደርጉት በምን ዓይነት መንገድ ነው? እንዴት?
፬. ስዕሉን በመመልከት የተረዳችሁትን ነገር አብራሩ፡፡

አዳምጦ መረዳት

ተግባር አንድ፡-

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ካዳመጣችሁት ምንባብ በመነሳት ትክክለኛ


መልስ ስጡ፡፡
፩. ሕጻናት በአቅማቸው መስራት አለባቸው ሲባል ምን ማለት ነው?
፪. ሕጻናትን ለጉልበት ብዝበዛና ለህገወጥ ዝውውር የሚዳርጉ
መንስኤዎች ምን ምን ናቸው?
፫. የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ ከተለያዩ ወንጀሎች ጋር ይያያዛል ሲል
ምን ለማለት ፈልጎ ነው?
፬. የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛና ህገ ወጥ ዝውውር በሕጻናቱ ላይ
የሚያስከትሏቸው አሉታዊ ተጽዕኖዎች ምን ምን ናቸው?
፭. ለህገ ወጥ ዝውውር የሚጋለጡ ሴት ሕጻናት ለተለያዩ ችግሮች
ይዳረጋሉ ሲል ምን ማለቱ ነው?
፮. ሕጻናት ከወላጆቻቸው ማግኘት ያለባቸው ነገር ምንድን ነው?
፯. የሕጻናት መብት ድንጋጌዎች ላይ የሰፈሩት ሀሳቦች ምንድን
ናቸው?

97 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፺፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር ሁለት፡-

በ“ሀ” አምድ ስር የቀረቡትን ቃላትና ሐረጋት በ”ለ”አምድ ስር ካሉት


ፍችዎቻቸው ጋር አዛምዱ፡፡
“ሀ” “ለ”
፩. መገናኛ ብዙሃን ሀ. ስስታም፣አልጠግብ ባይ
፪. መታነፅ ለ. መሰደድ፣ ከቦታ
ቦታ መንቀሳቀስ
፫. ክስተት ሐ. ተጫዋች፣
፬. ሥግብግብ መ. አዲስ ነገር
፭. ሞግዚት ሠ. መልዕክት ማሰራጫ
፮. መፍለስ ረ. ተንከባካቢ
፯. ተዋናይ ሰ. መቀረፅ፣ መገንባት

ክፍል ሁለት፡- መናገር

ተግባር፡-

በሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አራት አራት በመሆን ተወያይታችሁ


ከስምምነት ላይ የደረሳችሁበትን ሀሳብ በተወካያችሁ አማካኝነት
ለክፍል ጓደኞቻችሁ በንግግር አቅርቡ፡፡
፩. የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት
ምን ይጠበቃል?
፪. ለህገ ወጥ ዝውውር ተጋላጭ የሆኑ ህፃናት ምን ምን ችግሮች
የሚያጋጥሟቸው ይመስላችኋል?
፫. ሕጻናት የራሳቸውን መብት ማስከበር የሚችሉ ይመስላችኋል?
እንዴት?

98 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፺፰


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል ሶስት፡- ንባብ
የማሪቱ እና የመሰሎቿ ፍዳ

ቅድመ ንባብ
፩. ርዕሱንና ስዕሉን በማየት ምንባቡ ስለምን እንደሚያወራ ገምቱ፡፡
፪. ልጆች ቤተሰቦቻቸውን ማገዝ ያለባቸው እንዴት ይመስላችኋል?

የማሪቱ እና የመሰሎቿ ፍዳ
ማሪቱ በለጠ ተወልዳ ካደገችበት ምስራቅ ጎጃም ሞጣ ከተማ ከመጣች
ሁለት ዓመት ሊሞላት ጥቂት ቀናት ብቻ እንደቀራት ነገረችኝ፡፡
ከሰውነት ጎዳና የወጣ ፊቷ በድካም የመወየብ ምልክቶች ቢታዩበትም
ጠይምና መልከ መልካም ናት፡፡ 13 ዓመት ሆኗታል፡ ያገኘኋት
በአዲስ አበባ ሰፊ የቤቶች ግንባታ በሚካሄድበት ቦሌ ክፍለ ከተማ
ሲ ኤም ሲ/ሰሚት አካባቢ ነው፡፡ በሞጣ ከተማ እስከ ሁለተኛ ክፍል
ተምሬያለሁ ያለችኝ ልበገሯ ማሪቱ፤ ከጎጃም ይዛት የመጣችው
አክስቷ ወደ አረብ ሃገር ስትሄድ ለአባቷ ዘመዶች ሰጥታት እንደሄደች
አጫወተችኝ፡፡ ነገር ግን አክስቷም ሆነች አሁን የምትኖርባቸው
ዘመዶቿ “የተሻለ ትምህርት ቤት እናስገባሻለን” ቢሏትም የትምህርት
ቤት ደጃፍን ከረገጠች ድፍን ሁለት ዓመት ሊሆናት ነው፡፡ በዚህም
ሁልጊዜ ሆድ ስለሚብሳት ታለቅሳለች፤ ስለ ትምህርትም ስጠይቋት፣

99 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፺፱


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
በርዕሱ መነሳት ደስተኛ እንዳልሆነች የሚሸሸኝ አይኗ ያሳብቃል፡፡
የምትኖርባቸው ዘመዶቿ በዕድሜ ከዕሷ የሚያንሱ ሶስት ልጆች
እንዳሏቸው የገለጸችልኝ ማሪቱ እሷግን ቤት ውስጥ ምግብ መስራት፣
ቤት ማጽዳት፣ ልብስ ማጠብ፣ ልጆችን መንከባከብ፣ ትምህርት ቤት
ሲሄዱ ምሳ ዕቃ መቋጠር ወዘተ. የዕለት ተዕለት ሕይወቷ መሆኑን
ድካም ባዛለው ድምጿ ነገረችኝ፡፡

ይህ የማሪቱ ታሪክ ከአያት እስከ አየር ጤና፣ ከአዲሱ ገበያ እስከ


ቃሊቲ፣ ከልደታ እስከ ቦሌ፣ ከፒያሳ እስከ መገናኛ፣ ከሽሮ ሜዳ እስከ
ፈረንሳይ፣ ከጦር ሀይሎች እስከ አስኮ ወዘተ በርካታ የአዲስ አበባ
ቤቶችን የሚያንኳኳ፤ የክልል ከተሞችንም የሚነካ እውነታ ነው፡፡
በኢትዮጵያ አሁንም በገጠር ያለው ድህነት ከከተማው የከፋ
ነው፡፡ከኢኮኖሚ ባለፈ ገጠሬው በማህበራዊ አገልግሎቶትም በከተሜው
የሚመራ መሆኑ ደግሞ ‘‘ከድጡ ወደማጡ’’ ሆኖ በርካታ የማሪቱ
እኩዮች ከተማን እንዲናፍቁ አስገድዷቸዋል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን
ማህበራዊ ትስስራችን ጠንካራ በመሆኑ ልጅን ከተማ ያለ ቤተ-ዘመድ
ጋር ልኮ ማስተማር የተለመደ ነው፡፡

በምንባቡ መሰረት ማሪቱ ለደረሰባት ችግር ተጠያቂው ማን ነው?


የማሪቱ ሕይወት መጨረሻው ምን የሚሆን ይመስላችኋል?
የወላጅን አደራተ ቀብለው የሚያስተምሩ በርካቶች መኖራቸው
የማያጠራጥር ቢሆንም የማሪቱ ዘመዶች አይነት በገጠር አልያም
በአነስተኛ ከተሞች ያለ ቤተ-ዘመድን አቅም ማጣት ምክንያት
አድርገው የልጆቻቸውን እኩዮች ጉልበት የሚበዘብዙም ቁጥራቸው
ቀላል የሚባል አይደለም፡፡

ማሪቱ በጠዋት ተነስታ ወደ ትምህርት ቤት የሚወስዳቸውን አውቶብስ


አንድ ሰዓት ላይ ለሚጠብቁት ሶስት ታዳጊዎች ልብስ ማልበስ፣ ቁርስ

100 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ



አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ማዘጋጀትና የምሳ እቃቸውን መቋጠር ይጠበቅባታል፡፡ በተጨማሪም
‘‘ነውር ጌጡ’’ ለሆኑት የቤቱ ጌቶችም ምግብ ማዘጋጀት፣ ቤት
ማፅዳት፣ ልብስ ማጠብ ወዘተ. ደግሞ በተከታታይ የሚጠብቋት
ተግባራት ናቸው፡፡ ስለዚህ እንደ ጋራ ፊቷ የተቆለለው ስራ ካላለቀ
የሚደርስባትን የቁጣ ውርጅብኝ ሽሽት ያለ እረፍት ስትባትል
ትውላለች፡፡ ገና በለጋነቷ አምስት አባላት ያለውን ቤተሰብ፣ የዕለት
ተዕለት ስራ የተሸከመችው ማሪቱ፤ የልጅነት ወዟ እየተመጠጠ
መሆኑን እረፍት የራቀውና በስራ ብዛት የደቀቀው ሰውነቷ ይጠቁማል፡፡

ማሪቱ ምንም እንኳን ሰማይ ስለተደፋባት በምትኖረው ኑሮ ደስተኛ


ባትሆንም ‘‘አድሮ ቃሪያ’’ የሆነው ሕይወቷ አንድ ቀን ለውጥ
ይኖርና ያልፍልኛል በሚል ተስፋ ኑሮዋን መግፋቷ ግን አልቀረም፡
የማሪቱና መሰሎቿን ሕይወት መቀየር የሚቻለው በሕፃናት እና
በሴቶች ላይ ከፍተኛ ጫና ባለባቸው አካባቢዎች፣ የማህበረሰቡን
ግንዛቤ በማሳደግ፤ እንደ ትምህርትና ጤና የመሳሰሉ ማህበራዊ
አገልግሎቶችን በማስፋፋት ነው፡፡

አንብቦ መረዳት

ተግባር አንድ፡-

የሚከተሉትን ጥያቄዎችን በጥሞና በማንበብ ትክክል ከሆኑ ‹‹እውነት››


ስህተት ከሆኑ ደግሞ «ሕሰት» በማለት መልሱ፡፡
፩. ማሪቱ ከተወለደች ጀምሮ የትምህርት ቤትን ደጅ ረግጣ አታውቅም፡፡
፪. በምንባቡ አንቀፅ ሁለት ላይ ማሪቱ የምትኖረው የተደላደለ ኑሮ
እንደሆነ ተገልጿል፡፡
፫. የወላጅን አደራ ተቀብለው ልጆችን በአግባቡ የሚያሳድጉና
የሚያስተምሩ ሰዎች አሉ፡፡
፬. በኢትዮጵያ ውስጥ በገጠር ያለው ድህነት ከከተማው እንደሚብስ
የሚያስረዳው ሁለተኛው አንቀጽ ነው፡፡
101 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፩
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፭. የማሪቱንና የመሰሎቿን ሕይወት ለመቀየር ከተፈለገ
የማህበረሰቡ ግንዛቤ ማደግ ይኖርበታል፡፡
፮. ጽሁፉን እየተረከች ያቀረበቸው ራሷ ማሪቱ ናት፡፡

ተግባር ሁለት፡-
በሚከተሉት ዓረፍተነገሮች ውስጥ ለተሰመረባቸው ቃላት ፍች
የሚሆኑትን ምረጡ፡፡
፩. የትምህርትቤቱን ደጃፍ ከረገጠች ድፍን ሁለት ዓመት ሊሆናት
ነው፡፡
ሀ. ሰፈር ለ. በራፍ ሐ. አደባባይ መ. ክፍል
፪. ስለትምህርቷ ሲነሳ ደስተኛ እንዳልሆነች የሚሸሸኝ አይኗ
ያሳብቃል፡፡
ሀ. ይናገራል ለ. ይደብቃል ሐ. ይስቃል መ.ይለምናል
፫. እንደጋራ ፊቷ የተቆለለው ስራ ካላለቀ የቁጣ መዓት
ይወርድባታል፡፡
ሀ. የተሰበሰበው ለ. የተበተነው ሐ. የተከመረው
መ. ሀናሐ መልስ ናቸው
፬. የልጅነት ፊቷ እየተመጠጠ መሆኑን ሰውነቷ ይጠቁማል፡፡
ሀ. እያማረበት ለ. እየፈካ ሐ. ወዙ እየጠፋ
መ. ወዝ እየተፋ
፭. ከሰውነት ጎዳና የወጣው ፊቷ የመወየብ ምልክት ቢታይበትም
ጠይምና መልከመልካም ናት፡፡
ሀ. የመቅላት ለ. የመዋብ ሐ. የመገርጣት
መ. የመክሳት
፮. የዕለት ከዕለት ሕይወቷ ቤተሰቡን መንከባከብ እንደሆነ በዛለው
ድምጿ ነገረችኝ፡፡
ሀ. በደከመው ለ. በበረታው ሐ. ባማረው መ. በቀጠነው
፯. በርካታ የማሪቱ እኩዮች ከተማን እንዲናፍቁ አስገድዷቸዋል፡፡

102 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፪


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ሀ. ባልደረቦች ለ. ቤተሰቦች ሐ. ዘመዶች
መ. መሰሎች
፰. ልጅን ከተማ ያለ ዘመድ ጋር ልኮ ማስተማር የተለመደ ነው፡፡
ሀ. አስገብቶ ለ. ሰዶ ሐ. አስተላልፎ መ. አምጥቶ
፱. የሚደርስባትን የቁጣ ውርጅብኝ ሽሽት ያለ እረፍት ስትባትል
ትውላለች፡፡
ሀ. ስትለፋ ለ. ስትሰራ ሐ. ስትደክም መ. ሁሉም
፲. ማሪቱ ገና በለጋነቷ አምስት አባላት ያለውን ቤተሰብ ስራ ተሸከመች፡፡
ሀ. በህፃንነቷ ለ. በወጣትነቷ ሐ. በጮርቃነቷ
መ. በቀንበጥነቷ
ተግባር ሶስት፡-

በምንባቡ ውስጥ ያሉ ፈሊጣዊ አነጋገሮችን በማውጣት ትርጉማቸውን


ጻፉ፡፡
ተግባር አራት፡-
በ “ሀ” አምድ ስር ያሉትን ፈሊጣዊ አነጋገሮች በ “ለ” አምድ ስር
ካሉት ፍችዎቻቸው ጋር አዛምዱ፡፡
“ሀ” “ለ”
፩. ቃሉን ሰጠ ሀ. ሊቅ፣ አዋቂ፣ ተመራማሪ
፪. ቀንበር ሰበረ ለ. የስሚ ስሚ፣ ጭምጭምታ
፫. ነጭ ለባሽ ሐ. ሐጥያት
፬. የቀለም ቀንድ መ. ስማኝ፣ አዳምጠኝ
፭. የወሬ ወሬ ሠ. መሰከረ
፮. ደዌ ነፍስ ረ. ህግ ተላለፈ
፯. ውሃ መውቀጥ ሰ. የመንግስት ሰላይ
፰. የልጅ አዋቂ ሸ. ከንቱ ልፋት
፱. ድንጋይ ኳሱ ቀ. አስተዋይ፣ ቁምነገረኛ
፲. ጆሮ ስጠኝ በ. ደፋር፣ ለምንም ነገር የማይበገር
ተ. ፈሪ፣ እርብትብት
ቸ. የቀለም መበጥበጫ
103 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፫
አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ክፍል አራት፡- ጽሕፈት
ተግባር አንድ፡-

በጅምር የቀረቡትን አንቀፆች በሟሟላት አንቀፅ ጻፉ፡፡


፩. አንድ የራበው መንገደኛ ቤት ያንኳኳና የቤቱ ባለቤት ሲከፍትለት
‘‘የራበኝ መንገደኛ ነኝ እባካችሁ የሚበላ ነገር’’ ብሎ ጠየቀው፡፡ የቤቱ
ባለቤት ግን ገና እንዳየው ሚስቱ አንገቷ ላይ እባጭ ታማ ተጨንቆ
ነበርና ‘‘የራበው መንገደኛ እባክህ መድሀኒት ታውቅ እንዲሁ ብሎ
ጠየቀው፡፡ መንገደኛው ‘‘አዎ በደንብ አውቃለሁ‘‘በማለት ወደግቢ ገባ፡
፡ ከዚያም ‘‘እንዳክማት ከፈለጋችሁ ልትወጡ ይገባል’’ በማለት
አዘዛቸው፡ ቤት ውስጥ የነበሩት ሰዎችም ከበሽተኛዋ ጋር ትተውት
ወጡ፡፡ መንገደኛውም በሽተኛዋን ----------------------------------------
---------------------------------------------------------------------------------

