መፈንቅል
Appearance
መፈንቅል የማይልመጠመጥ ጠንካራ እቃ ሲሆን ከደጋፊ ችካል ላይ በመቀመጥ ሸክምን ለማንሳት በሚደረገው ስራ ጉልበትን ለማባዛት ወይም ሸክሙ የሚሄደውን ርቀት ከፍል ለማድረግ የሚጠቅም ቀላል ማሽን ነው። የጥንቱ የግሪክ ሂሳብ ተመራማሪ የነበረው አርክሜድስ፣ የመፈንቅልን ጉልበት የማብዛት ጠባይ በማዳነቅ እንዲህ ብሎ ነበር የምቆምበት ቦታ ስጡኝ እንጂ፣ መሬትን በመፈንቅል አነሳታለሁ። በጥንቱ ግብጽ አናጺወች ወደ 100 ቶን የሚጠጉ የድንጋይ ቅርጾችን በመፈንቅል ያነሱ እንደነበር ታሪክ ይዘግባል [1]።
- ዓይነት 1፡ መደገፊያው በጉልበቱና በሸክሙ መካከል የሆነ። ምሳሌ መቀስ፣ ከፍ-ዝቅ
- ዓይነት 2፡ ሸክሙ በመደገፊያውና በጉልበቱ መካከል የሆነ። ምሳሌ እጅ ጋሪ
- ዓይነት 3፡ ጉልበቱ በሸክሙና በመደገፊያው መካከል የሆነ። ምሳሌ ትዊዘር፣ የሰው ልጅ መንጋጭላ
- ^ Budge|first=E.A. Wallis|title=Cleopatra's Needles and Other Egyptian Obelisks|publisher=Kessinger Publishing|year=2003|page=28|isbn=9780766135246
- (እንግሊዝኛ) Lever Archived ጃንዩዌሪ 14, 2007 at the Wayback Machine at Diracdelta science and engineering encyclopedia
- (እንግሊዝኛ)A Simple Lever by Stephen Wolfram, Wolfram Demonstrations Project.
- (እንግሊዝኛ)Levers: Simple Machines at EnchantedLearning.com