፪. ‘‘ጋን በገል ይታጠናል’’ ይባላል፡፡ ጋንና ገል በሸክላነታቸው


አንድ ናቸው፡፡ አንድ ትንሽ ሸክላ አንድን ትልቅ ሸክላ የቃና ለውጥ
እንዲያደርግ ማጠኛ ትሆናለች፡፡ ከማህበረሰብዓዊ ግንኙነት አንፃር
ሲታይ አንድ ግለሰብ አንድ ማህበረሰብ ከአንድ አይነት ይዞታ እና
ሁኔታ ወደ ሌላ የተሻለ ይዞታ እና ሁኔታ እንዲለወጥ ምክንያት ወይም
መሳሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ለማድረግ ግለሰቡ የማህበረሰቡን
ስርዓትና መለያ ባህርያት በወጉ መገንዘብ አለበት፡፡ ግንዛቤው በከፊል
ከማህበረሰቡ የወል ግንዛቤ፣ ባህርይና ተግባር ያፈነገጠ ሊሆን
ይገባል፡፡ እንደዚህ ያለ አፈንጋጭ ግንዛቤ የያዘ ግለሰብ፤ ይዋል
ይደር እንጅ ግንዛቤው ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ማዳረሱ አይቀ
ርም----------------------------------------------------------------------------

104 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፬


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር ሁለት፡-

የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ በሕጻናት ላይ የሚያስከትለውን አካላዊና


ስነ-ልቦናዊ ችግር የሚመለከት ባለ አምስት አንቀጽ ጽፋችሁ ለክፍል
ጓደኞቻችሁ አንብቡላቸው፡፡

ክፍል አምስት፡-ቃላት

ተቃራኒ ፍች
ተግባር አንድ
ለሚከተሉት ቃላት ተቃራኒ ፍቻቸውን ከተሰጡት አማራጮች
መካከል በመምረጥ መልሱ፡፡
፩. ጉዳት
ሀ. ህመም ለ. መከፋት ሐ.ጥቅም መ. ችግር
፪. የግል
ሀ. የጋራ ለ. የሰው ሐ. የአንድ
መ. የነጠላ
፫. ጥፋት
ሀ. ክፋት ለ. ልማት ሐ. እድገት
መ.ሀብት
፬. እኩይ
ሀ. ሰናይ ለ. መጥፎ ሐ. አስቸጋሪ
መ. ሀይለኛ
፭. ቅንነት
ሀ. መልካምነት ለ. ጥሩ ሐ. ሰናይ
መ. ክፋት
፮. ሙቅ
ሀ. ለሰስ ያለ ለ. ቀዝቃዛ ሐ. የሚያቃጥል
መ. የማይታኘክ

105 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፯. ህቡዕ
ሀ. ድብቅ ለ. ስውር ሐ. ሚስጥራዊ
መ. ግልፅ
፰. ሁከት
ሀ. ሰላም ለ. ብጥብጥ ሐ. ነውጥ
መ. ሽብር
፱. ቧልት
ሀ. ፌዝ ለ. ቀልድ ሐ. ቁምነገር መ.ተረብ
፲. ኢምንት
ሀ. ቅንጣት ለ. ትንሽ ሐ. ጥቂት
መ. ብዙ

ተግባር ሁለት፡-
ከታች በዓረፍተነገር ውስጥ ለተሰመረባቸው ቃላት ተቃራኒ ፍች
የሚሆኑትን ከሰንጠረዡ እየመረጣችሁ ተኩ፡፡

ተጎጂ ንፉግ ያፋጥናሉ


መቀራረብ መጥፎ ህይወት
ምድረ በዳ ወረዛ ጥብቅ
፩. የኤልሳቤጥ አባት ለጋስ ናቸው፡፡
፪. በዝናብ እጥረት የተነሳ መሬቱ ደረቀ፡፡
፫. የነሙስጦፋ መንደር ነዋሪዎች የመስኖ ተጠቃሚ ናቸው፡፡
፬. ልማዳዊ እና ጎጂ ድርጊቶች የአንድን ሀገር እድገት ያጓትታሉ፡፡
፭. የእንጦጦ ጫካ ወደ መዝናኛነት ተቀይሯል፡፡
፮. የቤተሰብ መራራቅ ለህፃናት ስነ ልቦና ጉዳት አለው፡፡
፯. የክፍላችን አለቃ ፀባየ ሠናይ ነው፡፡
፰. የሁለቱ ዓረፍተ ነገሮች ቁርኝት ልል ነው፡፡

106 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፮


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር ሶስት፡-
ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ቃላት መካከል ልዩ የሆነውን ምረጡ፡፡
፩. ሀ. ተልባ ለ. ሱፍ ሐ. ኑግ መ. ሽንብራ
፪. ሀ. ክራር ለ. ዋሽንት ሐ. በገና መ. ማሲንቆ
፫. ሀ. ደቦል ለ. ሙጭሊት ሐ. ውርንጭላ መ. ቡችላ
፬. ሀ. ጀበና ለ. ድስት ሐ. ቅል መ. እንስራ
፭. ሀ. ጎመን ለ. ሰላጣ ሐ. ማንጎ መ. ቆስጣ
፮. ሀ. ጋቢ ለ. ፎጣ ሐ. ነጠላ መ. ኩታ
፯. ሀ. ሞፈር ለ. ቀንበር ሐ. ድግር መ. መንሽ
፰. ሀ. ጤፍ ለ. ዘንጋዳ ሐ. ማሽላ መ. በቆሎ
፱. ሀ. ባዝራ ለ. ቄብ ሐ. ጊደር መ. ኮረዳ
፲. ሀ. ሒስ ለ. ትችት ሐ. ነቀፋ መ. ዘለፋ

ክፍል ስድስት፡- ሰዋስው


ተግባር አንድ ፡-
የሚከተሉትን ዓረፍተነገሮች ሀተታዊ (አሉታዊ፣ አዎንታዊ)፣
ትዕዛዛዊ፣ እና መጠይቃዊ በማለት መልሱ፡፡
፩. ያንን ጫማ ማን ገዛልሽ?
፪. ወጣቶቹ አውሬውን ገደሉት፡፡
፫. ተማሪዎች ወደ ትምህርትቤት እንዳይመጡ!
፬. ደመወዝ ተቀበልክ እንዴ?
፭. ወለሉን ጥረጊ!
፮. ሕጻኗ የሰበረችው ምንድን ነው?
፯. መቅደስ ትናንት የወርቅ ቀለበት ገዛች፡፡
፰. ባለፈው የተመረቀው ልጅ ልብስ አልተገዛለትም፡፡
፱. ልብስ አትጠቡ!
፲. ለበሽተኛው መድሃኒት ተገዛለት፡፡

107 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር ሁለት፡-
በ “ሀ” አምድ ስር ያሉትን የዓረፍተነገር ዓይነቶች በ “ለ” አምድ
ውስጥ ካለው አገልግሎታቸው ጋር አዛምዱ፡፡
“ሀ” “ለ”
፩. ሐተታዊ ዓ.ነገር ሀ. ነገሮችን አግዝፎ፣አሳንሶ
የሚያቀርብ ዓ.ነገር
፪. ትዕዛዛዊ ዓ.ነገር ለ. መጠይቃዊ ቃላትን በተዋቃሪነት
ይይዛል
፫. መጠይቃዊ ዓ.ነገር ሐ. በአሉታዊና በአዎንታዊ መልክ
የሚቀርብ ዓ.ነገር
፬. አጋናኝ ዓ.ነገር መ. ትዕዛዝን የሚያሳይ ዓ.ነገር

108 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፰


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ማጠቃለያ
በዚህ ምዕራፍ የቃላት ተቃራኒን ምንነት ተረድተን ቃላትን
ከተቃራኒዎቻቸው ጋር አዛምደናል፡፡ በመቀጠልም ዓረፍተ ነገር
ከአገልግሎት አንፃር ጥያቄያዊ፣ ትዕዛዛዊ፣ ሀተታዊ እና አጋናኝ
ተብሎ እንደሚከፈል አስታውሰን ዓረፍተነገሮችን ከአገልግሎታቸው
ጋር ለማዛመድ ችለናል፡፡

በአዎንታዊ ወይም በዓሉታዊ መልክ የሚቀርብ ዓረፍተ ነገር


ሀተታዊ ዓረፍነ ነገር ሲባል ትዕዛዝን ለማመልከት የምንጠቀምበት
ዓረፍተነገር ደግሞ ትዕዛዛዊ ዓረፍተነገር እንደሚባል አይተናል፡፡
በተጨማሪም መጠይቃዊ ቃላትን በተዋቃሪነት የያዘ ዓረፍተነገር
ጥያቄያዊ ዓረፍተነገር ሲባል ነገሮችን አግዝፎ ወይም አሳንሶ
ለማቅረብ የሚያገለግል ዓረፍተነገር አጋናኝ ዓረፍተነገር እንደሚባል
ተገንዝበናል፡፡

የክለሳ ጥያቄዎች

ተግባር አንድ፡-
የሚከተሉትን ፈሊጣዊ አነጋገሮች ፍች ፃፉ፡፡
፩. እንጀራ ወጣለት
፪. የውሀ ሽታ
፫. የግንባር ስጋ
፬. ገመና ከታች
፭. ጉልበት አወጣ
፮. ደግ ዋለለት

ተግባር ሁለት፡-
የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች ሐተታዊ (አዎንታዊ፣ አሉታዊ)፣

109 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፱


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ትዕዛዛዊ፣ መጠይቃዊና አጋናኝ በማለት ለዩ፡፡
፩. የሂሩት ልጅ ትናንት አገባ፡፡
፪. ትምህርት ቤቱ መቼ ተከፈተ?
፫. እንግዶቹ ከሄዱበት አልተመለሱም፡፡
፬. አርፈሽ ትምህርትሽን አጥኚ!
፭. የፈጣሪ ስራ እፁብ ድንቅ ነው!

110 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፲


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ምዕራፍ ስምንት

ሰላም

ከምዕራፉ የሚጠበቁ ውጤቶች፣ ይህንን ምዕራፍ ተምራችሁ


ከጨረሳችሁ በኋላ፡-
• አዳምጣችሁ ፅሁፉን ትተነትናላችሁ፤
• የሰላምን አስፈላጊነት ትገልፃላችሁ፤
• አንብባችሁ የፅሁፉን ሀሳብ አጠቃላችሁ ትፅፋላችሁ፤
• በፅሁፍ ውስጥ ተገቢውን ስርዓተ ነጥብ ትጠቀማላችሁ፤

111 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፲፩


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ክፍል አንድ፡- ማዳመጥ

ሰላምን ፍለጋ

ቅድመ ማዳመጥ
፩. ሰላምን ፈልጎ ማግኘት የሚቻል ይመስላችኋል? እንዴት?
፪. የሰላምን አስፈላጊነት ግለፁ፡፡
፫. ስዕሉን በመመልከት የተረዳችሁትን ነገር አብራሩ፡፡

አዳምጦ መረዳት

ተግባር አንድ፡-
ባዳመጣችሁት ምንባብ መሰረት ትክክል ከሆኑ “እውነት” ስህተት
ከሆኑ ደግሞ “ሐሰት” በማለት መልሱ፡፡
፩. ሰዎች ብዙ ደክመውም ቢሆን ሰላምን ፈልገው ማግኘት ችለዋል፡፡
፪. ሰላምን መፈለግ ብቻውን የሰላም ማስፈኛ መሳሪያ ነው፡፡
፫. በአሁኑ ሰዓት የሰላም መደፍረስ ምክንያት ከወትሮው ይልቅ
ቀላል ለመፍታት ግን አስቸጋሪ ነው፡፡

112 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፲፪


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፬. የዓለም መንግስታት የሰላም ማስጠበቅ ስምምነት ሰነድ
በመፈራረማቸው ሰላምን ማስፈን ችለዋል፡፡
፭. ሰላም የእያንዳንዱን ግለሰብ በጎ ፈቃድና ትብብር የሚጠይቅ
ነው፡፡
፮. ከራሱጋር ሰላም ያላወረደ ግለሰብ ከሌላው ማህበረሰብ ጋር
በሰላም ለመኖር አይቸገርም፡፡

ተግባር ሁለት፡-

ባዳመጣችሁት ምንባብ መሰረት ለሚከተሉት ጥያቄዎች


ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡
፩. ከሚከተሉት አንዱ ሰላምን በተመለከተ የወጣ ስያሜ አይደለም፡፡
ሀ. ደብረ ሰላም ለ. ሀገረ ሰላም
ሐ. ፍቅረ ሰላም መ. መልስ አልተሰጠም
፪. ባዳመጣችሁት ምንባብ መሰረት በሰላም ለመኖር የማያስፈልገው
የትኛው ነው?
ሀ. ከጦርነት የፀዳ አካባቢ
ለ. ከሁከትና ብጥብጥ የተቆጠበ አንደበት
ሐ. ከራስ በላይ ንፋስ የሚል አመለካከት
መ. ከግጭት ነፃ የሆነ ሕይወት
፫. ከሚከተሉት አንዱ አብሮ ለመኖር አስፈላጊ አይደለም፡፡
ሀ. መተሳሰብ ለ. መናናቅ ሐ. መቻቻል
መ. መደጋገፍ
፬. ባዳመጣችሁት ምንባብ መሰረት ሰላምን ለማግኘት ከተሰሩ
ስራዎች ውስጥ ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. መንፈሳዊ ጉዞ ማድረግ ለ. የደራስያን ጽሁፍ
ሐ. የሰዎች ከሀገር መሰደድ መ. ለራስ ብቻ መጨነቅ

113 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፲፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፭. “ጉንጭ ማልፋት ቢሆንም ቅሉ” ሲል ምን ማለቱ ይመስላችኋል?
ሀ. ከንቱ ልፋት ለ. ጉንጭ ማሸት
ሐ. ስኬታማ ጥረት መ. ጉንጭ መምታት
፮. ለሰላም መታሰቢያነት በአገራት ባንዲራ ጎን የሚቀረፀው የምን
ምስል ነው?
ሀ. የግመል ለ. የዕርግብ ሐ. የአንበሳ መ. የንስር

ክፍል ሁለት፡- መናገር

ተግባር፡-

በሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥንድ ጥንድ በመሆን ተወያታችሁ


ከስምምነት ላይ የደረሳችሁበትን ሀሳብ በተወካያችሁ አማካኝነት
ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡ፡፡
፩. ሰላም ምንድን ነው?
፪. የሰላም መኖር ለእድገት ያለውን አስተዋፅኦ እንዴት ትገልፁታላችሁ?
፫. ሰላምን ማስጠበቅ የማን ሀላፊነት ይመስላችኋል?
፬. በአንድ ሐገር ሰላም ከሌለ ተጎጅዎች እነማን ይመስሏችኋል?

ክፍል ሶስት፡- ንባብ

ሰላም ለዕድገታችን

ቅድመ ንባብ
፩. ለሰላም እጦት ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮችን ዘርዝሩ፡፡
፪. የሰላም ዕጦት በአንድ ሀገር ላይ ምን አይነት ጉዳት
ያለው ይመስላችኋል?
፫. ከዚህ በታች ያለውን ስዕል አይታችሁ ምን እንደተረዳችሁ
ግለፁ፡፡
114 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፲፬
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ሰላም ለዕድገታችን

ሰላም የሕይወት ዋስትና የእድገት መሰረት ነው፡፡ የአንድነት፣


የፍቅርና የደስታ ምንጭም ነው፡፡ ሰላም እያንዳንዱ ጤናማ ሰው
ምንጊዜም በየትም ቦታ ሆኖ የሚመኘው ነው፡፡ ሰላምና እፎይታ
ያላጀበው ኑሮ መሰረቱ የተናጋ ነው፡፡ ውጤቱም ለፖለቲካ ቀውስ፣
ለኢኮኖሚ ድቀትና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የሚዳርግ ነው፡፡
ከዚህ ውጭ ለትውልድ የሚተርፍ ጠቃሚ ነገር የለውም፡፡

ሰላም ለህብረተሰብ ኑሮ ዋልታና ማገር ነው፡፡ በመሆኑም ሰርቶ


ለመኖር ሰላም፤ ወጥቶ ለመመለስ፣ ተወልዶ ለማድግ፣ ተምሮ
ለሀገርና ለወገን ቤዛ ለመሆን ሰላም፣ በአጠቃላይ የአዕምሮ እፎይታና
የመንፈስ እርካታ አግኝቶ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ግኝቶች እየተጠቀሙ
እድገትን በማፋጠን ረገድ ሰላም ወደር የለሽ ሚና ይጫወታል፡፡
በተለይ ሰፊው ህዝብ ከጦርነት ይልቅ ሰላምን ይሻል፤ ምክንያቱም
በማንኛውም ጊዜ በሚቀሰቀስ ችግር ግንባር ቀደም ተጠቂ ሆኖ ጉዳት
የሚደርስበት በመሆኑ ነው፡፡
115 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፲፭
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
• በምንባቡ መሰረት “ሰላም የህይዎት ዋስትና ነው” ሲባል ምን
ማለት ነው?
• ሰላም ሲደፈርስ ምን ምን ችግሮች የሚፈጠሩ ይመስላችኋል?

በሌላ በኩል ደግሞ ሰላም ሲደፈርስ ጦርነቶችና የዕርስ በዕርስ


ግጭቶች ይፈጠራሉ፡፡ አምራቹ ዜጋ በጦርነት እንዲሰለፍ
ይደረጋል፡፡ሀገሪቱ ያፈራችውም ጥሪት ለጦርነት መሳሪያ መግዣ
ይውላል፡፡ ከዚህም የተነሳ ሰፊው ሕዝብ በተጎሳቆለ ህይወት ውስጥ
እንዲኖር ይገደዳል፡፡ ጦርነትን የሚጭሩ ወይም የሚቀሰቅሱ ኃይሎች
ከሰላምና ከዲሞክራሲ ይልቅ ጦርነትን በማስቀደም ጥቅማቸውን
ያሳድዳሉ፡ የሚያቀጣጥሉት ጦርነት ግን ይህ ነው የማይባል
የሕይወትና የንብረት ጥፋት የሚያስከትል መሆኑን ይዘነጋሉ፡፡

በሀገሮች መካከል ጦርነት ሲኖር ተጠቂው ሰፊው ሕዝብ መሆኑ


እርግጥ ነው፡፡ በመሆኑም አስገዳጅ ሁኔታ ካላጋጠመው በስተቀር
ጦርነትን የሚናፍቅ ሕዝብ የለም፡፡ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ
ያለው ፍላጎት በአገሪቱ ሙሉ ለሙሉ ሰላም ሰፍኖ በህዝብ ፈቃደኝነት
አንድነቷ የፀና፣ ፍትህና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ማየት
ነው፡፡ ፍትህና እኩልነት በሀገራችን ሲሰፍን የጋራ ችግሮቻችንን
በመቀራረብ፣ በመግባባትና በውይይት በመፍታት ለሀገራችን ዘላቂና
አስተማማኝ ሰላም ለመፍጠር እንደሚቻል ይታመናል፡፡ ለዚህ ዓላማ
ግብ መምታት የአንድ ወገን ጥረት ብቻ ሳይሆን የሁላችንንም ጥረት
የሚጠይቅ ጉዳይ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡

ያለ ሰላም ወጥቶ መግባት፣ ወልዶ መሳም፣ ነግዶ ማትረፍ፣ ዘርቶ


መቃም ወዘተ. አይታሰብምና እያንዳንዱ ዜጋ ለሰላም ዘብ መቆም
ይኖርበታል፡፡
(ከቀድሞው የ8ኛ ክፍል የአማርኛ መማሪያ መፅሀፍ
ለማስተማሪያነት ተሻሽሎ የቀረበ)
116 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፲፮
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
አንብቦ መረዳት

ተግባር አንድ፡-

የሚከተሉትን ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት ትክክል ከሆኑ “እውነት”


ስህተት ከሆኑ ደግሞ “ሐሰት” በማለት መልሱ፡፡

፩. የአንድ ሀገር እድገት የሚረጋገጠው ሰላም ሲኖር ብቻ ነው፡፡


፪. ሁልጊዜም ሰላም ሊገኝ የሚችለው ተመራማሪዎች በሚያደርጉት
ጥናትና ምርምር ነው፡፡
፫. ፍትህና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ማየት የሕዝብ ምኞት
ነው፡፡
፬. አስተማማኝ ሰላም ዘላቂነት ያለውና በሕዝብ በጎ ፈቃደ ሊፈጠር
የሚችል አይደለም፡፡
፭. ጦርነት ሁልጊዜ አስከፊ ገፅታ ነው ያለው ማለት አይቻልም፡፡
፮. በሀገራት መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶች ከህዝብ መጠላላት የመነጩ
አይደሉም የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡
፯. ማንኛውም ሕዝብ ጦርነትን አይደግፍም፡፡
፰. ጦርነት ባለበት ዲሞክራሲ፣ ዲሞክራሲ ባለበት ጦርነት
አይታሰብም፡፡
፱. ከሰላም የተሻለ ኑሮ ሲገኝ፤ ከጦርነት ግን የሚገኘው እልቂት፣
ፍጅት፣ ረሀብና እርዛት ነው፡፡
፲. “ጦርነትን ለማስወገድ ለጦርነት ጆሮህን አትስጥ” የሚለው አባባል
ትክክል ይመስላል፡፡

117 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፲፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ተግባር ሁለት፡-

ለሚከተሉት ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት ትክክለኛውን መልስ


ምረጡ፡፡
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ሰላምን በተመለከተ ትክክል የሆነው የቱ
ነው?
ሀ. ሰላም የፍቅርና የደስታ ምንጭ ነው፡፡
ለ. ሰላም የሕይወት ዋስትና ነው፡፡
ሐ. ሰላም የዕድገት መሰረት ነው፡፡
መ. ሁሉም መልስ ነው።
፪. በምንባቡ አንቀፅ አንድ ላይ “ሰላምና እፎይታ ያላጀበው ኑሮ
መሰረቱ የተናጋ ነው” ሲል ምን ማለቱ ነው?
ሀ. የተረጋጋ ለ. የተስተካከለ ሐ. የተቃወሰ
መ. የተደላደለ
፫. በአንድ ሀገር ሰላም ሲደፈርስ ምን ይደረጋል።
ሀ. አምራቹ ዜጋ ለጦርነት እንዲሰለፍ ይደረጋል
ለ. የህዝቡ ኑሮ ይሻሻላል።
ሐ. ፍትህና እኩልነት ይሰፍናል።
መ. ሰርቶ መለወጥ ቀላል ይሆናል።
፬. የኢትዮጵያ ህዝብ በአሁኑ ወቅት ያለው ፍላጎት-------------ነው፡፡
ሀ. ልማት ለ. ጦርነት ሐ. እድገት መ. ሀናሐ መልስ ናቸው
፭. ጦርነት ---------------------------------ነው፡፡
ሀ. ፀረ-እድገት ለ. ፀረ-ሕዝብ ሐ. ፀረ-ሰላም
መ. ሁሉም

118 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፲፰


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፮. በምንባቡ አንቀፅ አራት ላይ “ፍትህና እኩልነት የሰፈነባት
ኢትዮጵያን ማየት” ሲል ምን ማለቱ ነው?
ሀ. ከአድልዎ የፀዳች
ለ. በዕድገት ያዘገመች
ሐ. በድህነት የተራቀቀች
መ. በቴክኖሎጂ የበለፀገች
፯. በምንባቡ ሊተላለፍ የተፈለገው መልዕክት ምንድን ነው?
ሀ. ጦርነት ለሀገር እድገት ወሳኝ መሆኑን
ለ. ሰላም ለሀገር ብልፅግና የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን
ሐ. ያለጦርነት ሰላም ሊሰፍን የማይችል መሆኑን
መ. ጦርነት ከሰላም የሚመነጭ መሆኑን

ተግባር ሶስት

“ሰላም” በሚል ርዕስ የቀረበውን ግጥም በደንብ አንብቡና መልዕክቱን


በአንድ አንቀፅ ፅፋችሁ ለመምህራችሁ አሳዩ፡፡

ሰላም
አንዱ ለፀሎተ ውዳሴው፤
ሌላው ለፍሬ ከርስኪ ጉባዬው፤
ደሞ ሌላው …  ለነገር ማጣፈጫ፤
ለፈራጅ አዕምሮ መቀጣጫ፤
ለአምባ-ገነን ሥልጣን መጨበጫ፤
ስንቱ ለከንቱ በከንቱ ያነሳሻል፤
አንስቶ …. ክቦ … ክቦ … ይጥልሻል፡፡

ከልጅነቴ ጀምሮ የምሰማት፤


ልጅ፣ ሽማግሌው የሚወዳት፤
የማትለወጥ ጣፋጭ ቃል፤
119 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፲፱
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
“ሰላም” የምትባል፤
ትርጉሟ ጠፍቶብኛል፡፡
እባካችሁ የገባችሁ አስረዱኝ፤
ሰላም ምንድን ናት ንገሩኝ።

በኢራን፣ በኢራቅ፣ በጋዛ ሠርጥ፣ ካምፑቺያ፤


ኒኳራጓ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ናሚቢያ፤
በሰሜን ሕንድ፣ በአፍጋኒስታን፣ በኢትዮጵያ፤
ያለሽ እናት፣ ያለህ ወገን፤
ያለህ ሕፃን፤
ሰላም ምን ማለት ነው ንገረኝ፤
ዋጋዋ ምን ያህል ነው አስረዳኝ፤
አንተም የአውሮፓው ሰው ንገረኝ፤
ስንት ነፍስ፣ ስንት ሀብት፣ ስንት ጥይት ነው፤
ሰላምን ገዝቶ ለማቆየት ‘ሚከፈለው?
(ከታደሰ ብሩ፣ ሕዳር 1982)
ተግባር አራት፡-
ለሚከተሉት ጥያቄዎች በግጥሙ መሰረት ትክክለኛውን መልስ
ምረጡ፡፡
፩. የሰላም ዋጋዋ ስንት ነው?
ሀ. በሚሊዮን የሚቆጠር ነው።
ለ. እልፍ ነው።
ሐ. በገንዘብ የሚተመን አይደለም።
መ. በገንዘብ መተመን ቀላል ነው።
፪. የሰላም መኖር አስፈላጊነቱ ለማን ነው?
ሀ. ለእኔ ለ. ለአንተ ሐ. ለአንቺ መ. ለሁላችንም

120 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፳


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፫. ገጣሚው ከልጅነቱ ጀምሮ ይሰማት የነበረችው ቃል ምንድን ናት?
ሀ. እኩልነት ለ. ሰላም ሐ. ዲሞክራሲ መ. ፍትሃዊነት
፬. ሰላምን አንግሶ ለማቆየት የሚያስፈልገው ምንድን ነው?
ሀ. ገንዘብ ለ. ጤና ሐ. ጊዜ መ. መልስ የለም
፭. ሰላምን ማስፈን የሚችለው ማን ነው?
ሀ. ግለሰብ ለ. ማህበረሰ ሐ. መንግስት መ. ሁሉም
፮. በግጥሙ ሁለተኛ ስንኝ ላይ “ፍሬከርስኪ” የሚለው ቃል ትርጉሙ
ምንድን ነው?
ሀ. እርባና ቢስ ለ. ቁምነገር አዘል ሐ. ጠቃሚ ነገር
መ. ፍሬ ነገር

ክፍል አራት፡- ጽሕፈት


ተግባር አንድ፡-

የሚከተሉትን ሥርዓተ ነጥብ ነክ ጥያቄዎች እንደ አጠያየቃቸው


መልስ ስጡ፡፡
፩. የመስሪያ ቤት ደብዳቤ ስንፅፍ መለያ ቁጥሮችንና ዓመተ
ምህረትን ለመለየት የምንጠቀምበት ስርዓተ ነጥብ የትኛው ነው?
ሀ. ቅንፍ ለ. ነጠላሰረዝ ሐ. እዝባር
መ. ሁለት ነጥብ
፪. ትክክለኛውን የሥርዓተ ነጥብ አጠቃቀም የተከተለው ዓረፍተነገር
የትኛው ነው?
ሀ. “ዛሬ ትምህርት እንዴት ነበር?” አለው አባት “በጣም ጥሩ
ነበር፡፡” ሲል ልጅ መለሰ፡፡
ለ. “ዛሬ ትምህርት እንዴት ነበር አለው?” አባት “በጣም ጥሩ
ነበር፡፡” ሲል ልጅ መለሰ፡፡

121 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፳፩


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ሐ. “ዛሬ ትምህርት እንዴት ነበር!” አለው አባት “በጣም ጥሩ
ነበር” ሲል ልጅ መለሰ፡፡
መ. “ዛሬ ትምህርት እንዴት ነበር?” አለው አባት በጣም
“ጥሩ” ነበር ሲል ልጅ መለሰ፡፡
፫. ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ቃላት ተከታትለው ሲመጡ ለመለየት
የምንጠቀመው ሥርዓተ ነጥብ የትኛው ነው?
ሀ. ድርብ ሰረዝ ለ. ነጠላ ሰረዝ ሐ. ጥያቄ ምልክት
መ. ቅንፍ
፬. ሊቁ እንዲህ ብሏል፤ የማውቀው አለማወቄን ነው፡፡ በዚህ ዓረፍተ
ነገር ውስጥ በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ የሚገባው ሀሳብ የትኛው ነው?
ሀ. እንዲህ ብሏል ለ. ሊቁ እንዲህ ብሏል
ሐ. አለማወቄን ነው መ. የማውቀው አለማወቄን ነው
፭. ኤልዳና በትምህርቷ ጎበዝ ናት---------ሆኖም ትበጠብጣለች፡፡ በባዶ
ቦታው የሚገባው ስርዓተ ነጥብ የትኛው ነው?
ሀ. ፣ ለ. « » ሐ. ፤ መ. …
ተግባር ሁለት፡-
ከሚከተሉት ስርዓተ ነጥቦች መካከል ተገቢ የሆኑትን መርጣችሁ
በአንቀፁ ውስጥ ያሉትን ቁጥሮች ተኩ፡፡

አራት ነጥብ (፡፡) ድርብ ትዕምርተ ጥቅስ (« »)

ነጠላ ሰረዝ (፣) ነጠላትዕምርተ ጥቅስ (‘ ‘)

ድርብ ስረዝ (፤) ጥያቄ ምልክት (?)

ቃለ አጋኖ (!) ሁለት ነጥብ ከሰረዝ (፡-)

122 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፳፪


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ጥያቄ፡- ፩. 1 ጥበቡ በለጠ 2 ድንቅ ተማሪ ነው 3 የዕውቀት
ይበልጣልማ አይነገርም 4 1 ሲል መምህሩ ተናገረ 5

ጥያቄ፡- ፪. የክብር እንግዳው ንግግራቸውን ቀጥለዋል 1 2


ሀገር ከባለሀገሩ ተለይታ እንዴት መታየት ትችላለች 3 4
ሀገሬ ለእኔ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን እኔ ለሀገሬ ምን አደረኩላት
4 እንደሚባለው 5 እያንዳንዱ ዜጋ ራሱን ሊጠይቅና የዜግነት
ግዴታውን ሊወጣ ይገባል 6 2

ተግባር ሶስት፡-
በ “ሀ” አምድ ስር ላሉ ስርዓተ ነጥቦች በ “ለ” አምድ ስር ካሉት
አቻቸው ጋር አዛምዱ፡፡
“ሀ” “ለ”
፩. አንድ ነጥብ (.) ሀ. የቃለ አጋኖ
ምልክት
፪. ሁለት ነጥብ (፡) ለ. የጥቅስ ምልክት
፫. ትዕምርተ አንክሮ (!) ሐ. ይዘት
፬. እዝባር (/) መ. አቆልቋይ
፭. ኖዑስ ሰረዝ (-) ሠ. ቃልን ከቃል ይለያል
፮. እሩይ (=) ረ. የኮከብ ምልክት
፯. ረድፍ (***) ሰ. ወይም
፰. አብይ ሰረዝ (–) ሸ. እኩል ይሆናል
፱. ቅንፍ ( ) ቀ. ጥምር ቃላትንለማመልከት
፲. ትዕምርተ ስላቅ (i) በ. እስከ
ተ. ምፀትን፣ ማሾፍንና
ስላቅን ያመለክታል

123 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፳፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል አምስት፡- ቃላት
አውዳዊ ፍች
ተግባር አንድ፡-
በሚከተሉት ዓረፍተነገሮች ውስጥ ለተሰመረባቸው ቃላት አውዳዊ
ፍቺ ስጡ፡፡
፩. ሄኖክ ለእናት ሀገር ጥሪ ወደ ድንበር ገሰገሰ፡፡
፪. እሱባለው ብዕሩን አልሰጥም አለ፡፡
፫. ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሙሌት በሰላም መጠናቀቁን
አስመልክታ ለዓለም ሀገራት ደስታዋን አበሰረች፡፡
፬. ለሁሉም ነገር የሚሻለው በሕብረት መቆም ነው፡፡
፭. ስነቃል በባህርይው ተለዋዋጭ ነው፡፡
፮. በሥርዓት የሚሰደሩ ድምፆች ስብስብ ቃል ይባላል፡፡

ተግባር ሁለት፡-
የሚከተሉትን ቃላት ተጠቅማችሁ ዓረፍተነገር መሰርቱ፡፡
፩. ባህል ፮. ፋይዳ
፪. ጠላት ፯. ሀሴት
፫. ንዋይ ፰. ሙስና
፬. አሸን ፱. ዋና
፭. አዛውንት ፲. አባይ

ተግባር ሶስት፦
የሚከተሉትን ቃላት መዝገበ ቃላት ተጠቅማችሁ ፍቻቸውን ስጡ፡፡
፩. ተደራሲ ፮. ሕፀፅ
፪. ታዳሚ ፯. ምንዳ
፫. አብነት ፰. አልፋ
፬. ፋና ፱. ኩታገጠም
፭. በየነ ፲. አደብ
124 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፳፬
አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ክፍል ስድስት፡- ሰዋስው


ዓረፍተ ነገር
በውስጣቸው ከሚይዙት የግስ ብዛት አንፃር በሁለት ይከፈላሉ፡፡
፩. ነጠላ ዓረፍተ ነገር፡- አንድ ግስ ብቻ ያለው ዓ.ነገር ነጠላ ዓ.ነገር
ተብሎ ይጠራል፡፡
ምሳሌ፡- አልማዝ ጫማና ቦርሳ ገዛች፡፡
ህፃን ልጅ ወተት ይወዳል፡፡
ልጁ መጣ፡፡
፪. ውስብስብ ዓረፍተ ነገር፡- ከአንድ በላይ ግስ ያለው ዓ.ነገር
ውስብስብ ዓ.ነገር ይባላል፡፡
ምሳሌ፡- ቀለሙ እያወራ ይበላል፡፡
ሜላት ስለምትፈራ ችግሯን አትናገርም፡፡
ፈትያ ወንደሟ ወደውጭ ሀገር ስለሄደ አዘነች፡፡

ተግባር አንድ፡-
የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች ነጠላ እና ውስብስብ ዓረፍተ ነገር
በማለት ለዩ፡፡
፩. አብዱ ዛሬ ብዙ ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡
፪. ጨዋታውን ፊት ለፊት በማየቴ ደስ አለኝ፡፡
፫. ዳናዊት እስር ቤት ሄዳ እህቷን ጠየቀች፡፡
፬. ቀለሙ ፊቱን ታጠበና ቁርሱን በላ፡፡
፭. አቤል ቁልፍ ወስዶ በሩን ከፈተ፡፡
፮. እውቀት ከጥበብ ጋር ቤተመፃሕፍት ሄደች፡፡
፯. አቤኔዘር የክፍል ስራውን ሰርቶ አሳረመ፡፡
፰. ወንድሙ ከመኝታው ተነስቶ አልጋ አነጠፈ፡፡
፱. የያፌት ወንድም ቁምሳጥኑን ከፈተ፡፡
፲. ፍቅር ዛሬ ጠዋት ትምህርት ቤት ሄደ፡፡

125 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፳፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ተግባር ሁለት፡-
አምስት ተራና አምስት ውስብስብ ዓረፍተነገር ፃፉና ለመምህራችሁ
አሳዩ፡፡

126 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፳፮


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ማጠቃለያ
በዚህ ምዕራፍ ሥርዓተ ነጥብ በወረቀት ላይ የሰፈረ ሀሳብ መልዕክቱ
ግልፅ ሆኖ እንዲተላለፍ የሚያደርግ እንደሆነ አይተን የተለያዩ
የስርዓተ ነጥብ አይነቶችን ጠቀሜታ ለመረዳት ችለናል፡፡

በመጨረሻም አንድ ግስ ብቻ ያለው ዓረፍተ ነገር ነጠላ ዓረፍተ ነገር


ሲባል ከአንድ በላይ ግሶችን ያካተተ ዓረፍተ ነገር ደግሞ ውስብስብ
ዓረፍተ ነገር እንደሚባል ተረድተናል፡፡

የክለሳ ጥያቄ
ተግባር አንድ፡
ከሚከተሉት ሥርዓተ ነጥቦች መካከል ተገቢ የሆኑትን መርጣችሁ
በአንቀፁ ውስጥ ባሉት ክፍት ቦታዎች አስገቡ፡፡

ድርብ ትዕምርተ ጥቅስ ነጠላ ሰረዝ


አራት ነጥብ ጥያቄ ምልክት
ድርብ ሰረዝ ነጠላ ትዕምርተ ጥቅስ
ሁለት ነጥብ ሁለት ነጥብ ከሰረዝ

------------ የተወለደባት ሀገር ላንድ ሰው ባንድ ቃል ሕይወቱ ናት-


----------ስለዚህ ድንበሯን የሚደፍር---------- መሬቷን የሚነጥቅና
የሚቃወም ጠላት ሲነሳ ወይም ሲመጣ ማን ዝም ይላል----------
ዜጎቿ ይቆሙላታል---------- ከምድሯ የተገኘውን ፍሬ በልተውና
ውሀዋን ጠጥተው የሚኖሩት ሁ በጋራ ይጠብቋታል---------- ያገር
ህልውና ሲከበር ህዝብ ይሰራል------------ ያመርታል---------
በነፃነትም ይኖራል፡፡-------
ተግባር ሁለት፡-
ሶስት ሶስት ነጠላ እና ውስብስብ ዓረፍተነገር ፃፉ፡፡

127 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፳፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ምዕራፍ ዘጠኝ

አየር ንብረት

ከምዕራፉ የሚጠበቁ ውጤቶች፣ ይህንን ምዕራፍ ተምራችሁ


ከጨረሳችሁ በኋላ፡-
• የጽሁፉን ሀሳብ አዳምጣችሁ ትገመግማላችሁ፤
• የአየር ንብረትን ምንነት ትገልፃላችሁ፤
• የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ውጤት
ታብራራላችሁ፤
• ለተለያየ ዓላማ ታነባላችሁ፡፡

128 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፳፰


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል አንድ፡- ማዳመጥ

ቅድመ ማዳመጥ
፩. ከፋብሪካዎች የሚወጡ ጭሶች ለአየር ንብረት ለውጥ
እንዴት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ይመስላችኋል?
፪. ሰዎች አካባቢያቸው እንዳይበከል ካደረጉ ምን ምን ጥቅም
የሚያገኙ ይመስላችኋል?
፫. የአካባቢ ብክለትና የአየር ንብረት ለውጥ ያላቸው ግንኙነት
ምንድን ነው?
፬. ስዕሉን በማየት የተረዳችሁትን ግለፁ፡፡

አዳምጦ መረዳት፡-

ተግባር አንድ፡-

የሚከተሉትን ጥያቄዎች ባዳመጣችሁት ምንባብ መሰረት በጽሁፍ


መልሱ፡፡
፩. የሰው ልጅ ከሚኖርበት አካባቢ ጋር ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?
፪. የተፈጥሮ ሀብቶች የምንላቸው እነማን ናቸው?

129 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፳፱


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፫. የአካባቢ ብክለት ጉዳትን በቶሎ የምንገነዘበው አይደለም ሲባል ምን
ማለት ነው?
፬. የአየር ብክለት ከገጠርና ከከተማ በየትኛው ጎልቶ ይታያል? ለምን?
፭. የኦዞን ሽፋን መሳሳት በከባቢ አየር ላይ የሚያስከትለው ጉዳት
ምንድን ነው?
፮. ውሃ ሲበከል ጉዳት የሚደርስባቸው አካላት እነማን ናቸው?
፯. ብዙዎቹ ፋብሪካዎች ከወንዝ አጠገብ የሚገነቡት ለምንድን ነው?

ክፍል ሁለት፡- መናገር

ተግባር አንድ፡-

በሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዬች ላይ ሶስት ሶስት ሆናችሁ በመወያየት


የደረሳችሁበትን የመፍትሄ ሀሳብ በተወካዮቻችሁ አማካኝነት
ለክፍል ጓደኞቻችሁ በንግግር አቅርቡ፡፡
፩. የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ ከህብረተሰቡ የሚጠበቀው
ምንድን ነው?
፪. አካባቢያቸውን ከብክለት ለመታደግ ሰዎች ምን ማድረግ
ይጠበቅባቸዋል?
፫. የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት የበለጸጉ ከሚባሉ ሀገራት
ምን ይጠበቃል? ከታዳጊዎችስ?

ተግባር ሁለት
ለሚከተሉት ቃላት የመዝገበ ቃላዊ ፍች ስጡ፡፡
ሀ. በከለ ለ. ሸፈነ ሐ. መሸሸት
መ. ጠንቅ ሠ.ዝቃጭ

130 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፴


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

የክርክር መመሪያ
ክርክር አንድና ከዚያ በላይ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ተቃራኒ አስተሳሰብ
ባላቸው ሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ቡድኖች መካከል የሚካሄድ ሙግት፣
ፍትጊያና ሰጣ ገባ ነው፡፡ ክርክር ሲካሄድ የተሟጋቾችን ሀሳብ መዝነው
ፍርድ የሚሰጡ ዳኞች ይኖራሉ፡፡ ተከራካሪዎች ደግሞ ደንብና መመሪያዎችን
ጠብቀው በቂ ዝግጀት አድርገው ይቀርባሉ፡፡
፩. የክርክር ዝግጀት
• የመከራከሪያ ርዕሰ ጉዳይ መለየትና መወሰን
• ርዕሱን በሚመለከት ከተለያዩ መረጃ ምንጮች መረጃ መሰብሰብ
• ከተሰበሰቡት መረጃዎች ለክርክሩ የሚመጥኑትን መምረጥ
• ክርክሩ የሚቀርብበትን ቅደም ተከተል መወሰን
• ለክርክር ከመቅረባችን በፊት በቂ ልምምድ ማድረግ
• በክርክሩ ላይ አለባበስንና ንፅህናን ጠብቆ መገኘት
• በስርዓትና ጨዋነት በተሞላበት መንገድ ዝግጁ ሆኖ መቅረብ
፪. የክርክር አቀራረብ
• ራስንና የመከራከሪያ ርዕሱ ለአድማጮች ማስተዋወቅ
• በተዘጋጁት መሰረት በልበ ሙሉነትና በተረጋጋ ሁኔታ በቅደም
ተከተል በቃል ማቅረብ
• ክርክሩን አስፈላጊ በሆኑ አካላዊ እንቅስቃሴዎች ማጀብ
• ተቃዋሚዎች የሚያነሱትን ሀሳብ በትክክል በመመዝገብ ተገቢ
ግብረ መልስ መስጠት
• ለክርክሩ የተመደበውን ጊዜ በአግባቡ መጠቀምና ማክበር
• ከመከራከሪያ ርዕሰ ጉዳዩ አለማፈንገጥ
• በመጨረሻም ተመልካችን ማመስገን

ተግባር ሁለት፡-

አራት አባላት ያለው ቡድን በመመስረት ዳኛ ሰይማችሁ ከሚከተሉት ርዕሰ


ጉዳዮች በአንዱ ክርክር አካሂዱ፡፡

፩. ፋብሪካዎች በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ከሚያሳድሩት አሉታዊ ተጽዕኖ


አንፃር መኖር አለባቸው ወይስ የለባቸውም?
፪. ለዓለማችን የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው ሰው
ሰራሽ ወይስ ተፈጥሯዊ ምክንያት ነው?

131 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፴፩


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል ሶስት፡- ንባብ

የአየር ንብረት ለውጥና ችግሮቹ

ቅድመ ንባብ
፩. የአየር ንብረት ለውጥ እንዴት የሚከሰት ይመስላችኋል?
፪. ስዕሉንና የምንባቡን ርዕስ በማየት ፅሁፉ ስለምን እንደሚናገር
ገምቱ፡፡

የአየር ንብረት ለውጥና ችግሮቹ

የአየር ሁኔታ በየቀኑና በየሳምንቱ የተመዘገበን የሙቀት፣ የደመና፣


የዝናብ፣ የንፋስና የቅዝቃዜ ወዘተ. ሁኔታዎችን ለመግለጽ
የምንጠቀምበት አገላለጽ ሲሆን የአየር ንብረት ደግሞ በአንድ አካባቢ
ለረጅም ጊዜ የተመዘገበ የአየር ሙቀት፣ የዝናብ መጠን፣ የአየር
እርጥበትና የንፋስ ፍጥነት ወዘተ. የመሳሰሉት አማካይ ውጤት
ነው፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁ ለበርካታ ዓመታት የተመዘገበ
የአየር ንብረት መቀየርን የሚያመለክት ነው፡፡

132 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፴፪


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
የአየር ንብረት ለውጥ ለረዥም ዓመታት የተመዘገቡ አጠቃላይ
የእርጥበት፣ የቅዝቃዜ፣ የሙቀት፣ የንፋስ አቅጣጫ የአየር ግፊት
ወዘተ የመሳሰሉት ባህርያት መለወጥ ሲሆን፡፡ በረጅም ጊዜ የሚከሰት
ነው፡፡ ሰፊ መልክዓ ምድራዊ ሽፋንም ያለው ነው፡፡ በሌላ በኩል
የአየር ጠባይ ለውጥ የምንለው በቀናትና በወራት የሚቀያየር የንፋስ፣
የዝናብ፣ የሙቀትና የቅዝቃዜ ለውጥ ሲሆን ለውጡም የሚገለጸው
በአነስተኛ መልክዓ ምድር ላይ ነው፡፡

ለአየር ንብረት ለውጥ ምክንያቶቹ በከባቢ አየር ውስጥ የሚገኙ


ሙቀት አማቂ ጋዞች ከመጠን በላይ መከማቸታቸው ነው፡፡ የሙቀት
አማቂ ጋዞችን ክምችት ያባባሰውና ለአየር ንብረት ለውጥ ትልቅ
አስተዋጽኦ ያደረገው የሰው ልጅ የድንጋይ ከሰልን፣ የተፈጥሮ
ነዳጅንና ጋዝን በሰፊው በመጠቀሙ ምክንያት ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ
የተባለውን ጋዝ ወደ አየር በመልቀቅ ቀድሞ የነበረውን የከባቢ አየር
ተፈጥሯዊ ሁኔታ እንዲዛባ ምክንያት በመሆኑ ነው፡፡ ስለሆነም የሰው
ልጅ አሁን እየገጠመው ያለው ፈተና በሰው ሰራሽ ምክንያት በከባቢ
አየር ውስጥ ባሉ የሙቀት አማቂ ጋዞች ለውጥ ሳቢያ እየተከሰተ
ያለው የአየር ንብረት ለውጥ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ተፈጥሮ በራሷ
ለአየር ንብረት ለውጥ አስተዋጽዖ አታደርግም ማለት አይደለም፡፡

በተጨማሪም እሳተ ገሞራና ተፈጥሯዊ የሰደድ እሳትም ለአየር


ንብረት ለውጥ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ያደርጋሉ፡፡ ለአየር ንብረት
ለውጥ መንስኤ የሆኑ ሁነቶች በተከሰቱበት አካባቢ ብቻ ተወስነው
የሚቀሩ ሳይሆን ድንበር ተሻጋሪዎችም ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት
ለአየር ንብረት ለውጥ ብዙም ድርሻ የሌላቸው የታዳጊ ሀገራት
ህዝቦች የበለጸጉ ሀገራት ሲያከማቹ በኖሩት የሙቀት አማቂ
ጋዝ ጥርቅም ሳቢያ በሚከሰተው የአየር ንብረት ለውጥ ይበልጥ

133 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፴፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተጎጂዎች ናቸው፡፡

የአየር ንብረትና የአየር ሁኔታ ልዩነት ምንድን ነው?


የአየር ንብረት ለውጥ ምን ምን ችግሮች የሚያስከትል ይመስላችኋል?

የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸው ዋና ዋና ችግሮች


የግብርና መሬት መቀነስ፡- አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚተዳደረው
በግብርና መሆኑ ይታወቃል፡፡ የሕዝቧም ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ
ነው፡፡ የሕዝብ ቁጥር መጨመር ደግሞ የምግብ አቅርቦትን የሚጠይቅ
ነው፡፡ ስለዚህ የምግብ ፍላጎትን ለማሟላት ሲባል በቀጥታም ይሁን
በተዘዋዋሪ አካባቢ ላይ ተጽዕኖ ማድረሱ የማይቀር ነው፡፡ በአካባቢ
ላይ ጫና ሲደርስ ደግሞ የግብርናው ዘርፍ ምርታማነት ስለሚቀንስ
ቁጥሩ እያደገ የሚገኘውን ሕዝብ መመገብ አዳጋች ይሆናል፡፡

የመሬት መሸርሸር፡- የኢትዮጵያ መልክዓ ምድር በተፈጥሮው ተራራ፣


ኮረብታማ እንዲሁም ዝቅተኛ ቦታዎችና ሜዳዎች የሚበዙበት ነው፡
እንደሚታወቀው ታላላቅ ወንዞችና ጅረቶች መነሻቸው ከደጋማው
አካባቢ ነው፡፡ የመሬቱ አቀማመጥ ከወንዞች የፍሰት አቅጣጫ ጋር
ተዳምሮ ለአፈር መሸርሸር የተመቸ አድርጎታል፡፡ በዚህም ምክንያት
አፈሯ እየታጠበ ወደ ጎረቤት ሀገር መጓጓዙ የተለመደ ሆኗል፡፡
ለአፈር መሸርሸር ዋና ዋናዎቹ ምክንያቶች ደግሞ ወራጅ ውሃ እና
በድርቅ ወቅት በሞቃታማው አካባቢ የሚከሰተው አውሎ ንፋስ
ናቸው፡፡ እነዚህ ምክንያቶችም የአየር ንብረት ለውጥን ከማባባሳቸው
በተጨማሪ ለድርቅ መከሰት፣ ለበረሃማነት መስፋፋት፣ ለግብርና
ምርት መቀነስና ለመሳሰሉት ሁነቶች መሰረት ይሆናሉ፡፡

የሰውና የእንስሳት ጤና ችግር፡- የአየር ንብረት ለውጥ የሚፈጥረው


የጤና ችግር በሰው ዘር ላይ ብቻ አይደለም፡፡ እንደ ሰው ልጅ ሁሉ

134 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፴፬


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
የቤትና የዱር እንስሳትም የአየር ንብረት ለውጥ በሚፈጥረው ጉዳት
ተጠቂዎች ናቸው፡፡ አሁን አሁን ደግሞ በቆላማውና በበርሃማው
የሀገራችን ክፍል ተወስነው የነበሩ በሽታዎች ወደ ደጋማው አካባቢ
በመሸጋገር ችግር በመፍጠር ላይ ይገኛሉ፡፡ ለአብነት ወባና የጋንዲ
በሽታ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ውሃ መጠን መቀነስ፡- የውሃ መጠን


ማነስና የጥራት መጓደል የሰብል ምርትንና ብዝሃ ሕይወትን
ይጎዳል፡ ሀገራችንን ይበልጥ እየጎዳት የሚገኘው ምጣኔ አቅማችን
አናሳ በመሆኑና ትላልቅ ወንዞችን ጠልፎ የመጠጥ ውሃ ማቅረብ
አለመቻሉ ነው፡፡ ‹‹የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው›› የሚለው አባባልም
ከዚሁ የመነጨ ይመስላል፡፡ በአጠቃላይ የአየር ንብረት ለውጥ
በሀገር ምጣኔ ሐብታዊ ግንባታ ላይ ጉልህ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ
ይፈጥራል፡ ማህበራዊ ችግሮችን በማባባስ አለመረጋጋት፣ ስደት፣
ረሃብ፣ ጦርነትና የመሳሰሉት ሁነቶች እንዲነግሱ ያደርጋል፡፡
(ከአብክመ የአካ/የደንና የዱር እንሰሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን
ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት፣ ለማስተማሪያነት ተሻሽሎ የተወሰደ)

አንብቦ መረዳት፡-
ተግባር አንድ፡-

ባዳመጣችሁት ምንባብ መሰረት ትክክል ከሆኑ “እውነት” ስህተት


ከሆኑ ደግሞ “ሐሰት” በማለት መልሱ፡፡
፩. ተፈጥሮ በራሷ ለአየር ንብረት ለውጥ አስተዋፅኦ አታደርግም፡፡
፪. እሳተ ገሞራ እና ተፈጥሯዊ የሰደድ እሳት በአየር ንብረት ለውጥ
ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራሉ፡፡
፫. ለአየር ንብረት ለውጥ መንስኤ የሆኑ ሁነቶች በተከሰቱበት አካባቢ
ብቻ ተወስነው የሚቀሩ ናቸው፡፡

135 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፴፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፬. የኢትዮጵያ መልክዓ ምድር በተፈጥሮው ተራራ፣ ኮረብታና
ዝቅተኛ ቦታዎች የሚበዙበት ነው፡፡
፭. ከኢትዮጵያ ምንም ዓይነት አፈር ወደ ጎረቤት ሀገራት አይሄድም፡
፮. በአየር ንብረት ለውጥ ተጠቂው የሰው ዘር ብቻ አይደለም፡፡
፯. የአየር ንብረት ለውጥ በአጭር ጊዜ የሚከሰት ነው፡፡

ተግባር ሁለት፡
ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን ሆሄ በመምረጥ
መልሱ፡፡
፩. በአንቀፅ አንድ መሰረት በየቀኑና በየሳምንቱ የተመዘገበን የሙቀት፣
የደመና፣ የዝናብ፣ የንፋስና የቅዝቃዜ ወዘተ. ሁኔታዎችን ለመግለጽ
የምንጠቀምበት አገላለጽ ምን ይባላል?
ሀ. የአየር ሁኔታ ለ. የአየር ንብረት
ሐ. የአየር ፀባይ መ. የአየር ለውጥ
፪. በጽሑፉ መሰረት ለአየር ንብረት ለውጥ በምክንያትነት የሚጠቀሰው
ምንድን ነው?
ሀ. ሙቀት አማቂ ጋዞች ከመጠን በላይ መከማቸት
ለ. የድንጋይ ከሰልንና የተፈጥሮ ጋዝን በሰፊው መጠቀም
ሐ. ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ የተባለውን ጋዝ ወደ አየር መልቀቅ
መ. ሁሉም መልስ ናቸው፡፡
፫. የበለጸጉ ሀገራት ባከማቹት ሙቀት አማቂ ጋዝ ጥርቅም የተነሳ
ለአየር ንብረት ለውጡ ብዙም ድርሻ የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት
ይበልጥ ተጎጂ የሆኑት ለምንድን ነው፡፡
ሀ. ደሃ ስለሆኑና ለመከላከል ፍላጎት ስለሌላቸው
ለ. የአየር ንብረት ለውጥ ድንበር ተሻጋሪ ስለሆነ
ሐ. የአየር ንብረት ለውጡ የፈጣሪ ቁጣ ስለሆነ
መ. አየር ንብረት ጊዜውን ጠብቆ መለወጡ ስለማይቀር

136 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፴፮


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፬. እንደ ጽሑፉ ገለፃ ከሆነ እየተከሰተ ላለው የአፈር መሸርሸር
አደጋ
ዋና ምክንያቱ -------------------------- ነው፡፡
ሀ. አውሎ ነፋስ ሐ. ወራጅ ውሃ
ለ. ለም አፈር መ. ሀ ና ሐ መልስ ናቸው
፭. በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በቆላማውም ሆነ በደጋማው
የሀገራችን ክፍል ችግር እየፈጠሩ ካሉ በሽታዎች ውስጥ
የማይካተተው የትኛው ነው?
ሀ. ወባ ለ. ጋንዲ ሐ. ኤች አይቪ መ. ሁሉም
፮. ከሚከተሉት አንዱ ለበርካታ ዓመታት የተመዘገበን የአየር
ንብረት መቀየር የሚመለከት ነው?
ሀ. የአየር ሁኔታ ለ. የአየር ንብረት ለውጥ
ሐ. የአየር ንብረት መ. የዝናብ መጠን
፯. የኢትዮጵያ ታላላቅ ወንዞችና ጅረቶች መነሻቸው ከየት ነው?
ሀ. ከደጋ ለ. ከበርሀ ሐ. ከቆላ መ. ከአባይ
፰. «የአባይን ልጅ ውሀ ጠማው» ከሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር በፍች
ተመሳሳይ የሆነው የትኛው ነው?
ሀ. የተጓዥን ልጅ ውሀ ወሰደው።
ለ. የባሮን ወንዝ አውሬ ጠጣው።
ሐ. የላጭን ልጅ ቅማል በላው።
መ. የድመትን ልጅ ውሻ በላው።
፱. የዚህ ምንባብ አብይ መልዕክት ምንድን ነው?
ሀ. በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በዓለም ላይ የተለያዩ ችግሮች
እየተከሰቱ መሆኑን ማሳየት
ለ. ለአየር ንብረት ለውጥ ግንባር ቀደም ተዋናዮቹ በማደግ ላይ
ያሉ ሀገራት መሆናቸውን ማስረዳት
ሐ. የበለፀጉ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ምንም ዓይነት
አስተዋፅዖ እንደማያደርጉ ማተት እንደሚፈስ መግለፅ

137 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፴፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
መ. ውሀ ከደጋማው ቦታ በመነሳት ወደ በርሃማው ቦታ

ተግባር ሶስት

ግጥሙን በጥሞና አንብቡና ከታች የቀረበላችሁን ጥያቄዎች ትክክለኛ


ውን መልስ በመምረጥ መልሱ
ይኸው እንደ ዋዛ

ይኸው እንደዋዛ!
ተራሮች ፈለሱ
ኮረብታዎች ተወሰዱ
ውሆች ተሰደዱ
ማነን? ብንላቸው
ፈጽመው ረሱን
በ’ኛ ተሰይመው
ዛሬ ‘ኛን’ ስም ነሱን፡፡
ይኸው እንደዋዛ!
ባለበት እንዲገኝ
መሬት መች ታመነ
መሀል የነበረው
ዳርቻችን ኾነ፡፡
ይኸው እንደዋዛ!
አራሹ ሳይለግም
ሳይሳሳ ደመና
ህላዌን ድርቅ መታት
ዘር መውደቂያ አጣና፡፡
(በዕውቀቱ ስዩም፣ 2001 ዓ.ም፣ ስብስብ ግጥሞች)

፩. ግጥሙ ባለስንት አርኬ ነው?


ሀ. ሁለት ለ. ሶስት ሐ. ዘጠኝ መ. አስራ ስምንት

138 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፴፰


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፪. በግጥሙ የመጀመሪያው አርኬ ላይ “ማነን? ብንላቸው ፈፅመው ረሱን”
የተባሉት እነማን ናቸው?
ሀ. ተራሮች ለ. ውሀዎች ሐ. ኮረብታዎች
መ. ሁሉም መልስ ናቸው
፫. በግጥሙ መሰረት መሬት ያልታመነው በምንድን ነው?
ሀ. እህል ባለመቀበል ለ. ቤት መስርያ ባለመሆን
ሐ. ባለበት ባለመገኘት መ. መዝናኛ ባለመሆን
፬. ከሚከተሉት አንዱ አማርኛ ቋንቋ ከግዕዝ የተዋሰው ቃል ነው፡፡
ሀ. ህላዌ ለ. አጣና ሐ. ሳይሳሳ መ. ዳርቻ
፭. በግጥሙ መሰረት ትክክል ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. ገበሬዎች እርሻቸውን እያረሱ ነው፡፡
ለ. ሰማይ ዝናብ መስጠቱን አቁሟል፡፡
ሐ. መሬት ባለበት እየቀጠለ አይደለም፡፡
መ. የሰው ልጅ በርሃብና በችግር እየተመታ ነው፡፡
ክፍል አራት፡- ጽሕፈት
ተግባር፡-
፩. በክፍል ሶስት ላይ የቀረበውን ስዕል ከዚህ በታች ከቀረበው ጋር
በማነጻጸር ጥልቅ የሆነ ትንታኔ በጽሁፍ ስጡ፡፡
፪. የጻፋችሁትን ጥልቅ ማብራሪያ እርስ በዕርስ በመቀያየር እርማት
ተሰጣጡ፡፡

ክፍል አምስት፡- ቃላት


139 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፴፱
አማርኛ ፰ኛ ክፍል

አውዳዊ ፍች
ተግባር አንድ፡-

ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ከቀረቡት ቃላት መካከል አውድን መሰረት አድርጋችሁ


በመምረጥና ባዶ ቦታው ውስጥ በማስገባት ዓረፍተነገሩን አሟልታችሁ ፃፉ፡፡
ዳጎስ ወላፈን ሳንካ ሀገረ
ሰብዓዊ
መሻሻል አዘቦት ቤተ ምርምር ማዕረግ

፩. ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚከበሩ------------------ ክብረ በዓላት


መካከል
የሲዳማ ህዝብ የዘመን መለወጫ “ፊቼ ጨምበላላ” አንዱ
ነው፡፡
፪. የእሳቱ--------------- ዳር ያሉትን ሰዎች ሁሉ ገረፋቸው፡፡
፫. የመስሪያ ቤቱ ኋላፊ ባለፈው ዓመት ላስመዘገቡት አመርቂ
ውጤት ---------ያለ ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡
፬. የአንዲት ሀገር ማሕበራዊ ኑሮ-------------የሚችለው ሕዝቡ በትምህርት
የታነጸ ከሆነ ነው፡፡
፭. ኮቪድ 19 (ኮሮና ቫይረስ) ለሀገራችን ዕድገት -------------- ከሆኑ ጉዳዮች
አንዱ ነው፡፡
፮. በሣይንስና ቴክኖሎጂ ጥበብ የበለጸጉት ሀገሮች አሁን ከደረሱበት
የዕድገት
ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት የ------------------ ጥናታቸውን በማጠናከራቸው
ነው፡፡
፯. ሄለን በበዓላት ቀን ይቅርና ለ-----------------ቀን የምታዘጋጀው
ምግብ ጣት ያስቆረጥማል፡፡
፰. ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ያዋለው ፖሊስ የ----------ዕድገት
አገኘ፡፡
140 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፵
አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ተግባር ሁለት፡-

የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን


በመምረጥ መልሱ፡፡
፩. ሰዎች ከደረሱበት ከፍተኛ ደረጃ ለመድረስ ከተፈለገ በወጣትነት
ዕድሜ ሳሉ በስርዓትና በበጎ ምግባር -----------------ያስፈልጋል፡፡
ሀ. መታነፅ ለ. መዘጋጀት ሐ. መሰናዳት
መ. መጠበቅ
፪. ህፃኑ የፈለገው ነገር ስለተሟላለት በደስታ ------------------------፡፡
ሀ. አማረ ለ. ቦረቀ ሐ. ዘለለ መ. ለ ና ሐ
፫. መብራት በመጥፋቱ የተነሳ ከተማውን -----------------ውጦታል፡፡
ሀ. ብቸኝነት ለ. ድፍረት ሐ. ፅልመት መ. አውሬ
፬. የሰራነው ስራ ጥሩ ስለነበር ነፍሳችን----------------------አደረገች፡፡
ሀ. ሀዘን ለ. ሀሴት ሐ. ክፋት መ. ስብሰባ
፭. ሁልጊዜ አንድ ዓለማ ይኑርህ፣ ዓላማህ ግቡን እንዲመታ
ደግሞ-------------ጥረት አድርግ፡፡
ሀ. ያልተመጣጠነ ለ. ያልተደጋገመ ሐ. ያለሰለሰ
መ. ያሰለሰ
፮. የስራ ባልደረባዬ ----------------ስለሆነ ችግሬን ፊት ለፊት ከመንገር
ይልቅ ወሬ ለአለቃ ማሳበቅ ይወዳል፡፡
ሀ. መሰሪ ለ. ቀና ሐ. መልካም መ. ጥሩ
፯. የራስን የአሰራር ዘዴ ከሌሎች የአሠራር ስልት ጋር---------------
መቻል ራስን ለማስተካከል ቁልፍ መሳሪያ ነው፡፡
ሀ. ማነፃፀር ለ. ማወዳደር ሐ. ማመሳከር
መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ

141 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፵፩


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ተግባር ሶስት
በ‹‹ሀ›› ስር የቀረቡትን ያልተለመዱ ቃላት በ‹‹ለ›› ስር ከቀረቡት
ፍችዎቻቸው ጋር አዛምዱ፡፡
“ሀ” “ለ”
፩. ሐኬት ሀ. መንቀጥቀጥ
፪. ገርበብ ለ. መከልከል
፫. ስርቅታ ሐ. መባከን
፬. ማሞናደል መ. ማቃጠል
፭. መክላት ሠ. ክፋት
፮. ቅራተኛ ረ. ከፈት
፯. መዋተት ሰ. ከብት ጠባቂ
፰. መፋጀት ሸ. ማቀማጠል
ቀ. ህቅታ
በ. ማስወገድ
ክፍል ስድስት፡- ሰዋስው
ተግባር፡
የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች ነጠላ ወይም ውስብስብ ዓርፍተ ነገር
በማለት ለዩ፡፡
፩. ንግስት የገዛችው ቀሚስ ያምራል፡፡
፪. የአንዳርጋቸው እናት ከገበያ ሽንኩርት፣ቃሪያና ቲማቲም ገዙ፡፡
፫. ሰዓዳ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ናት፡፡
፬. ብርጭቆውን የሰበረው ልጅ በእናቱ ተገረፈ፡፡
፭. ከነቀምት የመጣው ሰውዬ ትናንት ወደ መቀሌ ተጓዘ፡፡
፮. ዕነኬብሮን ቆንጆ የሳሎን ውሻ አለቻቸው፡፡
፯. ሀና ያዘጋጀችው ምግብ በጣም ይጣፍጣል፡፡
፰. ሳሙኤል ከሁሉም ተማሪዎች አንደኛ በመውጣት የትምህርት
ቤቱን ዋንጫ ወሰደ፡፡
፱. ሰለሞን ባረጋ የአስር ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸነፈ፡፡
142 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፵፪
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ማጠቃለያ
በዚህ ምዕራፍ ክርክር አንድና ከዚያ በላይ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ
ተቃራኒ አስተሳሰብ ባላቸው ቡድኖች መካከል የሚካሄድ ሙግት፣
ፍትጊያና እሰጣ ገባ መሆኑን አይተናል፡፡ በመቀጠልም ያልተለመዱ
ቃላት የሚባሉት በእለት ከዕለት የቋንቋ አጠቃቀማችን ውስጥ
የማንጠቀማቸው አዳዲስ ቃላት እንደሆኑ አስታወሰና፡፡

በመጨረሻም በውስጡ አንድ ግስ ብቻ የያዘ ዓረፍተነገር ነጠላ ዓረፍተ


ነገር ሲባል ሁለትና ከዚያ በላይ ግሶችን ያካተተ ዓረፍተ ነገር ውስብስብ
ዓረፍተነገር እንደሚባል ተምረናል፡፡

የክለሳ ጥያቄ
ተግባር፡-
ለሚከተሉት ያልተለመዱ ቃላት መዝገበቃላዊ ፍች ስጡ፡፡

፩. ጨመተ
፪. አዋይ
፫. እኩይ
፬. አክንባሎ
፭. በትር
፮. ወረንታ
፯. ጦማሪ
፰. ዐጸድ

143 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፵፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

ምዕራፍ አሥር

ተውኔት

ከምዕራፉ የሚጠበቁ ውጤቶች፣ ይህንን ምዕራፍ ተምራችሁ


ከጨረሳችሁ በኋላ፡-
• የጽሁፉን ሀሳብ አዳምጣችሁ ትተነትናላችሁ፤
• ስለ ተውኔት ምንነት ትንታኔ ትሰጣላችሁ፤
• የተውኔት አለባውያንን ትዘረዝራላችሁ፤
• በጽሁፍ ውስጥ የተለያዩ አያያዦችን ትጠቀማላችሁ፡፡

144 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፵፬


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል አንድ፡- ማዳመጥ
ለሁሉም ጊዜ አለው!

ቅድመ ማዳመጥ
፩. ‹‹ለሁሉም ጊዜ አለው›› በሚል ርዕስ በተጻፈ ተውኔት ምን ምን
ርዕሰ ጉዳዮች የሚዳሰሱ ይመስላችኋል?
፪. ከአሁን በፊት በሬድዮ ካዳመጣችሁት ወይም በቴሌቪዥን
ከተመለከታችሁት ወዘተ. ተውኔት ገጸባህሪያት በመጥቀስ እንዴት
ማስታወስ እንደቻላችሁ ተናገሩ፡፡
፫. ስዕሉን አይታችሁ የተረዳችሁትን ነገር ግለፁ፡፡

አዳምጦ መረዳት
ተግባር አንድ፡-
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በተወኔቱ መሰረት በቃል መልሱ፡፡
፩. ከተወኔቱ የተማራችሁት ምንድን ነው?
፪. መዓዛ በማትያስ የተናደደችው ለምንድን ነው?

145 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፵፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፫. አበበች መዓዛን “ለሰው መድሐኒቱ ሰው ነው ስትላት”፣ “አጥፊውም
እኮ ሰው ነው” ያለቻት መዓዛ ምን ለማለት ፈልጋ ነው?
፬. አበበች መዓዛን ይቅርታ መጠየቋ አግባብ ነው ብላችሁ ታምናላችሁ?
እንዴት?

ተግባር ሁለት፡-
ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን ሆሄ በመምረጥ
መልሱ፡፡
፩. የዚህ ተውኔት መቼቱ የት ነው?
ሀ. ቤት ውስጥ ምሳ ሰዓት ላይ።
ለ. መዝናኛ ቦታ ረፍት ሰዓት ላይ።
ሐ. ትምህርት ቤት ግቢ ረፍት ሰዓት ላይ።
መ. ትምህርት ቤት ግቢ ምሳ ሰዓት ላይ።
፪. መዓዛ “ማስተዋል የጎደላቸው ሰዎች የሰውን ሕይወት ከመጉዳት
አይመለሱም” ያለችው ምን ለማለት ፈልጋ ነው?
ሀ. የሰው ፍላጎት የማይረዱ ሰዎች ሰውን አይጎዱም
ለ. ነገሮችን ማመዛዘን የማይችሉ ሰዎች፣ ለጓደኞቻቸው ጠንቅ
ናቸው
ሐ. የማመዛዘን አቅም የሌላቸው ሰዎች፣ ሰውን ሊጎዱ
አይችሉም
መ. የሰውን ህይዎት ለመጉዳት ማስተዋል አስፈላጊ ነው።
፫. አበበችና መዓዛ የስንተኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው?
ሀ. የሰባተኛ ለ. የአስረኛ
ሐ. የስድስተኛ መ. የስምንተኛ
፬. መዓዛ አበበችን “ለሁሉም ጊዜ አለው” ሲባል አልሰማሽም ያለቻት
ምን ልታስረዳት ፈልጋ ነው?
ሀ. እድሜያቸው ገና ለአቅመ ሔዋን አለመድረሱን
ለ. ያሉበት የትምህርት ደረጃ ስለፍቅር የሚያስቡበት
አለመሆኑን
146 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፵፮
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ሐ. ፍቅር ጌዜያቸውን ጠብቀው የሚደርሱበት መሆናቸውን
መ. ሁሉም መልስ ይሆናል
፭. አበበችና መዓዛን ግጭት ውስጥ ያስገባቸው ጉዳይ ምንድን ነው?
ሀ. ማትያስ ለመዓዛ የፃፈው የፍቅር ደብዳቤ
ለ. ማትያስ ለአበበች የፃፈው የፍቅር ደብዳቤ
ሐ. አበበች ለማትያስ የፃፈችው የፍቅር ደብዳቤ
መ. መዓዛ ለማትያስ የፃፈችው የፍቅር ደብዳቤ

ክፍል ሁለት፡- መናገር


ተግባር አንድ፡-
በቡድን ተወያይታችሁ ለሚከተሉት ጥያቄዎች በቃል መልስ ስጡ፡፡
፩. ተውኔት ምንድን ነው?
፪. ተውኔት ልቦለዳዊ ወይስ ኢ-ልቦለዳዊ ጽሑፍ ይመስላችኋል?
እንዴት?
፫. የተውኔት አላባውያን የሚባሉትን ዘርዝሩ፡፡

ተግባር ሁለት፡-
ከዚህ በታች የቀረበውን ቃለ ምልልስ ጥንድ ጥንድ ሁናችሁ በማጥናት
ክፍል ውስጥ በቃላችሁ አቅርቡ፡፡

ጋዜጠኛ፡- እንደምን አላችሁ ተማሪዎች? አሁን አንድ እንግዳ


ስለምጋብዝላችሁ በጥሞና ተከታተሉ፡፡
እሽ እንግዳዬ በቅድሚያ ጥሪየን አክብረሽ እዚህ ስለተገኘሽ ከልብ
አመሰግናለሁ፡፡
ወ/ሪት ትህትና፡- እኔም ስለጋበዛችሁኝ አመሰግናለሁ፡፡
ጋዜጠኛ፡- እስኪ በመጀመሪያ ራስዎን ያስተዋውቁ
ወ/ሪት ትህትና፡- ትህትና ሞገስ እባባላለሁ፤ የእውቀት ለብርሃን
የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የልዩ ፍላጎት ባለሙያ ነኝ፡፡

147 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፵፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ጋዜጠኛ፡- እሺ ወ/ሪት ትህትና የልዩ ፍላጎት ትምህርት ማለት ምን
ጋዜጠኛ
ማለት ነው?
ወ/ሪት ትህትና፡- የልዩ ፍላጎት ትምህርት ማለት ከመደበኛ
ትምህርታቸው በተለየ ሁኔታ ልዩ ትምህርት
ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የሚሰጥ ትምህርት ነው፡፡
ጋዜጠኛ፡- የልዩ ፍላጎት ትምህርት አሰጣጥ እንዴት ነው?
ወ/ሪት ትህትና፡- የልዩ ፍላጎት ትምህርት ለሚያስፈልጋቸው
ተማሪዎች በልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህራን አማካኝነት የሚሰጥ
የትምህርት ዓይነት ነው፡፡
ጋዜጠኛ፡- የልዩ ፍላጎት ትምህርት የሚያስፈልጋቸው ምን አይነት
ተማሪዎች ናቸው?
ወ/ሪት ትህትና፡- አይነ ሥውራን፣ መስማት የተሳናቸው፣ የአዕምሮ
እድገት ውስንነት ያለባቸው፣ የባህሪ ችግር ያለባቸው፣ የአካል
ጉዳት ያለባቸው ወይም ደግሞ የተለየ ተሠጥኦ ያላቸው ተማሪዎች
ወዘተ. ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ጋዜጠኛ፡- እሺ ወ/ሪት ትህትና ለሰጠሽን ማብራሪያ በጣም
እናመሰግናለን፡፡ በመጨረሻም የምትይው ነገር ካለሽ እድሉን
ልስጥሽ!
ወ/ሪት ትህትና፡- እሺ! ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ትንሽ
ድጋፍ ከተደረገላቸው እንደማንኛውም ተማሪ ውጤታማ መሆን
ይችላሉ፡፡ ስለዚህ እነዚህን ልጆች ፍቅር እየሰጠን ውጤታማ
እንዲሆኑ ማድረግ የሁላችንም ሀላፊነት መሆኑን አውቀን
ለተግባራዊነቱ ልንተጋ ይገባል፡፡
ጋዜጠኛ፡- እሺ ወ/ሪት ትህትና በጣም አመሰግናለሁ፡፡
ወ/ሪት ትህትና፡- እኔም በጣም አመሰግናለሁ።

148 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፵፰


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል ሶስት፡- ንባብ
ጠልፎ በኪሴ

ቅድመ ምንባብ
፩. “ጠልፎ በኪሴ” በሚል ርዕስ በተጻፈ ተውኔት ምን ርዕሰ ጉዳይ
የሚነሳ ይመስላችኋል?
፪. በሲኒማ የታየውን ነገር ሁሉ በተግባር ለማዋል መሞከር አግባብ
ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? እንዴት?
፫. ከላይ ያለውን ስዕል አይታችሁ የተረዳችሁትን ነገር ግለፁ፡፡

ጠልፎ በኪሴ
ስምንት ሰዓት አካባቢ ነው፤ ሰፊ ቤት ሰፊ ሳሎን ውስጥ የተለያዩ
የቤት እቃዎች ይታያሉ፡፡ ወልደ ጨርቆስ በዝርግ ሰሀን ብርጭቆ
ይዞ ይደረድራል፡፡ ገላግሌ እና ይስሀቅ ደግሞ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለው
ጠረንጴዛ ላይ ካርታ በመደርደር ይጫወታሉ፡፡ በዛብህ ፈንጠር ብሎ

149 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፵፱


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ጋዜጣ እያነበበ ሲሆን ወንዳየሁ በበኩሉ በበዛብህ ተቃራኒ በኩል
ቁጭ ብሎ የሙዚቃ ሸክላ እየደበደበ እየዘፈነ ነው፡፡ በር የተቆለፈባት
ታፈሰች ደግሞ ክፈቱ እያለች በሩን በሀይል ትደበድባለች፡፡
በዛብህ፡- ጥልፊያ አያስፈልግም ወይም አይረባም የምትል ይመስላል
ገላግሌ!
ወልደ ጨርቆስ፡- (ወልደ ጨርቆስ በዝርግ ሰሃን የታጠቡ ብርጭቆዎች
ይዞ ገብቶ ይደረድራል) ምን ልታዘዝ ጌቶቼ?..... የለም? መልካም፣
በቃ ሄድኩላችሁ ተጫወቱ፡፡ (ይወጣል)
ገላግሌ፡- አዎን-በዛብህ፡፡ የተሰራው ስራ በመሰረተ ሀሳቡ አይረባም
ባይ ነኝ፡፡
ይስሃቅ፡- በሃሳቡ መሰረትስ?
በዛብህ፡- ተወው ይናገር፡፡ የሚለውን እንስማ፡፡ አዲስ ሀሳብ ከሆነ
ማድመጥ ግዴታችን ነው፡፡
ገላግሌ፡- ምን ይታወቃል? ስህተታችሁን ስታውቁት ትመለሱ
ይሆናል፡፡
በዛብህ፡- (ይግላል) ሀሳብህ ምንድን ነው?
ይስሃቅ፡- ተንፍሰው - ይውጣልህ፡፡
ገላግሌ፡- እግዜር አይወደውም ነው የምለው፡፡ ሌላ አይደለም፡፡
በዛብህ፡- (በጩኸት) ማስረጃ ነው የሚያስፈልገው-ማስረጃ!
ይስሃቅ፡- መጣባችሁ እንግዲህ! ጨዋታ ሲከር ክርክር ይሆናል፡፡
ገላግሌ፡- የምን ማስረጃ ትፈልጋለህ? ያረመኔ ስራ ነው፡፡ ተምሬያለሁ
የሚል የሰለጠነ ሰው ይህን አያደርግም፡፡
በዛብህ፡- ደሞሳ? ቀጥል…..
ገላግሌ፡- ከደንደር በለስ አይቀሰምም፡፡ በግድ በጉልበት የተቋቋመ
ጋብቻ ሊጸና፣ ደስታን ሊያስገኝ እንዴት ይችላል?
ይስሃቅ፡- ለጽጌሬዳ እሾህ የላትም በለኛ!
በዛብህ፡- (በንቀት) ገላግሌ ምስኪን ነህ፡፡ ያንተ ቢጤዎች ከዚህ ዓለም
ተለይተዋል፡፡ የሰማይቤቱን ስትሰብኩ ዋናውን ነገር ረስታችሁታል!

150 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ


፻፶
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ገላግሌ፡- የአዲሱ ዘመን ጋብቻ ከድሮው ልዩ መሆኑን ማወቅ
አለብህ፡፡መለዮው ፍቅር ነው፡፡ ከመጋባት አስቀድሞ መግባባት
ያስፈልጋል፡፡ ያለ ፍቅር ጋብቻ ደግሞ ሙት ነው፡፡
ይስሃቅ፡- ላይጋቡ መፋቀርም በዝቷል- ያለመጠን በዝቷል
በዘመናችን፡፡አትርሳ፣ ገላግሌ!
ገላግሌ፡- ከቁም ነገር እየገባህ አትበጥብጥ፡፡ ነገሬ ካንተ አይደለም
ካጫፋሪው ከበዛብህ ነው። አንድ ሰው አይቷት የማያውቃትን ልጅ
በምን መሰረት አገባኋት ይላል? የጥልፊያ ጋብቻ ጋብቻ ነው ከተባለም
ቂልነት ነው፡፡ እመኑኝ-ምን አለ በሉኝ- ኋላ ጸጸት ነው ትርፉ፡፡
በዛብህ፡- (በማቃለል) የኋላ ኋላ… በወዲያኛው ዓለም ማለትህ ነው?
ገላግሌ፡- እንዴት አንድ የተማረች ልጅ፣ ያዲሱ ዘመን ወጣት፣
እንዴት በጥልፊያ…
ይስሃቅ፡- አዎ- የከንፈሯን ቀለም፣ የአምባሩን፣ የጉትቻውን፣ የጌጧን፣
የፈርጧን አይተናል፡፡ እንዲህ አርጎም መማር መሰልጠን የለም!
ገላግሌ፡- አታቋርጠኝ ብዬሃለሁ…መዋደዱማ፣ ፍቅሩማ ይቅር….
አይኑን አይታው ከማታውቀው ሰው! እንዴት ደስ ብሏት ልትኖር
ትችላለች? ብታወቀው ይሻላል፣ በዛብህ ቶሪ፡፡ ብስጭት ተላላፊ በሽታ
ነው፣ ሚስትን ከያዘ ባሏን አይምርም፡፡
በዛብህ፡- ደሞሳ?
ገላግሌ፡- (ይበርዳል) ሳውቀው ባልነግራችሁ፣ አብሬያችሁ እየሳቅሁ
ገደል ስትገቡ ዝም ብዬ ባያችሁ፣ ይህ ጓደኝነት አይባልም፡፡ ልጅቱን
ካመጣችሁበት መልሱ፡፡ ከደሙ ንጹህ ነኝ፡፡ እጄን ታጥቤአለሁ፡፡
(ይቀመጣል)
ይስሃቅ፡- እባክህ ተወኝ ወንድሜ……የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም፡፡
እናትሽ ቢቆጡ ቢፈርጡ እንደምቧይ፣የፈሰሰ ውሃ ይታፈሳል ወይ?...
(ወንዳየሁ የሙዚቃ ሸክላ ይዞ እየዘፈነ ይገባል)
በዛብህ፡- ቀጥል ገላግሌ! (ጋዜጣውን በሀይል ወርውሮ ይነሳና በመስኮት
ውጭ ውጭ ያያል)

151 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፶፩


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ገላግሌ፡- ያለኝን ወርውሬያለሁ፡-….እነ ይስሃቅ ሳቁ- ምናለ፣ ሳቁ
(እዚህ ላይ በር ይመታል፡፡ ጸጥታ ይሰፍናል፡፡ በር ዳግመኛ
ይመታል፤ ይተያያሉ፡፡)
ገላግሌ፡- (በትካዜ ራሱን ይደፋል፡፡ ወንዳየሁ ሸክላውን እንደጨበጠ
ቆሞ ይቀራል፡፡)
ወንዳየሁ፡- አሁን ደሞ አረጋ ይሆናል ቀልደኛው….
የልጅቱ ድምጽ፡- ክፈቱ ኋላ ልባርጉ!... (እፎይ ይላሉ፡፡
በዛብህ ግን ዘወር እንኳ አላለም)
ይስሃቅ፡- እሷው ኖራለች ያቺ ግስላ፡፡ ምኗ አስደንጋጯ ነች በሉ?
የልጅቱ ድምጽ፡- ክፈቱ ዛሬ!... (መዝጊያውን በጡጫ ትወርድበታለች)
ይስሃቅ፡- ልጅቱ አበደችና አረፈችው!....ምን ይጠበስ ነው? ብይ፣
አሻፈረኝ፡፡ ጠጪ፣ አሻፈረኝ፡፡ (ይስቃል) (መዝጊያውን ሲንጓጓ
ያደነቁራቸዋል)
በዛብህ፡- (ትዕግስቱ አልቋል) ወንዳየሁ - ክፈትላት፡፡
ወንዳየሁ፡- (ያወላውላል) ይከፈትላት? (መልስ ስላልተሰጠው፣ሊከፍት
ይሄዳል፡፡ ይስሀቅ ካርታውን ይሰበስባል፡፡ ልጅቱ ስትገባ የተቀመጡት
ይነሳሉ፡፡ ገላግሌ አይነሣም፤ጠጉሯ ከመበታተኑም በላይ ቁጣዋና
እልኳ ካረማመዷ ይታያል፡፡ ስትናገር ግምባሯን ኮስትራ ነው፡፡)
ታፈሰች፡- …..እስካሁን ቀልዳችኋል፣ይበቃል፡፡ በናንተ ቤት አባቷ
ነጋድራስ ወርቅነህ ብሩ ባለጸጋ ነጋዴ ናቸውና አንድ ልጃቸውን አፍነን
ብንደብቃት ብር ይከፍላሉ ነው፡፡ እንደዚህ ያለ ጀብዱ ሲሰራ በሲኒማ
ታይቶልኛል! ቂሎች በሲኒማ የታየው ሁሉ እውነት ይመስላችኋል?
(ይስሃቅና ወንዳየሁ ሳቃቸው ይመጣና አፋቸውን ያፍናሉ) ፖሊስ
አሁን ሲይዛችሁ የሳቃችሁትን ያህል ታለቅሷታላችሁ፡፡
በዛብህ፡- ታዲያ ምን ይደረግ ነው?
ታፈሰች፡- (በንቀትና በጥላቻ ዓይነት ታያቸዋለች) አሁን ቀስ በሉና
እቤቴ መልሱኝ፡፡ እኔን ደብቆ ካባባ ገንዘብ እበላለሁ ማለት ዘበት
ነው፡፡ (በትዕቢት እጇን አጣምራ ትቆማለች)

152 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፶፪


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
በዛብህ፡- ንገራት፣ ወንዳየሁ፡፡ ለማኞች ወይንም አጭበርባሪዎች
አይደለንም፤ገንዘብ አንፈልግም፡፡ ንገራት፡፡
ወንዳየሁ፡- ምን ብዬ ልንገራት? እኔ አይሆንልኝም፡፡ ገላግሌ ንገራት፣
በዕድሜም አንተ ትበልጣለህ፡፡ (ገልግሌ ሳይመልስ ይነሳና
ወደ መኝታ ቤት ይገባል)
በዛብህ፡- ይስሃቅ፣ ንገራት፡፡
ይስሃቅ፡- እኔም ቃል ያጥረኛል፡፡….. ሰማዩ ሰሌዳ፣ ውቅያኖሱ
ቀለም ቢሆን እንኳ የዛሬን ቀን ታምራት ለመጻፊያ አይበቃም፡፡
ከታዘዝኩ ግን፣ ምን አደርጋለሁ? (ሊደሰኩር ይታጠቃል) እምህህ
..ህ..ህህ…! ከሁሉ አስቀድሜ ልናገር የምፈልገው ነገር ጥልቀቱ
ከባሕር ውቅያኖስ፣ ርቀቱ ከነፋስ፣ ምጥቀቱ ከራስ ዳሽን ተራራ
የበለጠ መሆኑን ስገልጽልዎ በደስታ ነው፡፡
ታፈሰች፡- (በማመናጨቅ ታቋርጠዋለች) ፍሬ ነገሩን እባክህ ጃል፣
ሌላውን ለበኋላ አቆየው፡፡
ይስሃቅ፡- ፍሬ ነገሩን ካሉ ፍሬ ነገሩን እሺ፡፡ … በዓሉ ሰርግ
ነው፡፡ ከሰርገኞቹ ላስተዋውቅዎ …..(እያመለከተ) እኔ ይስሃቅ ነኝ፣ ያ
ወጣቱ በዛብህ ቶሪ ነው፡፡ ይኸ ወንዳየሁ ነው፡፡ አንደኛው ሚዜ አረጋ
ሲሆን ከምሳ በኋላ ጥቂት ማንቀላፋት ልማዱ ስለሆነ ተኝቷል፡፡
ታፈሰች፡- ሰክሯል መሰለኝ!
ወንዳየሁ፡- አልገባዎትም፡፡ እርስዎ፣ እሜቴ፣ ተጠልፈዋል ነው
የምለው፡፡
ይስሀቅ፡- (እጅ ይነሳል) ይመኑኝ እሜቴ፣ የተጠለፉት ለተቀደሰው
ጋብቻ የተገቡና የታጩ ስለሆነ ነው እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡
ወንዳየሁ፡- የነጋድራስ ወርቅነህ ብሩ ልጅ መሆንዎን ያወቀ የለም፡፡
ይስሃቅ፡- (ደግሞ እጅ ይነሳል) እርስዎ እሜቴ ሙሽራይቱ ሲሆኑ እኛ
ደግሞ ሚዜዎች ነን፡፡
ታፈሰች፡- (አትበገርም) እኔ እቸኩላለሁ ቀልዳችሁ ቅጥ አጣ …. ገና
ሾላ ሚካኤል ሳንደርስ ነው የሚመሸው በኋላ፡፡

153 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፶፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ይስሃቅ፡- ቢያምኑም ባያምኑም እቅጩ ይኸው ነው፡፡
በዛብህ፡- ሌላ ጥያቄ ከሌላት አስገቡና ቆልፉባት፡፡ (ይወጣል) (ቤቱ ጸጥ
ይላል፡፡ ታፈሰች በድንጋጤ ዓይኗ ፍጥጥ ይላል፡፡ ይስሃቅና ወንዳየሁ
እጅና እጇን ይዘው ሲወስዷት ልጅቷ ትታገላለች፣ ትጮሃለች)
(መንግስቱ ለማ፤ ጠልፎ በኪሴ፤1953፣26-
33፤ለማስተማሪነት እንደመች ተሻሽሎ የቀረበ)

አንብቦ መረዳት

ተግባር ሁለት፡-

በተውኔቱ መሰረት ትክክል ከሆነ “እውነት” ስህተት ከሆነ ደግሞ


“ሐሰት” በማለት መልሱ፡፡
፩. ገላግሌ የጠለፋ ጋብቻ አስፈላጊ እንደሆነ አያምንም፡፡
፪. በተውኔቱ ከንፈር መቀባባት፣ አምባር፣ ጉትቻ እና የተለያዩ
ጌጣጌጦች ማድረግ የመማር ምልክት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
፫. አንድ ሰው ጓደኛው ያልሆነ ስራ ሲሰራ እያየ ማለፍ ተገቢ አይደለም፡
፬. የበዛብህና የገላግሌ ግጭት እያደገ ሂዶ እርስ በዕርስ ለመሰነዛዘር
ያርጓቸዋል፡፡
፭. ተውኔቱ የተካሄደበት መቼት በውል አይታወቅም፡፡

ተግባር ሶስት፡-
በተውኔቱ መሰረት ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን
ፊደል በመምረጥ መልሱ፡፡
፩. የተውኔቱ መቼት ____________ነው?
ሀ. የሰፊ ቤት ሳሎን ስምንት ሰዓት አካባቢ
ለ. የትምህርት ቤት ግቢ ስድስት ሰዓት አካባቢ
ሐ. የመዝናኛ ቦታ አራት ሰዓት አካባቢ
መ. የሰፊ ቤት ሳሎን ሁለት ሰዓት አካባቢ
154 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፶፬
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
፪. ጋዜጣ እያነበበ ፈንጠር ብሎ የተቀመጠው ገፀባህርይ ማን ነው?
ሀ. ገላግሌ ለ. በዛብህ ሐ. ይስሀቅ መ. ወንድዬ
፫. ታፈሰች በተባለችው ተዋናይ ላይ የተፈፀመው ድርጊት ምንድን
ነው?
ሀ. ዘረፋ ለ. መደፈር ሐ. ጠለፋ መ. ንጥቂያ
፬. “በግድ፣ በጉልበት የተቋቋመ ጋብቻ ሊፀና፣ ደስታንም ሊያስገኝ
አይችልም” ያለው ተዋናይ ማን ነው?
ሀ. በዛብህ ለ. አራጋው ሐ. ወልደጨርቆስ
መ. ገላግሌ
፭. ይስሃቅ “ለፅጌረዳ እሾህ የላትም በለኛ!” ሲል ምን ማለቱ ነው?
ሀ. ተግባራችን ከንቱ ልፋት ነው።
ለ. ፅጌረዳ እሾህ አልባ ናት።
ሐ. ተግባራችን ፍሬያማ ነው።
መ. እሾህና ፅጌረዳ ግንኙነት የላቸውም።

ተውኔት
ተዋንያን የሌሎችን ሰዎች ባህርይ ወርሰው ክዋኔን ከቋንቋ ጋር
በማዋሀድ መድረክ ላይ የሚያቀርቡት የስነ ፅሁፍ ዘርፍ ነው፡፡
በተዋንያን ተጠንቶና በብዙ ባለሙያዎች ትብብር ተዘጋጅቶ በመድረክ
ላይ ይታይ ዘንድ የተፃፈ ድርሰትም ነው፡፡
የተውኔት ሙያዊ ቃላት

ተዋንያን፡- ገፀባህርያትን ተላብሰው የሚጫወቱት የጥበብ ሰዎች


ናቸው፡፡

ቃለ ተውኔት፡- በተዋንያን መካከል የሚደረግ የንግግር ቅብብሎሽ


ወይም ምልልስ ነው፡፡

ትዕይንት፡- የመጋረጃ መዘጋት የማያስፈልገው አንድ የተውኔት ንዑስ


አሀድ ነው፡፡አጠቃላይ የመድረክ መልክቱን የመለከታል።
155 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፶፭
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ገቢር፡- የተውኔት አንድ አብይ ክፍል ወይም ምዕራፍ ነው፡፡
መነባንብ/ንባበ አዕምሮ/፡- አንድ ገፀ ባህርይ ሌሎች ገጽ ባህሪያት
በዙሪያው በለሌበት ቅፅበት የሚያስበውን
ሁሉ የሚያነበንብበት የብቻ ንግግር ነው
ጎንታ፦ አንድ ግፅ ባህርይ ሌሎች ገፀ ባህሪያት በዙሪያው ባሉበት
ቅፅበትእነሱ እንዳይሰሙት ገለል ብሎ በራሱና በተደራሲያኑ
የሚያነበንበው የብቻ ንግግር ነው።
የተውኔት አላባውያን ፡- የተውኔት አላባዊያን የሚባሉት የሚከተሉት
ናቸው መድረክ(መቼት)፣ ጭብጥ፣ ተዋንያን (ገፀባህርይ)፣ ታሪክ፣
ትልም/ሴራ እና ቋንቋ ናቸው፡፡
ተግባር አራት፡-
ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡
፩. ተዋንያን የሌሎችን ሰዎች ባህርይ ወርሰው ክዋኔን ከቋንቋ ጋር
በማዋሀድ መድረክ ላይ የሚቀርብ የስነፅሁፍ ዘርፍ ምን ይባላል?
ሀ. ግጥም ለ. ተውኔት ሐ. ልቦለድ መ. ስነቃል
፪. ከሚከተሉት አንዱ የተውኔት ባህርይ አይደለም፡፡
ሀ. መድረክ ላይ ሲቀርብ በግልፅ የሚታይ ነው
ለ. ገፀባህርያቱ ምናባዊ ሳይሆኑ ገሀዳዊ ናቸው
ሐ. በተለያዩ ባለሙያዎች ትብብር የሚዘጋጅ ነው
መ. ገፀባህርያቱ ገሀዳዊ ሳይሆኑ ምናባዊ ናቸው
፫. ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ የተውኔት ሙያዊ ቃል አይደለም፡፡
ሀ. ትዕይንት ለ. ገቢር ሐ. ስንኝ መ. ቃለተውኔት
፬. ከተውኔት አላባውያን መካከል ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. ጭብጥ ለ. ገፀባህርይ ሐ. ቋንቋ
መ. መልስ አልተሰጠም
፭. --------------------------የተውኔት ገፀባህርያት ማቅረቢያ ዘዴ
ነው፡፡
ሀ. ምልልስ ለ. ንግር ሐ. ምልሰት መ. ገለፃ

156 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፶፮


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል አራት፡- ጽሕፈት
ተግባር፡-
፩. “ጠልፎ በኪሴ” የሚለውን ተውኔት ሀሳብ በመረዳት በሁለት
አንቀፅ ፅፋችሁ ለመምህራችሁ አሳዩ፡፡
፪. አንድ የተውኔት ርዕስ መርጣችሁ አጭር ተውኔት በፅሁፍ አዘጋጁ፡

ክፍል አምስት፡- ቃላት


ዘይቤ
ዘይቤ የቋንቋ ለዛ ማለት ነው፡፡ለአገላለፃችን ጥንካሬ በመስጠት
የምናስተላልፈው መልዕክት ጎልቶ ወይም ግልፅ ሆኖ እንዲታይ
ለማድረግ የምንጠቀምበት አገላለጽ ወይም የአነጋገር ስልት ነው፡፡

የዘይቤ አይነቶች ብዙ ናቸው ዋና ዋናዎቹ ግን የሚከተሉት ናቸው፡፡

፩. ተነፃፃሪ ዘይቤ ፪. ተለዋጭ ዘይቤ


፫. ሰውኛ ዘይቤ ፬. እንቶኔ ዘይቤ
፭. አያዎ ዘይቤ ፮. ምፀት ዘይቤ
፯. ግነት ዘይቤ

ተግባር፡-
በሚከተሉት ዓረፍተነገሮች ውስጥ ያሉትን የዘይቤ አይነቶች ፃፉ፡፡
፩. ----------------------------------የሰማይ ስባሪ የሚያክል ዳቦ ሰጠኝ፡፡
፪. ----------------------------------አጫውተኝ እንጅ ተራራው!
፫. ---------------------------------ህይዎት ያለው በድን
፬. --------------------------------ብዕር አለቀሰ፡፡
፭. --------------------------------እጁ በረዶ ሆነ፡፡
፮. --------------------------------ሄለን እብድ ይመስል ጨርቋን ጣለች፡

157 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፶፯


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ክፍል ስድስት፡- ሰዋስው

መስተፃምር
መስተፃምር፡- ቃላትን፣ ሀረጋትንና ዓረፍተነገሮችን የሚያያይዝ
ወይም የሚያጣምር አያያዥ ቃል ነው፡፡
ምሳሌ፡- እና፣ ስለሆነም፣ ወይም፣ እንደ፣ እንዲሁም፣ ስለዚህ፣
እስከ፣ ሆኖም፣ ምክንያቱም፣ ወዲያውኑ፣ በኋላ፣
ቢሆንም ወዘተ. ናቸው፡፡
• እነዚህን አያያዥ ቃላት በዓረፍተነገር ውስጥ እንደሚከተለው
መጠቀም ይቻላል፡፡
ምሳሌ፡- ኬክ እና ፒዛ የምወዳቸው ምግቦች ናቸው፡፡
• አሸብር ሲያዩት ጨካኝ ይመስላል ልቡ ግን ሩህሩህ ነው፡፡
• ቀኑ ፀሀያማ ነው ስለዚህ እረፍት ማድረግ አለብኝ፡፡
• አባትህ ተመልሶ አስከሚመጣ ድረስ እዚህ መጠበቅ አለብህ፡፡
ተግባር፡-
ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ከቀረቡት አያያዥ ቃላት መካከል ተገቢ የሆኑትን
በመምረጥ ከታች ያሉትን ዓረፍተነገሮች አሟልታችሁ ፃፉ፡፡

እንደሁ ግን አለበለዚያ

ስለሆነ ነገር ግን ወይም

ስለ ቢሆንም ይሁን እንጅ

፩. ያሬድ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ ነው --------------------- ማጥናት አይወድም፡፡


፪. ጀማል ይመጣ-----------------------------አላወኩም፡፡
፫. ልጁ ታማኝ-------------------------------አምነዋለሁ፡፡
፬. ሄኖክ ብዙ አጥንቶ ነበር፤------------------ፈተናውን አላለፈም፡፡
፭. የገና ጨዋታ ማየት ደስ ይለኛል፤ መጫዎት--------------------------
አልችልም፡፡
፮. ማንበብ አለብህ-------------------------ፈተናውን ልትወድቅ ትችላለህ፡፡
፯. መፅሀፉን መግዛት---------------------ከቤተመፃህፍት መዋስ ትችላለህ፡፡
፰. ውጭው በጣም ---------ሚቀዘቅዝ ጃኬት አመጣሁልህ፡፡
158 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፶፰
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ማጠቃለያ
በዚህ ምዕራፍ ተዋንያን የሌሎችን ሰዎች ባህርይ ወርሰው ክዋኔን ከቋንቋ
ጋር በማዋሀድ መድረክ ላይ የሚያቀርቡት የሥነፅሁፍ ዘርፍ ነው።
ሲባል የተውኔት ሙያዊ ቃላት የሚባሉት ተዋንያን፣ ቃለተውኔት፣
ትዕይንት፣ ገቢር፣ መነባንብ እና ጎንታ መሆናቸውን አይተናል፡፡
የተውኔት ዓላባውያን የሚባሉት ደግሞ መቼት፣ ገፀባህርይ፣ ሴራ፣
ቋንቋ እና ጭብጥ እንደሆኑ ተመልክተናል፡፡
በሌላ በኩል ለአገላለፃችን ጥንካሬ በመስጠት የምናስተላልፈው መልዕክት
ጎልቶ ወይም ግልፅ ሆኖ እንዲታይ ለማድረግ የምንጠቀምበት አባባል
ወይም የዓነጋገር ስልት ዘይቤ ሲባል አይነቶችም ተነፃፃሪ፣ ሰውኛ፣
ተለዋጭ፣ እንቶኔ፣ ምፀት፣ አያዎ፣ ግነት ዘይቤ ወዘተ መሀኖቸውን
ተምረናል፡፡
በተጨማሪም ቃልን ከቃል፣ ሀረግን ከሀረግ፣ ዓረፍተነገርን
ከዓረፍተነገር ለማያያዝ የሚያገለግሉ አያያዥ ቃላት መስተፃምር
እንደሚባሉ መረዳት ችለናል፡፡

የክለሳ ጥያቄዎች
ተግባር አንድ፡-
የሚከተሉትን አያያዥ ቃላት ተጠቅማችሁ ዓረፍተነገር መስርቱ፡፡
ሀ. እንደ መ. ምክንያቱም
ለ. እስከ ሠ. ወዲያውኑ
ሐ. ሆኖም ረ. በኋላ

ተግባር ሁለት፡-
በሚከተሉት ዓረፍተነገሮች ውስጥ ያሉትን የዘይቤ አይነቶች ፃፉ፡፡
ሀ. ፊቱን ተነቅሎ የተቀመጠ የአረም ቅጠል ይመስላል፡፡
ለ. ኢትዮጵያውያን እናት ሀገራቸውን አረንጓዴ ሻማ ለማልበስ ደፋ
ቀና እያሉ ነው፡፡
ሐ. የጨረቃዋ ብርሃን ጤፍ ያስለቅማል፡፡
159 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፶፱
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
የቃላት ፍች
ቃል ፍች
ሙልሙል ዳቦ፣ ጢቢኛ፣ ለከት
መዘላበድ መቀባጠር፣ መቀላመድ
ሚዜ የቅርብ ጓደኛ፣ በጋብቻ ጊዜ
ምስጢር አዋቂ
ራሮት ሀዘኔታ፣ ሀዘን
ቀቢጸተስፋ ተስፋ መቁረጥ
ቀትር እኩለቀን፣ የቀን ግማሽ፣
ተሲያት
ቃለ ተውኔት በሰዎች መካከል የሚደረግ
የፊት ለፊት ንግግር
ቆሌ አድባር፣ አውልያ፣ ውቃቢ፣
ጠባቂ
ቋንጣ በቀጫጭኑ ተዘልዝሎ የደረቀ ስጋ
ቡሃ ነጭ እከክ፣ ለምጽ፣ መላጣ
ቤተ መዘክር ልዩ ልዩ ጥናታዊና ታሪካዊ
ቅርሶች የሚገኙበት
ብራና ከበግ (ፍየል) ቆዳ የሚሰራ እንደ
ወረቀት የሚያገለግል
ነጋድራስ የነጋዴዎች ግብር የሚሰበስብ
የመንግስት ሹም
አማት የሚስት (የባል) እናት ወይም
አባት
አምባር ከአልማዝ፣ ከወርቅና ከመሳሰሉት
የሚሰራ ክንድ ላይ የሚደረግ
ጌጥ
አውታር የድንኳን መወጠሪያ ገመድ
ወይም የበገና፣ የክራር
160 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፷
አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ጅማት
አዕላፍ ብዙ፣ አያሌ
አጋፋሪ አስተናጋጅ፣ አስተናባሪ
እደጥበብ የእጅ ስራ ውጤት
ዋልጌ በስራው ላይ የማይገኝ፣ ወስላታ
ዘረመል ተወራራሽ ባህሪያትን የሚያስተላልፍ
በማንኛውም ሕይወት ያለው
ነገር ውስጥ የሚገኝ ኬሚካል
የታጨ ቃል ያሰረ፣ ለማግባት የተስማማ
ደንደር ኮሸሽላ፣ ሁለንተናው እሾህ የሆነ
እንጨት
ጆሮ ደግፍ አጣዳፊ ተላላፊ የመንጋጭላ እጢ
(እብጠት)
ገመገም እንደ ሰንሰለት የተያያዘ ተራራ
ገቢር የተውኔት አብይ ክፍል
ገጽ ለገጽ ፊት ለፊት
ጉትቻ ከወርቅ (ብር) የሚሰራ የጆሮ ጌጥ
ጉፍታ በራስ በጀርባ ላይ ጣል የሚደረግ
ነጠላ (ልብስ)
ግብዓተ መሬት ቀብር
ጎንታ ገጸ ባሕሪያት ለራሳቸው
የሚያደርጉት ንግግር
ጥልፊያ በሃይል አስገድዶ መውሰድ፣
መንጠቅ
ጥሩር የወታደር የብረት ልብስ
ጥሪት ቅርስ፣ ገንዘብ፣ ሀብት ንብረት
ፈታሂ ፈራጅ፣ ፍርድ ሰጪ
ፍርደ ገምድል አድሏዊ ፍርድ የሚሰጥ

161 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፷፩


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ዋቢ ጽሑፎች
ህይወት እምሻው፡፡ 2010፡፡ ፍቅፋቂ፡፡ አ.አ፣ፋር ኢስት አሳታሚ
ድርጅት፡፡
መስፍን ሀ/ማርያም፡፡ 1976 ፡፡ የቡና ቤት ሥዕሎችና ሌሎችም ወጎች፡
አ.አ፣ የኢትዮጵያ መጻህፍት ድርጅት፡፡
መንግስቱ ለማ ፡፡1953 ፡፡ የተውኔት ጉባዔ፡፡ አ.አ፣ ተራመድ ማተሚያ
ቤት፡፡
ምህረት ሞገስ፡፡ አዲስ ዘመን፣ ጥር 25/ 2012፡፡
ምስራቅ ተረፈ፡፡2009፡፡ ጨው በረንዳ፡፡ ፋር ኢስት ማተሚያ
ድርጅት፡፡
ሞላ ኅብስቱ። 2013። ባዶ ምጥ።
ሰለሞን ሀለፎም፡፡ 1997፡፡ የድርሰት አጻጻፍ፡፡ አ.አ፤ ብራና ማተሚያ
ድርጅት፡፡
ሲሣይ መንግስቴ፡፡ 2006፡፡ ለባሕልና ቱሪዝም ኢንስቲቱት የፓናል
ውይይት የቀረበ ጥናታዊ ጽሁፍ፣ ያልታተመ፡፡
ሳህሉ አክሊሉ እና ፋንቱ ደምሴ፡፡ 1997፡፡ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት
የተማሪ መጽሀፍ አስረኛ ክፍል፡፡ አዲስ አበባ፣ ኩራዝ አሳታሚ
ድርጅት፡፡
በዕውቀቱ ስዩም ፡፡ 2001፡፡ ስብስብ ግጥሞች፡፡ አ.አ፣ ፋርኢስት
ትሬዲንግ፡፡
በድሉ ዋቅጅራ፡፡2009፡፡ ያልተከፈለ ስለት፡፡ አ.አ፣ እሌኒ ማተሚያ
ድርጅት፡፡
ባይ ይማም፡፡ 2002፡፡ አጭርና ቀላል የአማርኛ ሰዋስው፡፡ አ. አ፣
አልፋ አታሚዎች፡፡
ታሪኩ ፋንታዬ፡፡ 2001፡፡ አማርኛ ሁሉ ለሁሉ፡፡ አ.አ፣ ዜድ .ኤ
ማተሚያ ቤት
አለም እሸቱ እና ግርማ አውግቸው ፡፡1998፡፡ የአማርኛ ቋንቋ
ትምህርት የተማሪ መጽሃፍ አስራ ሁለተኛ ክፍል፡፡ አዲስ አበባ፤

162 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፷፪


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት፡፡
አምሳሉ አክሊሉ እና ዳኛቸው ወርቁ፡፡ 1993፡፡ የአማርኛ ፈሊጦች፡፡
አ.አ ሜጋ አሳታሚ ድርጅት፡፡
አብክመ ፕላን ኮሚሽን፡፡ 2012 የስነ ህዝብና ልማት ቅንጅት
ዳይሬክቶሬት፣ ያልታተመ፡፡
አብክመ፡፡ የአካባቢ የደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን
የኮሚኒኬሽ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት፣ ያልታተመ፡፡
አ.አ.ከ.አ. ት/ቢሮ፡፡ 2007፡፡ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛና ህገ ወጥ
ዝውውርን ለመከላከል የተዘጋጀ መጽሃፈ ዕድ፣ ያልታተመ፡፡
ዘሪሁን አስፋው፡፡ 1998፡፡ የስነጽሁፍ መሰረታውያን፡፡ አ.አ፣ ንግድ
ማተሚያ ድርጅት፡፡
የሺጥላ መንግስቴ፡፡ 2004፡፡ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪ
መጽሀፍ አስራ አንደኛ ክፍል፡፡ አዲስ አበባ፣ ኩራዝ አሳታሚ
ድርጅት፡፡
የሻው ተሰማ፡፡ 1996፡፡ ልሳነ ብዕር ከመ ልሳነ ሰብዕ፡፡ አ.አ፣ብራና
ማተሚያ ድርጅት፡፡
፡፡ 1998፡፡ የተውኔት አጽናፍ መነጽር ፡፡አ.አ ፣አርቲስቲክ
ማተሚያ ቤት፡፡
ድንቄሳ ደሬሳ እና ጽጌ አበበ፡፡ 1999፡፡ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት
የተማሪ መጽሀፍ አስራ አንደኛ ክፍል፡፡ አዲስ አበባ፣ ኩራዝ
አሳታሚ ድርጅት፡፡
ጌታሁን አማረ፡፡1989፡፡ የአማርኛ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ፡፡ አ.አ፣
ንግድ ማተሚያ ድርጅት፡፡
ጽጌሬዳ ጫንያለው፡፡ አዲስ ዘመን፣ ነሀሴ 12 /2011፡፡
፡፡ አዲስ ዘመን፣ ሐምሌ 28/ 2011 ፡፡

163 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፷፫


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

የአማርኛ የፊደል ገበታ

ግዕዝ ካዕብ ሣልስ ራብዕ ኃምስ ሳድስ ሳብዕ


ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ
ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ
ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሕ ሖ
መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞ
ሠ ሡ ሢ ሣ ሤ ሥ ሦ
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ
ሰ ሱ ሲ ሳ ሴ ስ ሶ
ሸ ሹ ሺ ሻ ሼ ሽ ሾ
ቀ ቁ ቂ ቃ ቄ ቅ ቆ
በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ
ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ
ቸ ቹ ቺ ቻ ቼ ች ቾ
ኀ ኁ ኂ ኃ ኄ ኅ ኆ
ነ ኑ ኒ ና ኔ ን ኖ
ኘ ኙ ኚ ኛ ኜ ኝ ኞ
አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ
ከ ኩ ኪ ካ ኬ ክ ኮ
ኸ ኹ ኺ ኻ ኼ ኽ ኾ
ወ ዉ ዊ ዋ ዌ ው ዎ
ዐ ዑ ዒ ዓ ዔ ዕ ዖ
ዘ ዙ ዚ ዛ ዜ ዝ ዞ
ዠ ዡ ዢ ዣ ዤ ዥ ዦ
የ ዩ ዪ ያ ዬ ይ ዮ
ደ ዱ ዲ ዳ ዴ ድ ዶ
ጀ ጁ ጂ ጃ ጄ ጅ ጆ
ገ ጉ ጊ ጋ ጌ ግ ጎ

164 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፷፬


አማርኛ ፰ኛ ክፍል
ጠ ጡ ጢ ጣ ጤ ጥ ጦ
ጨ ጩ ጪ ጫ ጬ ጭ ጮ
ጰ ጱ ጲ ጳ ጴ ጵ ጶ
ጸ ጹ ጺ ጻ ጼ ጽ ጾ
ፀ ፁ ፂ ፃ ፄ ፅ ፆ
ፈ ፉ ፊ ፋ ፌ ፍ ፎ
ፐ ፑ ፒ ፓ ፔ ፕ ፖ
ቨ ቩ ቪ ቫ ቬ ቭ ቮ

የኢትዮጵያ ቁጥሮች

፩ 1 ፪ 2 ፫ 3 ፬ 4 ፭ 5 ፮ 6 ፯ 7 ፰ 8 ፱ 9 ፲ 10
፲፩ ፲፪ ፲፫ ፲፬ ፲፭ ፲፮ ፲፯ ፲፰ ፲፱ 20
፳፩ ፳፪ ፳፫ ፳፬ ፳፭ ፳፮ ፳፯ ፳፰ ፳፱ 30
፴፩ ፴፪ ፴፫ ፴፬ ፴፭ ፴፮ ፴፯ ፴፰ ፴፱ 40
፵፩ ፵፪ ፵፫ ፵፬ ፵፭ ፵፮ ፵፯ ፵፰ ፵፱ ፶ 50
፶፩ ፶፪ ፶፫ ፶፬ ፶፭ ፶፮ ፶፯ ፶፰ ፶፱ 60
፷፩ ፷፪ ፷፫ ፷፬ ፷፭ ፷፮ ፷፯ ፷፰ ፷፱ 70
፸፩ ፸፪ ፸፫ ፸፬ ፸፭ ፸፮ ፸፯ ፸፰ ፸፱ 80
፹፩ ፹፪ ፹፫ ፹፬ ፹፭ ፹፮ ፹፯ ፹፰ ፹፱ ፺ 90
፺፩ ፺፪ ፺፫ ፺፬ ፺፭ ፺፮ ፺፯ ፺፰ ፺፱ ፻ 100
፪፻ 200 ፫፻ 300 ፬፻ 400 ፭፻ 500 ፮፻ 600
፯፻ 700 ፰፻ 800 ፱፻ 900 ፲፻ 1000 ፳፻ 2000

፴፻ 3000 ፵፻ 4000 ፶፻ 5000 ፷፻ 6000 ፸፻ 7000


፹፻ 8000 ፺፻ 9000 ፻፻ 10000

165 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፻፷፭


አማርኛ ፰ኛ ክፍል

አማርኛ
እንደ መጀመሪያ ቋንቋ
የተማሪ መጽሐፍ

፰ኛ ክፍል

166 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

You might also like